-
እድገትህ በግልጽ እንዲታይ አድርግየመንግሥት አገልግሎት—1995 | ታኅሣሥ
-
-
እድገትህ በግልጽ እንዲታይ አድርግ
1 መጀመሪያ የመንግሥቱን መልእክት የሰማህበትን ጊዜ አስታውስ። ቀላል የሆኑ እውነቶች እውቀትና ማስተዋል ለማግኘት ያለህን ፍላጎት ቀስቅሰውታል። መንገዶችህ ከይሖዋ መንገዶች የራቁ ስለነበሩ አኗኗርህን የማስተካከሉን አስፈላጊነት ብዙም ሳይቆይ ተገንዝበህ ነበር። (ኢሳ. 55:8, 9) እድገት አደረግህና ራስህን ለአምላክ ወስነህ ተጠመቅህ።
2 አንዳንድ መንፈሳዊ እድገቶች ካደረግክ በኋላ እንኳ መወገድ የነበረባቸው ድክመቶች ነበሩ። (ሮሜ 12:2) ምናልባትም በመስክ አገልግሎት ለመካፈል ፈራ ተባ እንድትል ያደረገህ የሰው ፍርሃት አድሮብህ ይሆናል። ወይም የአምላክን መንፈስ ፍሬዎች ማሳየት አስቸጋሪ ሆኖብህ ይሆናል። ያላንዳች ማመንታት ለራስህ ቲኦክራሲያዊ ግቦችን በማውጣት እድገት ለማድረግ ወስነህ ነበር።
3 አሁን ራስህን ከወሰንክ ብዙ ዓመታት አልፈው ሊሆን ይችላል። መለስ ብለህ ስትመለከት ምን እድገት አድርገሃል? አንዳንዶቹ ግቦችህ ላይ ደርሰሃልን? “መጀመሪያ” የነበረህ ዓይነት ቅንዓት አለህን? (ዕብ. 3:14) ጳውሎስ ጢሞቴዎስን “ማደግህ በነገር ሁሉ እንዲገለጥ ይህን አስብ፣ ይህንም አዘውትር” በማለት ሲመክረው ጢሞቴዎስ የብዙ ዓመታት ተሞክሮ የነበረው የጎለመሰ ክርስቲያን ነበር።— 1 ጢሞ. 4:15
4 ራስን በራስ መመርመር አስፈላጊ ነው፦ የቀድሞ አኗኗራችንን መለስ ብለን ስንመረምር ጥናት ስንጀምር የነበሩብንን አንዳንድ ድካሞች አሁንም እንዳሉ ናቸውን? አንዳንድ ያወጣናቸው ግቦች ላይ መድረስ ተስኖናልን? ከሆነ ምክንያቱ ምንድን ነው? ጥሩ ዕቅዶች ቢኖሩንም እንኳ ዛሬ ነገ እንል ይሆናል። ምናልባት የኑሮ ጭንቀቶች ወይም የዚህ ሥርዓት ተጽዕኖዎች የምናደርገውን እድገት እንዲጎትቱብን ፈቅደንላቸው ሊሆን ይችላል።— ሉቃስ 17:28-30
5 ላለፈው ጊዜ ምንም ማድረግ ባንችልም ለወደፊቱ ግን ማድረግ የምንችለው ነገር ይኖራል። ራሳችንን በሃቀኝነት ጠለቅ ብለን በመመርመር ድክመታችን ምን እንደሆነ ማወቅና ለማሻሻል በሙሉ ኃይላችን ጥረት ማድረግ እንችላለን። ራስን መግዛት፣ የዋህነት ወይም ትዕግሥት የመሳሰሉ የመንፈስ ፍሬዎችን በማፍራት ረገድ ይበልጥ ጥረት ማድረግ ያስፈልገን ይሆናል። (ገላ. 5:22, 23) ከሌሎች ጋር ተስማምቶ መኖር ወይም ከሽማግሌዎች ጋር ተባብሮ መሥራት ካስቸገረን የዋህነትና ትሕትና ማዳበር ያስፈልገናል።— ፊልጵ. 2:2, 3
6 አንዳንድ የአገልግሎት መብቶች ላይ ለመድረስ በመጣጣር እድገታችንን በግልጽ ማሳየት እንችላለንን? ወንድሞች ተጨማሪ ጥረት በማድረግ ዲያቆን ወይም ሽማግሌ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዳንዶቻችን የዘወትር አቅኚ መሆን እንችላለን። ብዙዎች ረዳት አቅኚነት ሊደረስበት የሚችል ግብ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ። ሌሎች ደግሞ የግል ጥናት ልማዳቸውን ለማሻሻል፣ በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ይበልጥ ንቁ ተሳታፊ ለመሆን ወይም ይበልጥ ፍሬያማ የጉባኤ አስፋፊዎች ለመሆን ጥረት ሊያደርጉ ይችላሉ።
