-
የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎችየመንግሥት አገልግሎት—1999 | ግንቦት
-
-
የግንቦት የአገልግሎት ስብሰባዎች
ግንቦት 3 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 8 (21)
13 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። ከመንግሥት አገልግሎታችን የተመረጡ ማስታወቂያዎች።
17 ደቂቃ፦ “ራሳቸውን መጥቀም እንዲችሉ አስተምሯቸው።” አንድ ደቂቃ በማይሞላ ጊዜ ውስጥ የመግቢያ ሐሳቦች ከተናገርክ በኋላ በጥያቄና መልስ አቅርበው። በእውቀት መጽሐፍ 13ኛ ምዕራፍ ተጠቅመህ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በማጥናት፣ በመገንዘብና በተግባር በማዋል ሰዎች እንዴት ተግባራዊ ጥቅም እንዳገኙ ግለጽ።
15 ደቂቃ፦ “አስቀድማችሁ ዕቅድ አውጡ!” ከፊታችን ባሉት ወሮች በአካባቢው ሊደረጉ የታቀዱትን ቲኦክራሲያዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ በመከለስ በንግግር ይቀርባል። ሁሉም እነዚህን ቀኖች ቀን መቁጠሪያቸው ላይ ምልክት እንዲያደርጉባቸውና ሌሎች ነገሮች ጣልቃ እንዲገቡባቸው እንዳይፈቅዱ አበረታታ።
መዝሙር 74 (168) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 10 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 98 (220)
8 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የሒሳብ ሪፖርት።
25 ደቂቃ፦ “አገልግሎትህን ማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች።” ከአድማጮች የሚነሱትን ጥያቄዎች መሠረት አድርገው ሁለት ሽማግሌዎች ትምህርቱን በውይይት ያቀርቡታል። አንድ በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ የጉባኤ አስፋፊ፣ አንድ ባልና ሚስት እንዲሁም ጡረታ የወጣ አንድ ወንድም አገልግሎታቸውን ማስፋት የሚችሉበትን መንገድ በተመለከተ ጥያቄ ያቀርባሉ። በዚህ ርዕስና አገልግሎታችን ከተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 9 ከገጽ 116-18 ላይ “ለወደፊቱ ጊዜ ያወጣሃቸው መንፈሳዊ ግቦችህ ምንድን ናቸው?” በሚል ጥያቄ ከሰፈረው ነጥብ ተግባራዊ ሐሳቦች ይቀርባሉ። አስፋፊዎቹ ማኅበሩ ከፊታችን ባሉት ጊዜያት የአገልግሎት እንቅስቃሴያችንን እንዴት ማስፋት እንደምንችል የሚጠቁም ጠቃሚ ትምህርት በማቅረቡ ያላቸውን አድናቆት ይገልጻሉ።
12 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
መዝሙር 7 (19) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 17 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 10 (27)
7 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች።
18 ደቂቃ፦ የጥያቄ ሣጥን። በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ነጥቦቹን በመከለስ ደምድም።
20 ደቂቃ፦ በጎችንና ፍየሎችን በመለያየት ሥራ እየተካፈልን ነውን? በሐምሌ 1, 1997 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 30-1 ላይ ተመሥርቶ በአገልግሎት የበላይ ተመልካቹ ቀስቃሽ በሆነ መንገድ የሚቀርብ ንግግር።
