የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አንተስ በዚያ ትገኝ ይሆን?
    የመንግሥት አገልግሎት—2000 | መስከረም
    • አንተስ በዚያ ትገኝ ይሆን?

      1 አንድ የቆየ የይሖዋ ምሥክር “የአውራጃ ስብሰባው የመጀመሪያ ቀን ስብሰባ ካመለጣችሁ በጣም ብዙ ቁምነገር አመለጣችሁ ማለት ነው!” ብሎ ነበር። እንዲህ የተሰማው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ይህ ቀን የይሖዋ ድርጅት ያዘጋጀልን ታላቅ መንፈሳዊ ግብዣ የሚጀምርበት ቀን በመሆኑ ነው። (ኢሳ. 25:​6) ከመክፈቻው አንስቶ በዚያ መገኘታችን “ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ” በማለት ስሜቱን ከገለጸው መዝሙራዊ ጋር እንደምንስማማ ያሳያል።​—⁠መዝ. 122:​1

      2 ባለፈው ዓመት በአንዳንድ “የአምላክ ትንቢታዊ ቃል” የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ የዓርብ ቀን ተሰብሳቢዎች ቁጥር ከቅዳሜውና ከእሑዱ ጋር ሲወዳደር አነስተኛ ነበር። ይህ ማለት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወንድሞቻችን ስለ ትንቢታዊው ቃል የተነገረው በጣም አስፈላጊ እውቀት አምልጧቸዋል ማለት ነው። እንዲሁም ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በመቀራረብ የሚገኘውን ደስታ አጥተዋል።

      3 ሰብዓዊ ሥራ እንዲያስቀራችሁ አትፍቀዱ:- አንዳንዶች በዓርቡ ስብሰባ ላይ የማይገኙበት ምክንያት ሥራዬን አደጋ ላይ እጥላለሁ የሚል ስጋት ስለሚያድርባቸው ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ብዙ የይሖዋ ምሥክሮች ቀደም ብለው አሠሪያቸውን ፈቃድ ከጠየቁ አሠሪዎቻቸው ሳያንገራግሩ እንደሚተባበሯቸው ተረድተውታል። አንድ አሠሪ፣ አንዲት አቅኚ በሁሉም የጉባኤ ስብሰባዎች እንዲሁም በወረዳና በልዩ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ያላት ቁርጥ አቋም በጣም ስላስደነቀው የአውራጃ ስብሰባ ሲደረግ ከእርሷ ጋር ሙሉ ቀን ተካፍሏል!

      4 አሠሪዬ ፈቃድ አይሰጠኝ ይሆናል ብላችሁ ከመጠየቅ ማመንታት ወይም ከአውራጃ ስብሰባው አንዱ ቀን ቢያመልጠኝ ምንም አይደለም ብላችሁ መደምደም አይገባችሁም። በአውራጃ ስብሰባው ላይ መገኘታችሁ በጣም አስፈላጊ የሆነ የአምልኮታችሁ ክፍል የሆነበትን ምክንያት በዘዴ ከቅዱሳን ጽሑፎች ለማሳየት ተዘጋጁ። (ዕብ. 10:​24, 25) ከዚያም ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ቅድሚያ የምትሰጡ ከሆነ ይሖዋ ሥጋዊ ፍላጎቶቻችሁን ሁሉ እንደሚያሟላ በገባው ቃል ላይ ሙሉ በሙሉ ትምክህት ይኑ​ራችሁ።​—⁠ማቴ. 6:​33፤ ዕብ. 13:​5, 6

      5 ቁልፉ ‘ይበልጥ አስፈላጊ ለሆነው ነገር’ አድናቆት ማዳበር ነው። (ፊልጵ. 1:​10, 11፤ መዝ. 27:​4) እንዲህ ማድረጉ በጣም አስፈላጊ ከሆነው የይሖዋ ዝግጅት ሙሉ ጥቅም ለማግኘት እቅድ እንድናወጣ ይገፋፋናል። አሁኑኑ ቁርጥ ያለ እቅድ ማውጣት ጀምር፤ እንዲሁም ሦስቱንም ቀን በዚያ ለመገኘት ቁርጥ ውሳኔ አድርግ!

  • ማስታወቂያዎች
    የመንግሥት አገልግሎት—2000 | መስከረም
    • ማስታወቂያዎች

      ◼ የሚበረከቱ ጽሑፎች መስከረም:- በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ። ጥቅምት:- የመጠበቂያ ግንብ እና የንቁ! መጽሔት ነጠላ ቅጂዎች። ተመላልሶ መጠየቅ የምታደርጉላቸው ሰዎች ፍላጎት ካሳዩ ኮንትራት ማስገባት ይቻላል። ከወሩ መገባደጃ ጀምሮ የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ማሰራጨት ይጀመራል። ኅዳር:- የመንግሥት ዜና ቁጥር 36 ስርጭት ይቀጥላል። ጉባኤዎች በክልላቸው ውስጥ ለሚገኝ ለእያንዳንዱ የቤት ባለቤት የመንግሥት ዜና ቁጥር 36ን አበርክተው ከጨረሱ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው የተባለውን ብሮሹር ወይም እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ማበርከት ይችላሉ። የምናነጋግራቸው ሰዎች እነዚህ ጽሑፎች ካሏቸው ለዘላለም መኖር ወይም ፍጥረት የተባሉትን መጻሕፍት ማበርከት ይቻላል። ታኅሣሥ:- ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት የተባለውን መጽሐፍ ወይም በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ የተባለውን መጽሐፍና እስከዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ሰው።

