የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ጥናት ለማስጀመር የሚረዳ አዲስ መሣሪያ አግኝተናል!
    የመንግሥት አገልግሎት—2001 | ኅዳር
    • ካሄድበትን መንገድ አሳየው። ይህ ቀላል አቀራረብ አይደለም?

      9 አድማጭህ በጉዳዩ ለማሰብ ጊዜ የሚፈልግ ከሆነስ፦ ብዙ ሳትቆይ በድጋሚ አግኝተህ ለማነጋገር ጥረት አድርግ። በዚህ ጊዜ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ይዘህ መሄድ አትርሳ። በሽፋኑ ውስጠኛ ገጽ ላይ የሚገኘውን የአርዕስት ማውጫ አሳየውና ይበልጥ የሳበውን ርዕሰ ጉዳይ እንዲመርጥ አድርገው። ከዚያም የመረጠውን ትምህርት ግለጽና በዚያ ላይ ውይይት ጀምር።

      10 መጽሔት ያበረከትክላቸውን ሰዎች ተከታትሎ መርዳት:- ትራ​ክቱን ከመጽሔት ጋር አበርክተኸው ከነበረ ተመልሰህ ስትሄድ እንደዚህ ለማለት ትችላለህ:- “ባለፈው ስንገናኝ አንድ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት ሰጥቼዎት ነበር። የመጽሔቱ ሙሉ ስም የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ እንደሚል ምናልባት ሳያስተውሉ አይቀሩም። ዛሬ ይህ ምን ዓይነት መንግሥት እንደሆነና ለእርስዎና ለቤተሰብዎ ምን ትርጉም እንዳለው ባወያይዎት ደስ ይለኛል።” ከዚያም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ትምህርት 6 ግለጥና የቤቱ ባለቤት ጊዜ እስከፈቀደለት ድረስ ከአንቀጽ አንድ በመጀመር አወያየው። ከዚያም በሌላ ጊዜ ተመልሰህ ትምህርቱን ለመጨረስ ቀጠሮ ያዝ።

      11 በቂ ትራክት ያዝ:- የአገልግሎት የበላይ ተመልካቹና በሥነ ጽሑፍ ክፍል የሚሠሩት ወንድሞች ጉባኤው ምንጊዜም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ማወቅ የተባለው ትራክት በቂ አቅርቦት እንዲኖረው ያደርጋሉ። ትራክቱን በቀላሉ ልታገኘው በምትችልበት ስፍራ ማለትም በኪስህ ወይም በቦርሳህ ውስጥ፣ በመኪናህ ውስጥ፣ በሥራ ቦታ፣ በትምህርት ቤት እንዲሁም በቤትህ ውስጥ በመግቢያው አካባቢ አስቀምጠው። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ልታወያየው የምትችለው ሰው ሲያጋጥምህ እንድትጠቀምበት በአገልግሎት ቦርሳህም ያዝ።

      12 ይሖዋ ጥረታችንን ይባርከው:- እውነትን ለሌሎች ማስተማር ሁሉም ክርስቲያኖች ሊኖራቸው የሚገባ ግብ ነው። (ማቴ. 28:19, 20) አሁን የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አለህ? ካለህ በሳምንቱ ፕሮግራምህ ውስጥ ተጨማሪ ጥናት የምትመራበት ጊዜ ማግኘት ትችላለህ? የቤት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ከሌለህ እንዲኖርህ እንደምትመኝ የተረጋገጠ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት እንዲባርክልህ ወደ ይሖዋ ጸልይ። ከዚያም ከጸሎትህ ጋር የሚስማማ ነገር አድርግ።​—⁠1 ዮሐ. 5:​14, 15

