የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን እውነት አስታውቁ
    የመንግሥት አገልግሎት—2002 | ኅዳር
    • ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን እውነት አስታውቁ

      1 ቅቡዓን ክርስቲያኖች የሌሎች በጎች ክፍል በሆኑት አጋሮቻቸው እየታገዙ ‘ስለ ኢየሱስ ይመሠክራሉ’። (ራእይ 12:17) መዳን የሚገኘው በእርሱ በኩል ብቻ ስለሆነ ይህ ተልዕኮ ትልቁን ቦታ የሚይዝ ነው።​—⁠ዮሐ. 17:3፤ ሥራ 4:12

      2 ‘መንገድ፣ እውነትና ሕይወት’:- ኢየሱስ “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ” በማለት ተናግሯል። “በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐ. 14:6) ወደ አምላክ በጸሎት መቅረብና ከእርሱ ጋር ጥሩ ዝምድና መመሥረት የምንችለው “መንገድ” በሆነው በኢየሱስ በኩል ብቻ ነው። (ዮሐ. 15:16) በዕብራይስጥ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ የሰፈሩት ትንቢቶችና ጥላዎች ፍጻሜያቸውን ያገኙት በእርሱ ላይ በመሆኑ ኢየሱስ “እውነት” ነው። (ዮሐ. 1:17፤ ቆላ. 2:16, 17) እንዲያውም ትንቢት የሚነገርበት ዋነኛ ዓላማ ኢየሱስ የአምላክን ዓላማ በማስፈጸም ረገድ በሚጫወተው ወሳኝ ሚና ላይ የእውቀት ብርሃን ለመፈንጠቅ ነው። (ራእይ 19:10) በተጨማሪም ኢየሱስ “ሕይወት” ነው። የዘላለምን ሕይወት ስጦታ ለማግኘት ሁሉም ሰው በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ማመን አለበት።​—⁠ዮሐ. 3:16, 36፤ ዕብ. 2:9

      3 የጉባኤ ራስና በመግዛት ላይ የሚገኝ ንጉሥ:- በተጨማሪም ይሖዋ ለልጁ ከፍተኛ የአስተዳደር ሥልጣን እንደሰጠው ሰዎች አምነው መቀበል አለባቸው። ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ ተሹሟል። “የአሕዛብ መታዘዝም ለእርሱ ይሆናል።” (ዘፍ. 49:10) ከዚህም በተጨማሪ ይሖዋ የጉባኤው ራስ አድርጎ ሾሞታል። (ኤፌ. 1:22, 23) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን ኢየሱስ ጉባኤውን እንዴት እንደሚመራና መንፈሳዊ ‘ምግብ በጊዜው’ ለማቅረብ ‘ታማኝና ልባም ባሪያን’ እንዴት እንደሚጠቀም እንዲገነዘቡ መርዳት ይኖርብናል።​—⁠ማቴ. 24:45-47

      4 ሩኅሩኅ ሊቀ ካህናት:- ኢየሱስ ሰው ሆኖ መከራና ሥቃይን ስለቀመሰ ‘ፈተና የሚደርስባቸውን ሊረዳቸው ይችላል።’ (ዕብ. 2:17, 18) ፍጽምና የጎደላቸው የሰው ዘሮች ኢየሱስ ድክመታቸውን ተመልክቶ እንደሚራራላቸውና በደግነት እንደሚማልድላቸው ማወቃቸው ምንኛ ያስደስታቸዋል! (ሮሜ 8:34) በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕትና ሊቀ ካህናት ሆኖ በሚሰጠው አገልግሎት በመጠቀም ‘በሚያስፈልገን ጊዜ እርዳታ ለማግኘት’ ወደ ይሖዋ ‘በእምነት መቅረብ’ እንችላለን።​—⁠ዕብ. 4:15, 16

      5 ሰዎች ስለ ኢየሱስ የሚናገረውን እውነት ማወቃቸው ከእኛ ጋር ሆነው እርሱን እንዲታዘዙና እንዲያገለግሉት የሚያነሳሳቸው እንዲሆን እንመኛለን።​—⁠ዮሐ. 14:15, 21

  • ከጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቻችሁ ጋር ተባበሩ
    የመንግሥት አገልግሎት—2002 | ኅዳር
    • ከጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቻችሁ ጋር ተባበሩ

      1 ሁላችንም ከጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት በርካታ ጥቅሞች እናገኛለን። ባለፈው ወር የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካች ኃላፊነቱን እንዴት እንደሚወጣ ተወያይተን ነበር። ይሁን እንጂ እኛስ ከእርሱ ጋር በመተባበር ራሳችንንም ሆነ ሌሎችን መጥቀም የምንችለው እንዴት ነው?

