የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w15 7/1 ገጽ 15
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እንጀራ ከገበታ እንዳይጠፋ ትልቅ ድርሻ የሚያበረክተው ወፍጮ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • ጥርስህን የማፋጨት ልማድ አለህን?
    ንቁ!—1998
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
w15 7/1 ገጽ 15

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በጥንት ዘመን ሰዎች በእጅ ወፍጮ የሚጠቀሙት እንዴት ነበር?

የእጅ ወፍጮዎች እህል ፈጭቶ የዳቦ ዱቄት ለማዘጋጀት ያገለግሉ ነበር። በየትኛውም ቤት ውስጥ ማለት ይቻላል በእንዲህ ዓይነት ወፍጮዎች እህል መፍጨት ሴቶች ወይም አገልጋዮች የሚያከናውኑት የዕለት ተዕለት ሥራ ነበር። በጥንት ዘመን የወፍጮ ድምፅ በየዕለቱ ከሚከናወን ሥራ ጋር ተዛማጅነት ነበረው።—ዘፀአት 11:5፤ ኤርምያስ 25:10

በእጅ ወፍጮ እህል ሲፈጭ የሚያሳይ አንድ የግብፃውያን ሐውልት

በጥንቷ ግብፅ የተገኙ ጥንታዊ ሥዕሎችና ሐውልቶች በእጅ ወፍጮ እንዴት እንደሚፈጭ ያሳያሉ። የእጅ ወፍጮው ጎድጎድ ብሎ ከፊት በኩል ዘቅዘቅ ያለ ሲሆን ከላይ መጅ አለው። የምትፈጨው ሴት ትንበረከክና ወፍጮውን ከፊቷ አድርጋ መጁን በሁለት እጅዋ በመያዝ በኃይል ተጭና ገፋ መለስ እያደረገች በድንጋዮቹ መሃል ያለውን እህል ትፈጫለች። አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ እንደሚናገረው በአብዛኛው የሚሠራበት የአንድ መጅ ክብደት ከ2 እስከ 4 ኪሎ ግራም ይመዝናል። እንዲህ ዓይነቱ መጅ ጥቃት ለማድረስ ከተጠቀሙበት ሰው ሊገድል ይችላል።—መሳፍንት 9:50-54

ወፍጮና መጅ ለአንድ ቤተሰብ ሕልውና ወሳኝ ነገር ስለሆነ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሕግ ወፍጮውንና መጁን በመያዣነት መውሰድን ይከለክላል። ዘዳግም 24:6 “ማንም ሰው ወፍጮን ወይም መጅን የብድር መያዣ አድርጎ መውሰድ የለበትም፤ ምክንያቱም የሰውየውን መተዳደሪያ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆንበታል” በማለት ይገልጻል።

“እቅፍ” የሚለው አባባል ምን ያመለክታል?

በመጨረሻው የፋሲካ በዓል ወቅት ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠግቶ

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ “በአብ እቅፍ” እንዳለ አድርጎ ይገልጻል። (ዮሐንስ 1:18 የግርጌ ማስታወሻ) ይህ አገላለጽ ኢየሱስ ከአምላክ ጋር ያለውን የተለየ ቅርበትና በእሱ ዘንድ ያገኘውን ሞገስ ያመለክታል። ይህ አባባል አይሁዳውያን በማዕድ ፊት በሚቀመጡበት ጊዜ ይከተሉት የነበረውን ልማድ በተዘዋዋሪ የሚጠቅስ ነው።

ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ጊዜ አይሁዳውያን በመመገቢያ ጠረጴዛው ዙሪያ በተደረደሩ መከዳዎች ላይ ጋደም ብለው ይቀመጡ ነበር። በማዕዱ ዙሪያ ያለው እያንዳንዱ ተመጋቢ ራሱን ወደ ማዕዱ አድርጎ እግሮቹን ወደ ኋላ በመዘርጋት በግራ ክርኑ መከዳው ላይ ተደግፎ ይቀመጥ ነበር። ይህ አቀማመጥ ቀኝ እጁ ነፃ እንዲሆንለት ያስችለዋል። ተመጋቢዎቹ በሙሉ በግራ ጎናቸው በኩል አንዱ ከሌላው አጠገብ ጋደም ስለሚሉ አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ “የአንዱ ሰው ራስ ከኋላው ወዳለው ሰው ደረት ይጠጋል” በማለት ይገልጻል፤ ይህ ጽሑፍ በመቀጠል “በመሆኑም አንደኛው ሰው በሌላኛው ሰው ‘እቅፍ’ እንዳለ ተደርጎ ይቆጠር ነበር” ብሏል።

በአንድ የቤተሰብ ራስ አሊያም በአንድ ጋባዥ ደረት አጠገብ ጋደም ማለት ልዩ ክብር ወይም መብት እንደማግኘት ተደርጎ ይቆጠር ነበር። ስለሆነም ኢየሱስ ለመጨረሻ ጊዜ ባከበረው የፋሲካ በዓል ላይ አጠገቡ ጋደም ብሎ የነበረው “ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር” ማለትም ሐዋርያው ዮሐንስ ነበር። ስለዚህ ዮሐንስ ኢየሱስን አንድ ነገር ለመጠየቅ ከፈለገ ‘ወደ ደረቱ ጠጋ’ ማለት ይችል ነበር።​—⁠ዮሐንስ 13:23-25፤ 21:20

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