      13 ጥናቶችን ለማስጀመር የሚረዳ አዲስ መሣሪያ አግኝተናል! ከትራክቱ ይዘት ጋር በሚገባ ተዋወቁ። ሳትቆጥቡ አሰራጩት። ‘መልካምን ለማድረግ በበጎም ሥራ ባለ ጠጎች ለመሆን፣ ለመርዳትና ስለ አምላክ ቃል የተማራችሁትን ለማካፈል የተዘጋጃችሁ እንድትሆኑ’ የሚቻላችሁን ሁሉ አድርጉ።​—1 ጢ⁠ሞ. 6:18

  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎት—2001 | ኅዳር
    • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች

      ◼ በሚከተሉት ጉባኤዎች አዲስ የመንግሥት አዳራሽ ግንባታ ሥራ በቅርቡ ተጠናቋል:- አዋሳ፣ ጊንጪ፣ ጎባ፣ መቱ፣ ሚዛን፣ ሞጆ እና ናዝሬት። በአሁኑ ወቅት ቢያንስ 45 የሚሆኑ ተሠርተው የተጠናቀቁ የመንግሥት አዳራሾች አሉን።

      ◼ ባለፈው ዓመት የሚከተሉት አዳዲስ ጉባኤዎች ተቋቁመዋል:- አዲስ አበባ አስኮ፣ አየለ (ፊንጫ አቅራቢያ)፣ ባኮ፣ በለስቶ (አለታ ወንዶ አቅራቢያ)፣ ጫኖ (አርባ ምንጭ አቅራቢያ)፣ ፍቼ፣ ኢሎ (ወሊሶ አቅራቢያ)፣ ከሚሴ፣ ለኩ (አዋሳ አቅራቢያ)፣ መቂ፣ ኦፋገንዳባ (ሶዶ አቅራቢያ)፣ ሻሸመኔ ደቡብ፣ ጢስአባሊማ (በደሴ እና በወልድያ መካከል) እና ወንዶ ጢቃ (አዋሳ አቅራቢያ)። ይህ የጉባኤዎችን አጠቃላይ ቁጥር ወደ 107 ከፍ ያደርገዋል።

      ◼ በተከታታይ ባደረግናቸው 16 የወረዳ ስብሰባዎች ላይ በድምሩ 8,874 የሚደርስ ከፍተኛ የተሰብሳቢ ቁጥር የተገኘ ሲሆን 79 ተጠማቂዎች ነበሩ። በተጨማሪም 20 የልዩ ስብሰባ ቀኖች የነበሩን ሲሆን 8,819 የሚያህሉ ተሰብሳቢዎች ተገኝተዋል። ከእነዚህ ውስጥ 63 ሰዎች ተጠምቀዋል።

  • በማውጫው ውስጥ ይገኛል
    የመንግሥት አገልግሎት—2001 | ኅዳር
    • በማውጫው ውስጥ ይገኛል

      ምኑ? በአገልግሎት ልትጠቀምባቸው የምትችላቸውን የናሙና አቀራረቦች የያዘ ዝርዝር። የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ጽሑፎች ማውጫ በርካታ መግቢያዎችና አቀራረቦችን በርዕሰ ጉዳይና በጽሑፉ ዓይነት ዘርዝሮ ይዟል። በአገልግሎት ላይ ለሚሰነዘሩ የተቃውሞ ሐሳቦች ምን ብለን እንደምንመልስ ጭምር እርዳታ ልናገኝበት እንችላለን። ከዚህ በታች ለመስክ አገልግሎት የሚሆኑ ግሩም ሐሳቦች የሚገኙባቸው ዋና ዋና ርዕሶችና ገባ ብለው የተጻፉ ንዑስ ርዕሶች ቀርበዋል።

      መግቢያዎች

      በርዕሰ ጉዳይ

      የተቃውሞ ሐሳቦች

      የተለመዱ የተቃውሞ ሐሳቦች

      አቀራረቦች

      በጽሑፉ ዓይነት

      በርዕሰ ጉዳይ

      ተመላልሶ መጠይቆች

      በጽሑፉ ዓይነት

      በርዕሰ ጉዳይ

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