-
በራእይ ምዕራፍ 17 ላይ የተጠቀሰው ደማቅ ቀይ አውሬ ምን ያመለክታል?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
ለአጭር ጊዜ አይኖርም። የመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኅበር የተቋቋመው አንደኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ነበር፤ ዓላማው ሰላም ማስፈን የነበረ ቢሆንም በዓለም ዙሪያ ግጭቶችን መከላከል አልቻለም። ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በ1939 ሲፈነዳ አገልግሎት መስጠቱን አቆመ። ሁለተኛው የዓለም ጦርነት በ1945 ሲያበቃ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቋቋመ። የዚህ ድርጅት ዓላማ፣ አሠራርና አወቃቀር ከመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኅበር ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል።
-
-
በራእይ ምዕራፍ 17 ላይ የተጠቀሰው ደማቅ ቀይ አውሬ ምን ያመለክታል?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
c ለምሳሌ ያህል፣ በአሜሪካ የሚገኙ በፕሮቴስታንት ሥር የሚታቀፉ በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን የሚወክል ምክር ቤት፣ የቃል ኪዳኑ ማኅበር “የአምላክን መንግሥት በምድር ላይ የሚወክል ፖለቲካዊ ምልክት” እንደሆነ በ1918 ገልጾ ነበር። በ1965 የሂንዱይዝም፣ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ፣ የቡድሂዝም፣ የአይሁድ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት እምነት ተወካዮች ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ለመጸለይ በሳን ፍራንሲስኮ ተሰብስበው ነበር። በ1979 ደግሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዳግማዊ ጆን ፖል፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት “ከፍተኛው የሰላምና የፍትሕ መድረክ ሆኖ እንዲቀጥል” ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል።
-