      2 በየሳምንቱ ተገኙ:- በመጽሐፍ ጥናት ቡድን ውስጥ የሚታቀፉት አስፋፊዎች ቁጥር አነስተኛ ስለሆነ የአንድ ሰው መምጣት ወይም መቅረት የጎላ ልዩነት ያመጣል። ስለዚህ ሁልጊዜ ለመገኘት ግብ አውጡ። የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቹ ስብሰባውን ያለ ችግር መምራት እንዲችል ስለሚረዳው ሰዓት አክባሪ በመሆንም እገዛ ልናበረክት እንችላለን።​—⁠1 ቆ⁠ሮ. 14:40

      3 የሚያንጹ መልሶችን በማካፈል:- ሌላው ተባባሪ መሆናችንን ማሳየት የምንችልበት መንገድ በሚገባ በመዘጋጀትና በስብሰባው ላይ የሚያንጹ ሐሳቦችን በማካፈል ነው። በአንድ ነጥብ ላይ ብቻ የሚያተኩሩ መልሶችን መመለስ አብዛኛውን ጊዜ የተሻለ ከመሆኑም በላይ ሌሎችም እንዲሳተፉ ያበረታታል። በአንቀጹ ውስጥ ያለውን ሐሳብ በሙሉ ለመሸፈን አትሞክሩ። በትምህርቱ ውስጥ የነካችሁ አንድ ነጥብ ካለ ያንን በማካፈል ውይይቱን ሕያው አድርጉ።​—⁠1 ጴ⁠ጥ. 4:10

      4 የመጽሐፍ ጥናት ቡድኑን በንባብ የምትረዳ ከሆነ ይህን ኃላፊነትህን በትጋት ለመወጣት ጥረት አድርግ። ጥርት ያለ ንባብ ጥናቱን ይበልጥ አስደሳች ለማድረግ ይረዳል።—⁠1 ጢ⁠ሞ. 4:13

      5 የቡድን ምሥክርነት:- የመስክ አገልግሎት ስምሪት ስብሰባዎች በአብዛኞቹ የመጽሐፍ ጥናት መሰብሰቢያ ቦታዎች ይደረጋሉ። እነዚህን ዝግጅቶች መደገፋችን የበላይ ተመልካቹ በወንጌላዊነቱ ሥራ በግንባር ቀደምትነት ለመሥራት ለሚያደርገው ጥረት እገዛ ያበረክትለታል። እነዚህን ዝግጅቶች ከወንድሞች ጋር ለመቀራረብና እነርሱን ለማበረታታት እንደሚያስችሉ አጋጣሚዎች አድርገን እንመልከታቸው።

      6 የመስክ አገልግሎት ሪፖርት:- ከበላይ ተመልካቹ ጋር ልንተባበር የምንችልበት ሌላው መንገድ በወሩ መጨረሻ ላይ የመስክ አገልግሎት ሪፖርታችንን ሳንዘገይ በመስጠት ነው። የአገልግሎት ሪፖርታችሁን በቀጥታ ለእርሱ ልትሰጡት ወይም በመንግሥት አዳራሹ ውስጥ ለዚህ ዓላማ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ልትከቱት ትችላላችሁ። የጉባኤው ጸሐፊ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቾች የሰበሰቡትን የመስክ አገልግሎት ሪፖርት ለመቀበል ይህን ሣጥን ሊጠቀምበት ይችላል።

      7 ለጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የበላይ ተመልካቻችሁ የምታደርጉትን እገዛ በእጅጉ እናደንቃለን። ከሁሉም በላይ ይሖዋ ‘ከመንፈሳችሁ ጋር እንደሚሆን’ እርግጠኛ ልትሆኑ ትችላላችሁ።​—⁠ፊልጵ. 4:23

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