የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክርስቶስ ጉባኤውን ይመራል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | መጋቢት 15
    • 5, 6. (ሀ) ሐዋርያው ዮሐንስ በተቀበለው ራእይ ውስጥ ‘ሰባቱ የወርቅ መቅረዞች’ እና ‘ሰባቱ ከዋክብት’ ምን ያመለክታሉ? (ለ) ‘ሰባቱ ከዋክብት’ በኢየሱስ ቀኝ እጅ ውስጥ መሆናቸው ምን ያመለክታል?

      5 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው የራእይ መጽሐፍ ታማኝና ልባም ባሪያ በቀጥታ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን ሥር እንደሆነ ይናገራል። ሐዋርያው ዮሐንስ ‘የጌታን ቀን’ በማስመልከት በተመለከተው ራእይ ውስጥ ‘ሰባት የወርቅ መቅረዞች እና በመቅረዞቹም መካከል በቀኝ እጁ ሰባት ከዋክብት የያዘ የሰው ልጅ የሚመስል’ ተመልክቷል። ኢየሱስ ራእዩን ለዮሐንስ ሲገልጽለት እንዲህ አለ:- “በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፣ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።”​—⁠ራእይ 1:1, 10-20

      6 ‘ሰባቱ የወርቅ መቅረዞች’ በ1914 በጀመረው ‘የጌታ ቀን’ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የእውነተኛ ክርስቲያን ጉባኤዎች ያመለክታሉ። ሆኖም ‘ሰባቱ ከዋክብት’ ምንድን ናቸው? በመጀመሪያ ደረጃ የሚያመለክቱት በአንደኛው መቶ ዘመን ለነበሩት ጉባኤዎች እንክብካቤ ያደርጉ የነበሩትን በመንፈስ የተወለዱትን ቅቡዓን የበላይ ተመልካቾች በሙሉ ነው።a የበላይ ተመልካቾቹ በኢየሱስ ቀኝ እጅ ውስጥ ማለትም በእርሱ ቁጥጥርና አመራር ሥር ነበሩ። አዎን፣ ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰዎች የተውጣጣውን የባሪያ ክፍል መርቷል። ይሁን እንጂ በአሁኑ ጊዜ የቅቡዓን የበላይ ተመልካቾች ቁጥር በጣም ጥቂት ነው። ታዲያ የክርስቶስ አመራር በዓለም ዙሪያ ለሚገኙት ከ93, 000 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤዎች በሙሉ የሚዳረሰው እንዴት ነው?

      7. (ሀ) ኢየሱስ በመላው ምድር የሚገኙ ጉባኤዎችን ለመምራት የአስተዳደር አካሉን የሚጠቀመው እንዴት ነው? (ለ) ክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች በመንፈስ ቅዱስ የተሾሙ ናቸው ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው?

      7 እንደ መጀመሪያው መቶ ዘመን ሁሉ በአሁኑም ጊዜ ከቅቡዓን የበላይ ተመልካቾች መካከል የተውጣጣ መላውን ታማኝና ልባም ባሪያ የሚወክል ብቃት ያላቸውን ወንዶች ያቀፈ አንድ አነስተኛ ቡድን የአስተዳደር አካል ሆኖ ያገለግላል። መሪያችን ይህን የአስተዳደር አካል በመጠቀም በመንፈስ ከተቀቡትም ሆነ ካልተቀቡት መካከል በጉባኤ ውስጥ ሽማግሌ ሆነው እንዲያገለግሉ ብቃት ያላቸው ወንዶችን ይሾማል። በዚህ ረገድ ኢየሱስ እንዲጠቀምበት ይሖዋ የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። (ሥራ 2:32, 33) በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ የበላይ ተመልካቾች በመንፈስ ቅዱስ አነሣሽነት በተጻፈው በአምላክ ቃል ውስጥ የሰፈሩትን ብቃቶች ማሟላት ይገባቸዋል። (1 ጢሞቴዎስ 3:1-7፤ ቲቶ 1:5-9፤ 2 ጴጥሮስ 1:20, 21) የድጋፍ ሐሳብ የሚቀርበው እንዲሁም ሹመቱ የሚጸድቀው ጸሎት ከተደረገ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው። በተጨማሪም የሚሾሙት ግለሰቦች የዚህን መንፈስ ፍሬ እንዳፈሩ በግልጽ ያሳያሉ። (ገላትያ 5:22, 23) እንግዲያው ጳውሎስ “ለራሳችሁና እግዚአብሔር ጠባቂ አድርጎ በላዩ ለሾማችሁ መንጋ ሁሉ ተጠንቀቁ” በማለት የሰጠው ምክር ለሁሉም ሽማግሌዎች፣ ለተቀቡትም ሆነ ላልተቀቡት በእኩል ደረጃ ይሠራል። (ሥራ 20:28 አ.መ.ት ) እነዚህ የተሾሙ ወንዶች ከአስተዳደር አካሉ መመሪያ ይቀበላሉ እንዲሁም በፈቃደኝነት ጉባኤውን ይጠብቃሉ። በዚህ መንገድ ክርስቶስ ከእኛ ጋር በመሆን ጉባኤውን በሚገባ ይመራል።

  • ክርስቶስ ጉባኤውን ይመራል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | መጋቢት 15
    • a እዚህ ላይ የተጠቀሱት “ከዋክብት” ቃል በቃል መላእክትን አያመለክቱም። ኢየሱስ አንድን ሰብዓዊ ሰው በመጠቀም በዓይን ለማይታዩ መንፈሳዊ ፍጥረታት መልእክት እንደማያጽፍ የተረጋገጠ ነው። ስለዚህ ‘ከዋክብቱ’ በጉባኤ ውስጥ ያሉትን የኢየሱስ መልእክተኛ እንደሆኑ ተደርገው የተቆጠሩትን ሰብዓዊ የበላይ ተመልካቾችን ወይም ሽማግሌዎችን የሚያመለክቱ መሆን አለባቸው። ቁጥራቸው ሰባት መሆኑ በአምላክ የተወሰነ ሙላትን ያመለክታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