      ◼ ሽማግሌዎች የመመለስ ዝንባሌ ያላቸውን የተወገዱ ወይም ራሳቸውን ያገለሉ ግለሰቦችን በተመለከተ በሚያዝያ 15, 1991 መጠበቂያ ግንብ ከገጽ 21-23 ላይ የተሰጡትን መመሪያዎች እንዲሠሩባቸው ልናስታውሳቸው እንወዳለን።

      ◼ ማኅበሩ አስፋፊዎች በግል የሚልኩትን የጽሑፍ ትእዛዝ አያስተናግድም። የጉባኤው ወርኃዊ የጽሑፍ ትእዛዝ ወደ ማኅበሩ ከመላኩ በፊት በግል የሚታዘዙ ነገሮች ማግኘት የሚፈልጉ ሁሉ ለጽሑፍ አገልጋዩ ማስታወቅ እንዲችሉ ሰብሳቢ የበላይ ተመልካቹ በየወሩ ማስታወቂያ እንዲነገር ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል። በልዩ ትእዛዝ የሚገኙት የትኞቹ ጽሑፎች እንደሆኑ እባካችሁ አስታውሱ።

  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎት—2000 | መስከረም
    • የጥያቄ ሣጥን

      ◼ አንድ ተናጋሪ አድማጮቹ ጥቅስ እንዲያወጡ በሚጋብዝበት ጊዜ ጥቅሱን አውጥቶ መከታተል ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

      አድማጮች አውጥተው እንዲከታተሉ የሚጋበዙትን ጥቅስ ብዛት የሚወስነው የንግግሩ ርዕሰ ጉዳይ እንዲሁም ንግግሩ የተወሰነ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ቁጥር በቁጥር የሚያብራራ መሆን አለመሆኑ ነው።

      ጥቅስ የሚነበብበት አንደኛው ምክንያት እየተነገረ ያለው ነገር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ለመስጠት እንደሆነ ልብ ማለት ያስፈልጋል። (ሥራ 17:​11) ሌላው ዓላማ የአድማጮች እምነት ይገነባ ዘንድ ለትምህርቱ ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃዎችን ማቅረብ ነው። አንድ ቁልፍ ጥቅስ በሚነበብበት ጊዜ በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል መከታተል ትምህርቱ እንዳይረሳ ያደርጋል። ጥቅሶች ሲነበቡ አውጥቶ ከመከታተል በተጨማሪ ማስታወሻ መያዝና ሐሳቦቹ በቅደም ተከተል ሲቀመጡ በትኩረት መከታተል ጥቅም አለው።

      ማኅበሩ የሚያዘጋጀው የንግግር አስተዋጽዖ አንድን ርዕሰ ጉዳይ የሚያዳብሩ ብዙ ጥቅሶች ሊኖሩት ቢችሉም ተናጋሪው ንግግሩን በሚዘጋጅበት ጊዜ እንዲረዱት ታስበው የሚቀርቡ ናቸው። ንግግር ስለሚሰጥበት ርዕሰ ጉዳይ የተሟላ ግንዛቤ እንዲኖረው ወይም ተናጋሪው ከበስተ ጀርባ ያሉት ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች ቁልጭ ብለው እንዲታዩትና ርዕሱ እንዴት እንደተብራራ እንዲያስተውል ይረዱታል። ንግግሩን ለማብራራት የትኞቹን ጥቅሶች እንደሚጠቀም የሚወስነው ተናጋሪው ሲሆን የመረጣቸውን ጥቅሶች ሲያነብና ሲያብራራ አውጥተው እንዲከታተሉት አድማጮቹን ይጋብዛል። ተጨማሪ መረጃ ለመስጠት ሲባል የገቡትን ጥቅሶች በቃሉ መናገር ወይም በራሱ አባባል መግለጽ ይችላል። ሆኖም በዚህ ጊዜ አድማጮች የግድ አውጥተው መከታተል አለባቸው ማለት አይሆንም።

      ተናጋሪው የመረጣቸውን ጥቅሶች በኮምፒዩተር አትሞ ወይም በእጅ ጽፎ ከወረቀት ላይ ከማንበብ ይልቅ በቀጥታ ከመጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ይኖርበታል። አድማጮች ጥቅስ አውጥተው እንዲከታተሉት በሚጋብዝበት ጊዜ ጥቅሱ የሚገኝበትን መጽሐፍ፣ ምዕራፍና ቁጥር (ቁጥሮች) በግልጽ መናገር አለበት። ጥቅሱ የሚነበብበትን ዓላማ ግልጽ ለማድረግ የሚረዳ ጥያቄ በማንሳት ወይም አጠር ያለ ሐሳብ በመስጠት አድማጮች ጥቅሱን ለማውጣት ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ ይችላል። ጥቅሱን ደግሞ መናገሩ አድማጮች ቦታውን ቶሎ እንዲያገኙ ይረዳቸዋል። ይሁን እንጂ አድማጮች የሚይዙት የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ሊለያይ ስለሚችል ገጹን መናገር አስፈላጊ አይደለም። ጥቅስ እንድናወጣ ስንጋበዝ አውጥተን መከታተላችን በንግግሩ አማካኝነት የሚብራራው የአምላክ ቃል ካለው ኃይል እንድንጠቀም ይረዳናል።​—⁠ዕብ. 4:​12

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