7 እርግጥ ነው፣ በምን ረገድ እድገት ማድረግ እንዳለብን የምንወስነው ራሳችን ነን። “ወደ ጉልምስና ለመድረስ” የምናደርገው ልባዊ ጥረት ደስታችንን እንደሚጨምርልንና ፍሬያማ የጉባኤው አባላት እንደሚያደርገን እርግጠኞች መሆን እንችላለን።— ዕብ. 6:1 አዓት
-
-
የታኅሣሥ ወር የአገልግሎት ስብሰባዎችየመንግሥት አገልግሎት—1995 | ታኅሣሥ
-
-
የታኅሣሥ ወር የአገልግሎት ስብሰባዎች
ታኅሣሥ 4 የሚጀምር ሳምንት
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
15 ደቂቃ፦ “ይሖዋን በየዕለቱ አወድሱት።” በጥያቄና መልስ። አንቀጾቹ ይነበቡ። አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሲያገለግሉ ያጋጠሟቸውን የሚያበረታቱ ተሞክሮዎች ይናገሩ።
20 ደቂቃ፦ “በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት።” ይህንን መጽሐፍ በተለይ ቀደም ሲል ስናነጋግራቸው ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች የማበርከትን አስፈላጊነት ጠበቅ አድርገህ ግለጽ። የተሰጡትን አቀራረቦች ከልስና በእነዚህ አቀራረቦች አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ።
መዝሙር 212 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 11 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 215
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት። በመስክ አገልግሎት የተሟላና ትርጉም ያለው ተሳትፎ ለማድረግ ዕቅድ ማውጣት ያለብን ለምን እንደሆነ የሚያሳዩ ጥቂት ምክንያቶች አጠር አድርገህ አቅርብ። መስክ ወጥተን አንድ ሰዓት አገልግለን ከመመለስ ይልቅ የሚቻል ከሆነ ለምን ሁለት ሰዓት ወይም ከዚያ በላይ ለማገልገል እቅድ አናወጣም? ብዙውን ጊዜ በአገልግሎታችን ስኬታማ መሆን የምንችለው ለተመላልሶ መጠየቆች ቀደም ብለን የምንዘጋጅና ሁለት ሰዓት ወይም ከዚያ በላይ በመስክ አገልግሎት ለማሳለፍ ዕቅድ ካላቸው አስፋፊዎች ጋር የምናገለግል ከሆነ ነው።
20 ደቂቃ፦ “የመስክ አገልግሎታችንን ሪፖርት ማድረግ ያለብን ለምንና እንዴት ነው?” የጉባኤው ጸሐፊ ሪፖርት ማድረግን በተመለከተ ለጉባኤው በሚስማማ መንገድ አገልግሎታችን በተባለው መጽሐፍ ገጽ 102-110 ላይ የተመሠረተ ማብራሪያ ይሰጣል። ተመላልሶ መጠየቅ ተብለው ሪፖርት ሊደረጉ የሚችሉት የተለያዩ ሁኔታዎች የትኞቹ እንደሆኑ፣ አዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ሪፖርት የሚደረጉት ከመቼ ጀምሮ እንደሆነ፣ አንድ ወላጅ ልጆቹን መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስጠና አንድ ጥናት ብቻ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት (ወላጆች ልጆቻቸውን ሲያስጠኑ አብሮ የሚያጠና ሌላ ሰው በሚኖርበትም ጊዜ እንኳ ይህ ሰው ሁለተኛ ጥናት ተደርጎ ሪፖርት ሊደረግ አይችልም) እና አንድ አስፋፊ ወደ ሌላ ጉባኤ ሲዛወር ምን ማድረግ እንዳለበት ግልጽ አድርግላቸው። ሪፖርት ማድረግን በተመለከተ ያሉትን የተሳሳቱ ሐሳቦች አርም።
