የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የስብከቱ ሥራ እንድንጸና ይረዳናል
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ሰኔ
    • የስብከቱ ሥራ እንድንጸና ይረዳናል

      1 የአምላክ ቃል “በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት [እንድንሮጥ]” ይመክረናል። (ዕብ. 12:​1) አንድ ሯጭ ውድድሩን በድል ለመጨረስ ጽናት እንደሚያስፈልገው ሁሉ እኛም የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ጽናት ያስፈልገናል። (ዕብ. 10:​36) በታማኝነት እስከ መጨረሻው ለመጽናት ክርስቲያናዊ አገልግሎታችን እንዴት ሊረዳን ይችላል?​—⁠ማቴ. 24:​13

      2 በመንፈሳዊ ያጠነክረናል:- በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሰፍሮ የሚገኘውን ጽድቅ ስለሰፈነበት አዲስ ዓለም የሚገልጽ ግሩም ምሥራች ማወጃችን ተስፋችን ብሩህ ሆኖ እንዲቀጥል ይረዳናል። (1 ተ⁠ሰ. 5:​8) አዘውትረን በመስክ አገልግሎት ስንካፈል ከመጽሐፍ ቅዱስ የተማርነውን እውነት ለሌሎች የማሳወቅ አጋጣሚ እናገኛለን። ስንሰብክ ስለ እምነታችን ማስረጃ ለማቅረብ አጋጣሚ የምናገኝ ሲሆን ይህም በመንፈሳዊ ጠንካሮች እንድንሆን ይረዳናል።

      3 ሌሎችን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተማር እኛ ራሳችን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በሚገባ እንዲገባን ያስፈልጋል። ይህም በትምህርቱ ላይ ምርምር ማድረግና ማሰላሰልን ይጠይቃል። የምናደርገው ከፍተኛ ጥረት እውቀታችን ጥልቀት እንዲኖረው፣ እምነታችን እንዲጠነክርና መንፈሳዊነታችን እንዲታደስ ያደርግልናል። (ምሳሌ 2:​3-5) በዚህ መንገድ ሌሎችን ለመርዳት በምንጥርበት ጊዜ ራሳችንን እናጠናክራለን።​—⁠1 ጢ⁠ሞ. 4:​15, 16

      4 ‘የእግዚአብሔር ሙሉ የጦር ዕቃ’ ዋነኛ ክፍል በሆነው በስብከቱ ሥራ በቅንዓት መሳተፋችን ዲያብሎስንና አጋንንቱን ለመቋቋም ያስችለናል። (ኤፌ. 6:​10-13, 15) በቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች ራሳችንን ማስጠመዳችን አእምሯችን በሚያንጹ ነገሮች ላይ እንዲያተኩርና በሰይጣን ዓለም እንዳንበከል ይረዳናል። (ቈላ. 3:​2) ሌሎችን ስለ ይሖዋ መንገዶች በምናስተምርበት ጊዜ እኛ ራሳችን ቅዱስ ምግባር ማሳየት እንዳለብን ዘወትር እናስታውሳለን።​—⁠1 ጴ⁠ጥ. 2:​12

      5 ከአምላክ ኃይል እናገኛለን:- በመጨረሻም በወንጌላዊነት ሥራ መሳተፍ በይሖዋ ላይ መመካትን ያስተምረናል። (2 ቆ⁠ሮ. 4:​1, 7) ይህ እንዴት ያለ በረከት ነው! እንዲህ ዓይነት እምነት ማዳበራችን አገልግሎታችንን እንድንፈጽም ብቻ ሳይሆን በሕይወታችን ውስጥ ምንም ዓይነት ሁኔታዎች ቢያጋጥሙን እንድንጸና ያስችለናል። (ፊልጵ. 4:​11-13) እውነት ነው፣ ሙሉ በሙሉ በይሖዋ ላይ መደገፍን መማር ለጽናት ዋነኛው ቁልፍ ነው። (መዝ. 55:​22) የስብከቱ ሥራ እንድንጸና በብዙ መንገዶች ይረዳናል።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎት—2005 | ሰኔ
    • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶቻችን እድገት እንዲያደርጉ መርዳት