መዝሙር 11 (29) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
ግንቦት 24 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 22 (47)
12 ደቂቃ፦ የጉባኤ ማስታወቂያዎች። የአገልግሎት ክልሎችን ለመሸፈን ባደረግነው ልዩ ዘመቻ ጉባኤው ያከናወነውን ሥራ ባጭሩ ጥቀስና ፍላጎት ያሳዩ ሰዎችን ተከታትሎ የመርዳትን አስፈላጊነት አጉላ። ሁሉም የመስክ አገልግሎት ሪፖርታቸውን እሁድ ዕለት ወይም በቀጣዩ ሳምንት መጀመሪያ ላይ እንዲመልሱ አሳስባቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ በቀጣዩ ሳምንት ማበርከት የምንጀምረውን ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ በማበርከት ረገድ መልካም ጅምር እንዲያሳዩ አበረታታ።
18 ደቂቃ፦ አካላዊ ንጽሕና ይሖዋን ያስከብራል። በአገልግሎታችን መጽሐፍ ገጽ 130-132 ላይ ተመሥርቶ በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። እባክህ፣ ልጆቻችንም ጭምር ወደ ስብሰባዎች ሲመጡ መልበስ ያለባቸው ጂንስና ሌላ የቤት ልብስ ሳይሆን ንጹሕ፣ ተገቢና ሥርዓት ያለው ልብስ መሆን እንዳለበት በግልጽ ተናገር። ቤቴልን ለመጎብኘት የሚመጡ ወንድሞች ስብሰባ ሲመጡ እንዲለብሱ የሚጠበቅባቸው ዓይነት ተመሳሳይ የሆነ አለባበስ ሊኖራቸውም እንደሚገባ ሁሉንም አሳስብ። ከመስከረም 22, 1988 ንቁ! (እንግሊዝኛ) ገጽ 8-11 ላይ ተስማሚ የሆኑ ነጥቦችን ጨምረህ አቅርብ። መኖሪያ ቤታችን በአካባቢያችን ከተለመደው በተሻለ ሁኔታ ንጹሕ ሆኖ መታየት እንዳለበት ጎላ አድርገህ ግለጽ። ግድግዳና በሮች (የአጥር ግቢም ሆነ የቤቱ) ላይ ያሉ ቆሻሻዎችን ማጽዳት፤ የቤት ዕቃዎችን ስር፣ ጥግ ጥጉን፣ ክፈፎችን እንዲሁም የበርና የመስኮቶችን አናት፣ የበር እጀታዎችን፣ ማብሪያና ማጥፊያዎችን እንዲሁም ዙሪያቸውን፣ ወዘተ ያለውን አቧራ ማንሳትና መወልወል አስፈላጊ መሆኑን ጥቀስ።
15 ደቂቃ፦ ሃይማኖቴ ምን አለኝ? ሁለት የጉባኤ አገልጋዮች በውይይት ያቀርቡታል። ለእውነት ቀና አመለካከት ያላቸውና የይሖዋ ምሥክሮችን የሚያደንቁ በርካታ ሰዎች ያጋጥሙናል። ሆኖም ከቤተ ክርስቲያናቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ወደኋላ ይጎትታቸዋል። እውነተኛውን ሃይማኖት የያዝነው እኛ ብቻ መሆናችንንና እነርሱ የሚከተሉት አምልኮ ደግሞ ውሸት መሆኑን ማመን ያዳግታቸዋል። ይህም ለመንፈሳዊ እድገታቸው ትልቅ መሰናክል ይፈጥርባቸዋል። ሁለቱ ወንድሞች ሌሎች ሃይማኖቶች መጽሐፍ ቅዱስን እንደማይከተሉ በግልጽ የሚያሳዩትን በማመራመር መጽሐፍ ገጽ 204-5 ላይ የተጠቀሱትን ስድስት ነጥቦች ይከልሳሉ። ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ሃይማኖታዊ ትምህርቶቻቸውን እንዲመረምሩ ለመርዳት በእነዚህ ነጥቦች በዘዴ እንዲጠቀሙ አድማጮችን ያበረታታሉ።
መዝሙር 12 (32) እና የመደምደሚያ ጸሎት።
-
-
የጥያቄ ሣጥንየመንግሥት አገልግሎት—1999 | ግንቦት
-
-
የጥያቄ ሣጥን
◼ የጉባኤ አስፋፊዎች ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የመኖሪያ ቦታ ለመቀየር ሲዘጋጁ መታወስ ያለበት ነገር ምንድን ነው?
