የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ ቀን ቀርቧል
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ግንቦት
    • የይሖዋ ቀን ቀርቧል

      1 ክርስቲያኖች አሁን ያለውን ሥርዓት አጥፍቶ ጽድቅ የሰፈነበት አዲስ ምድር የሚያመጣውን የይሖዋን ቀን መምጣት በናፍቆት ይጠባበቃሉ። (2 ጴ⁠ጥ. 3:​12, 13 የግርጌ ማስታወሻ) የይሖዋ ቀን የሚመጣበትን ጊዜ ስለማናውቅ ነቅተን መጠባበቅና ሌሎችም እንዲህ እንዲያደርጉ መርዳት ይኖርብናል። (ሕዝ. 33:​7-9፤ ማቴ. 24:​42-44) በአምላክ ትንቢታዊ ቃል ላይ ማሰላሰላችን “ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ” እንደሆነ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል።​—⁠ሶፎ. 1:​14

      2 የዓለም ኃያላን መንግሥታት ቅደም ተከተል:- ሐዋርያው ዮሐንስ በራእይ 17:​9-11 ላይ የጠቀሳቸው “ሰባት ነገሥታት” በተከታታይ የሚነሱ ሰባት የዓለም ኃያላን መንግሥታትን ያመለክታሉ። ዮሐንስ ቀጥሎ የገለጸው “ስምንተኛው ንጉሥ” የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን የሚያመለክት ነው። ከአሁን በኋላ ሌሎች የዓለም ኃያላን መንግሥታት እንደሚመጡ መጠበቅ ይኖርብናል? በፍጹም፣ ምክንያቱም ትንቢቱ ይህ ስምንተኛ ንጉሥ ‘ወደ ጥፋቱ እንደሚሄድ’ የገለጸ ሲሆን ከስምንተኛው በኋላ የሚነሳ ሌላ ምድራዊ ንጉሥ አልተጠቀሰም። ታዲያ ይህ ትንቢት በጊዜ ሂደት ውስጥ የት ቦታ ላይ እንዳለን ለማስተዋል አስችሎሃል?

      3 ዳንኤል 2:​31-45 ስለ ይሖዋ ቀን መምጣት ግልጽ ግንዛቤ እንዲኖረን ይረዳናል። በትንቢቱ ውስጥ የተገለጸው ናቡከደነፆር በሕልሙ የተመለከተው ግዙፍ ምስል በተለያዩ ጊዜያት የተፈራረቁትን የዓለም ኃያላን መንግሥታት ያመለክታል። በምስሉ የተወከሉት የዓለም ኃያላን መንግሥታት በሙሉ አልፈዋል። በዛሬው ጊዜ የሚገዛው ኃያል መንግሥት ማነው? በሕልም በታየው ምስል ላይ በእግር የተመሰለው መንግሥት ነው። ከዚህ በኋላ ምን እንደሚከሰት ትንቢቱ በግልጽ አስቀምጦታል። የሰው ልጅ አገዛዝ ሙሉ በሙሉ ተወግዶ ‘ፈጽሞ ለማይፈርሰው መንግሥት’ ቦታውን ይለቅቃል። ይህ ትንቢት የይሖዋ ቀን ምን ያህል እንደቀረበ የሚያሳየው እንዴት እንደሆነ መገንዘብ ችለሃል?

      4 ተጨማሪ ማስረጃ:- የይሖዋ ቀን መቅረቡን የሚያመለክተውን ተጨማሪ ማስረጃ እኛ ራሳችን የዓይን ምሥክሮች ሆነን አይተነዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ “በመጨረሻው ዘመን” ስለሚኖረው ማኅበረሰብ ባሕርያት የተናገረው ትንቢት ፍጻሜውን እንዳገኘ በግልጽ እየተመለከትን ነው። (2 ጢ⁠ሞ. 3:​1-5) እኛም መጨረሻው ከመምጣቱ በፊት በዓለም ዙሪያ በሚከናወነው የስብከት ሥራ ላይ እየተካፈልን ነው። (ማቴ. 24:​14) “እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ክብርም ስጡት፤ ምክንያቱም የፍርዱ ሰዓት ደርሶአል” እያለ የሚያውጀውን መልአክ በመምሰል አገልግሎታችንን በጥድፊያ ስሜት እናከናውን።​—⁠ራእይ 14:​6, 7

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ግንቦት
    • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት

      ክፍል 9፦ ጥናቶቻችን መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር እንዲችሉ ማሠልጠን

      1 እንድርያስና ፊልጶስ፣ እንደሚመጣ ተስፋ የተደረገው መሲሕ ኢየሱስ መሆኑን ሲያውቁ ይህን አስደሳች ዜና ለሌሎች ከመንገር ወደኋላ አላሉም። (ዮሐ. 1:​40-45) ዛሬም በተመሳሳይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን በተማሩት ነገር ላይ እምነት ማሳደር ሲጀምሩ ያወቁትን ለሌሎች ለመናገር ይገፋፋሉ። (2 ቆ⁠ሮ. 4:​13) መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲመሠክሩ እንዴት ማበረታታት እንችላለን? በዚህ ረገድ ውጤታማ እንዲሆኑ ልናሠለጥናቸው የምንችለውስ እንዴት ነው?

      2 ጥናትህ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማረውን ለሌሎች መናገር ጀምሮ እንደሆነ ልትጠይቀው ትችላለህ። ምናልባት በሚያጠናበት ወቅት ጓደኞቹንና የቤተሰቡን አባላት በጥናቱ ላይ እንዲገኙ ሊጋብዛቸው ይችላል። ከሥራ ባልደረቦቹ፣ አብረውት ከሚማሩት ልጆች ወይም ከሌሎች ወዳጆቹ መካከል ለምሥራቹ ፍላጎት ያሳዩ እንዳሉ ጠይቀው። በዚህ መንገድ መመሥከር ሊጀምር ይችላል። ስለ ይሖዋ አምላክና ስለ ዓላማዎቹ ለሌሎች በሚናገርበት ጊዜ አስተዋይ መሆን እንዳለበት እንዲሁም አክብሮትና ደግነት ማሳየቱ አስፈላጊ መሆኑን እንዲገነዘብ እርዳው።​—⁠ቈላ. 4:​6፤ 2 ጢ⁠ሞ. 2:​24, 25

      3 ስለ እምነታቸው ለሌሎች መናገር:- የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ስለ እምነታቸው ለሌሎች በሚናገሩበት ጊዜ በአምላክ ቃል እንዲጠቀሙ ማሠልጠኑ በጣም አስፈላጊ ነው። በጥናቱ ወቅት በአንዳንድ ነጥቦች ላይ ጥናትህን እንዲህ እያልክ ጠይቀው:- “ይህንን እውነት በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመህ ለቤተሰቦችህ እንዴት ማስረዳት ትችላለህ?” ወይም “ስለዚህ ጉዳይ ለአንድ ጓደኛህ ለማስረዳት የትኛውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ትጠቀማለህ?” የሚሰጠውን መልስ ልብ ብለህ አዳምጠው፤ ከዚያም ለሚናገረው ነገር የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ እንዴት ማቅረብ እንደሚችል አሳየው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