17 ደቂቃ፦ “ለጉባኤ ስብሰባዎች መዘጋጀትና ከስብሰባዎቹ መጠቀም።” ንግግርና ውይይት። አንድ ወይም ሁለት አስፋፊዎች ከስብሰባዎች ደስታና ሙሉ ጥቅም እንዲያገኙ ያስቻላቸው ምን ነገር ማድረጋቸው እንደሆነ እንዲናገሩ አድርግ።
መዝሙር 47 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 18 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 204
10 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። በበዓላት ሰሞን ለሚቀርቡ ሰላምታዎች እንዴት በዘዴ መልስ መስጠት እንደሚቻል ጥቂት ሐሳቦች አቅርብ።
15 ደቂቃ፦ “እድገትህ በግልጽ እንዲታይ አድርግ።” በጥያቄና መልስ።
20 ደቂቃ፦ “ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተመልሳችሁ አነጋግሩ።” የተሰጡትን አቀራረቦች ከልስና ሁለት አጠር ያሉ ሠርቶ ማሳያዎች አቅርብ። ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ግብ በማድረግ ተመላልሶ መጠየቅ እንዲያደርጉ አበረታታ።
መዝሙር 19 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ታኅሣሥ 25 የሚጀምር ሳምንት
5 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከጥር 1 ጀምሮ ስብሰባ የምታደርጉበት ጊዜ የሚለወጥ ከሆነ ወንድሞች አስፈላጊ የሆኑ ማስተካከያዎች በማድረግ ሙሉ ትብብር እንዲያደርጉ አበረታታ።
15 ደቂቃ፦ “ወደ ውጪ አገር የመሄድን ጉዳይ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ማገናዘብ” በሚለው ርዕስ ላይ አንድ ሽማግሌ ከአንድ ወጣት ወንድም ጋር ይወያያል። ወጣቱ ወንድም መደምደሚያው ላይ አድናቆቱን ይገልጽና የመንግሥቱ አገልጋዮች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ተዛውሮ ለማገልገል የይሖዋን እርዳታ ለማግኘት ጥረት እንደሚያደርግ ይናገራል። ወጣቱ ወንድም ምሥጢራዊ ዕቅድ ከማውጣት ይልቅ ያለውን ሐሳብ በግልጽ ስላወያየው ሽማግሌው ያመሰግነዋል።
25 ደቂቃ፦ “ብርሃናችን ሳያቋርጥ እንዲበራ ማድረግ።” ከ1-5 ላይ ያሉትን አንቀጾች አጠር ባለ መንገድ መግቢያ አድርገህ ተጠቀምባቸው። ከ6-16 ያሉት አንቀጾች በጥያቄና መልስ ይሸፈናሉ። አንቀጽ 6-9, 15 እና 16ን አንብብ። ከ17-19 ያሉትን አንቀጾች መደምደሚያ አድርገህ ተጠቀምባቸው። የሚቻል ከሆነ የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ያቅርበው።
መዝሙር 4 እና የመደምደሚያ ጸሎት።
-