ወደ ሌላ ቦታ፣ ከተማ ወይም አገር የሚደረግ ማንኛውም የቦታ ለውጥ ተጨማሪ ሥራ እንዲሁም በአብዛኞቹ ሁኔታዎች የተወሰነ አለመረጋጋት ያስከትላል። በዚህ ዓይነት ሁኔታ ስር ጥሩ ቲኦክራሲያዊ ልማዳችንን በቀላሉ ልናቋርጥ እንችላለን። ስለዚህ ዛሬ ነገ ሳንል በተዛወርንበት አካባቢ ከሚገኙ ወንድሞች ጋር ለመገናኘት የሚያስችል ተገቢ ዝግጅት ለማድረግ ልዩ ትኩረት መስጠት አለብን።
አንድ የጉባኤ አስፋፊም ሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ የቦታ ለውጥ ከማድረጉ በፊት የጉባኤውን ጸሐፊ ማነጋገሩ ጥሩ ነው። ግለሰቡ በሚሄድበት አካባቢ ያለው ጉባኤ አድራሻ ይታወቃል? ሁኔታው እንዲህ ከሆነ የጉባኤው ጸሐፊ ለዚያኛው ጉባኤ ጸሐፊ ደብዳቤ መላኩ ቀላልና የተሻለ አማራጭ ነው። አንድ አስፋፊ የቦታ ለውጥ ካደረገ ከደብዳቤው ጋር የአስፋፊ ካርዱ ተያይዞ መላክ አለበት። አስፋፊው ሁለቱንም የምክር መስጫ ቅጽ ቅጂዎች በእጁ ይዞ የማይሄድ ከሆነ ቅጾቹ አንድ ላይ ሊላኩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ የአዲሱ ጉባኤ አድራሻ ባይታወቅስ? የጉባኤው ጸሐፊ የቦታ ለውጥ የሚያደርገውን ሰው ስምና አዲሱን አድራሻውን ለቅርንጫፍ ቢሮው ከላከ ግለሰቡ ረጅም ጊዜ የሚፈጅ ፍለጋ ከማድረግ ሊተርፍ ይችላል። ተዛውሮ በሄደበት ቦታ ያለውን የጉባኤ አድራሻና የስብሰባዎቹን ሰዓት ለመስጠት ፈቃደኞች ነን። እንዲሁም ለአዲሱ ጉባኤ ወደ ክልላቸው ተዛውሮ የሄደውን ፍላጎት ያለው ሰው አድራሻ ማሳወቅ እንችላለን። የቦታ ለውጥ ያደረገው ሰው የጉባኤ አስፋፊ ከሆነ የጉባኤው ጸሐፊ መጻፍ እንዲችል የአዲሱን ጉባኤ የፖስታ አድራሻ ልንሰጠው እንችላለን።
ግለሰቡ በሄደበት አካባቢ አንድም ጉባኤ ከሌለ የወረዳ የበላይ ተመልካቹ አስፋፊውን ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪውን እንዲጎበኘው ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን። በተጨማሪም ለጉባኤ አስፋፊዎችና ቋሚ የጉባኤ ተሰብሳቢዎች ለሆኑ ሰዎች የመንግሥት አገልግሎታችን የመሳሰሉትን አስፈላጊ የሆኑ ጽሑፎች ልንልክላቸው እንችላለን። ግለሰቡ በእንዲህ ዓይነት ገለልተኛ ቦታ የሚኖር ከሆነ በተቻለ ፍጥነት የመጽሔቶቻችን ኮንትራት እንዲገባ ዝግጅት ማድረጉ ጠቃሚ ነው። እንዲሁም አስፋፊዎች በመስክ አገልግሎት የሚያበረክቷቸው አንዳንድ ጽሑፎች እንዲላኩላቸው ማዘዝ ይችላሉ። አንድ ሰው ጊዜ ሳያባክን በሄደበት አዲስ አካባቢ ‘ብርሃኑ እንዲበራ’ ማድረጉ መብት ብቻ ሳይሆን ጥበቃም ነው። (ማቴ. 5:
-