      ክፍል 10፦ ጥናቶቻችን ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው አገልግሎት እንዲካፈሉ ማሠልጠን

      1 አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ያልተጠመቀ አስፋፊ ለመሆን ብቃቱን እንዳሟላ ሽማግሌዎች ሲወስኑ ግለሰቡ ከጉባኤው ጋር ሆኖ በስብከቱ ሥራ ሊሳተፍ ይችላል። (የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ የተባለውን መጽሐፍ ገጽ 79-81 ተመልከት።) ጥናቱን ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ምሥክርነት እንዲካፈል እንዴት ልንረዳው እንችላለን?

      2 አብሮ መዘጋጀት:- ጥሩ ዝግጅት በጣም አስፈላጊ ነው። ለጥናቱ የናሙና አቀራረቦችን ከመንግሥት አገልግሎታችን እና ከማመራመር መጽሐፍ ሊያገኝ እንደሚችል ካሳየኸው በኋላ ለክልሉ ተስማሚ የሆነ ቀለል ያለ መግቢያ እንዲመርጥ እርዳው። ገና ከጅምሩ አገልግሎቱን ሲያከናውን በመጽሐፍ ቅዱስ እንዲጠቀም አበረታታው።​—⁠2 ጢ⁠ሞ. 4:​2

      3 አብሮ መለማመድ ለአዲስ አስፋፊ በጣም ጠቃሚ ነው። ጥናቱ መግቢያውን እየተለማመደ እያለ በክልሉ ውስጥ ሰዎች በአብዛኛው ለሚሰነዝሯቸው ሐሳቦች እንዴት በጥበብ መልስ መስጠት እንደሚችል አሳየው። (ቈላ. 4:​6) አንድ ክርስቲያን የቤቱ ባለቤት ለሚያነሳው ጥያቄ ሁሉ መልስ ማወቅ እንደማያስፈልገው ንገረው። ብዙውን ጊዜ እንደነዚህ የመሰሉ ጥያቄዎች ሲነሱ ምርምር አድርጎ በሌላ ጊዜ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ሐሳብ ማቅረቡ የተሻለ ይሆናል።​—⁠ምሳሌ 15:​28

      4 አብሮ ማገልገል:- ጥናቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቤት ወደ ቤት ሲያገለግል አብራችሁ ሆናችሁ የተዘጋጃችሁትን መግቢያ ስትጠቀምበት እንዲመለከት አድርግ። ከዚያም በውይይቱ ላይ ሐሳብ እንዲሰጥ አድርግ። አንዳንድ ጊዜ አዲሱ አስፋፊ አንድ ጥቅስ እንዲያነብና በጥቅሱ ላይ ሐሳብ እንዲሰጥ ብቻ ማድረጉ የተሻለ ሊሆን ይችላል። የጥናትህን ባሕርይና ችሎታ ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብሃል። (ፊልጵ. 4:​5 NW ) ደረጃ በደረጃ በስብከቱ ሥራ የተለያዩ ዘርፎች እንዲካፈል ስታሰለጥነው ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ አመስግነው።

      5 አዲሱ አስፋፊ ከተቻለ በየሳምንቱ በአገልግሎት የሚሳተፍበት ቋሚ ፕሮግራም እንዲኖረው መርዳት አስፈላጊ ነው። (ፊልጵ. 3:​16) አብራችሁ የምታገለግሉበት የተወሰነ ጊዜ መመደብ እንዲሁም ከሌሎች ቀናተኛ የይሖዋ ምሥክሮች ጋር አብሮ እንዲሠራ ማበረታታት ያስፈልጋል። የእነርሱን ፈለግ መከተሉና አብሯቸው ማገልገሉ ከቤት ወደ ቤት በሚደረገው ምሥክርነት ደስታ እንዲያገኝና ችሎታውን እንዲያሻሽል ይረዳዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