-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 25—ሰቆቃወ ኤርምያስ“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
-
-
—ዘዳ. 28:53) በተጨማሪም ሰቆቃወ ኤርምያስ ዘዳግም 28:63-65 ለመፈጸሙ ግልጽ ማስረጃ ነው። ከዚህም በላይ ብዙ ጊዜ ከሌሎች የቅዱሳን መጻሕፍት ክፍሎች ይጠቅሳል። (ሰቆ. 2:15—መዝ. 48:2፤ ሰቆ. 3:24—መዝ. 119:57) ዳንኤል 9:5-14 በሕዝቡ ላይ የደረሰው ጥፋት ሕጉን በመተላለፋቸው ምክንያት እንደመጣ በመግለጽ ሰቆቃወ ኤርምያስ 1:5ን እና 3:42ን ይደግፋል።
15 በኢየሩሳሌም ላይ የደረሰው ሰቆቃ በእርግጥም አሳዛኝ ነበር! የሰቆቃወ ኤርምያስ መጽሐፍ ጸሐፊ፣ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እያሉም እንኳ ይሖዋ ፍቅራዊ ደግነትና ምሕረት በማሳየት ጽዮንን እንደሚያስባትና ከምርኮ እንደሚመልሳት ያለውን እምነት ያስተጋባል። (ሰቆ. 3:31, 32፤ 4:22) መጽሐፉ፣ ጥንት ንጉሥ ዳዊትና ሰሎሞን በኢየሩሳሌም በነገሡበት ጊዜ እንደነበረው ያለ “አዲስ ዘመን” እንደሚመጣ የሚገልጽ ተስፋ ይዟል። ይሖዋ የዘላለም መንግሥት ለመመሥረት ከዳዊት ጋር የገባው ቃል ኪዳን እንደተጠበቀ ነበር! “ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው።” በጽድቅ መንግሥቱ ሥር የሚኖሩ ይሖዋን የሚወዱ ፍጥረታት ሁሉ “እግዚአብሔር ዕድል ፈንታዬ ነው” በማለት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በምስጋና እስከሚዘምሩበት ጊዜ ድረስ ርኅራኄ ማሳየቱን ይቀጥላል።—5:21፤ 3:22-24
-
-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 26—ሕዝቅኤል“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
-
-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 26—ሕዝቅኤል
ጸሐፊው:- ሕዝቅኤል
የተጻፈበት ቦታ:- ባቢሎን
ተጽፎ ያለቀው:- 591 ከክ. ል. በፊት ገደማ
ታሪኩ የሚሸፍነው ጊዜ:- ከ613 ከክ. ል. በፊት እስከ 591 ከክ. ል. በፊት ገደማ
በ617 ከክርስቶስ ልደት በፊት የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን ኢየሩሳሌምን ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጠ። ናቡከደነፆርም በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ቦታ የነበራቸውን ሰዎች እንዲሁም በይሖዋ ቤትና በንጉሡ ቤት የነበሩትን ንብረቶች ወደ ባቢሎን አጋዘ። ከምርኮኞቹ መካከል የንጉሡ ቤተሰብና መሳፍንቱ፣ የጦር አለቆቹ፣ ተዋጊዎቹ፣ የእጅ ባለሙያዎችና ግንበኞች እንዲሁም የቡዝ ልጅ ካህኑ ሕዝቅኤል ይገኙበት ነበር። (2 ነገ. 24:11-17፤ ሕዝ. 1:1-3) ልባቸው በሐዘን የተሰበረው እነዚህ እስራኤላውያን ምርኮኞች ተራራማ ከሆነው፣ ምንጮች ከሞሉበትና ሸለቆዎች ካሉበት ምድራቸው ተነስተው አድካሚ ጉዞ በማድረግ ሜዳማ ወደሆነው መድረሻቸው ደረሱ። ከዚያም በኮቦር ወንዝ አጠገብ በአንድ ኃያል መንግሥት ሥር፣ እንግዳ ባህል ባላቸውና አረማዊ አምልኮ በሚያከናውኑ ሰዎች መካከል መኖር ጀመሩ። ናቡከደነፆር፣ እስራኤላውያኑ የራሳቸው ቤቶችና አገልጋዮች እንዲኖሯቸው እንዲሁም የራሳቸውን ሥራ እንዲያከናውኑ ፈቅዶላቸው ነበር። (ሕዝ. 8:1፤ ኤር. 29:5-7፤ ዕዝራ 2:65) ታታሪ ከሆኑ ሊበለጽጉ ይችሉ ነበር። እስራኤላውያን የባቢሎናውያንን ሃይማኖት ይከተሉ ወይም በፍቅረ ነዋይ ወጥመድ ይወድቁ ይሆን? በይሖዋ ላይ ማመፃቸውን ይገፉበት ይሆን? በምርኮ የተወሰዱት ይሖዋ ስለቀጣቸው መሆኑን ይገነዘቡ ይሆን? በግዞት በሚኖሩበት አገር ውስጥ አዳዲስ ፈተናዎች ይጠብቋቸው ነበር።
2 ኢየሩሳሌም ከመጥፋቷ በፊት በነበሩት አስቸጋሪ ዓመታት ይሖዋ ነቢያቶቹን ወደ እነርሱ መላኩን አላቋረጠም። ኤርምያስ እዚያው ኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር፣ ዳንኤል በባቢሎን ቤተ መንግሥት የነበረ ሲሆን ሕዝቅኤል ደግሞ ባቢሎን ውስጥ በግዞት በነበሩት አይሁዶች መካከል ነቢይ ሆኖ ያገለግል ነበር። ሕዝቅኤል እንደ ኤርምያስ ካህንና ነቢይ የነበረ ሲሆን ዘካርያስም ከጊዜ በኋላ በነቢይነትና በካህንነት አገልግሏል። (ሕዝ. 1:3) የሕዝቅኤልን ትንቢት ስናጠና ሕዝቅኤል ከ90 ጊዜ በላይ “የሰው ልጅ” ተብሎ መጠራቱን ልብ ልንለው ይገባል፤ ምክንያቱም ከዚህ ጋር በሚመሳሰል መንገድ በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች ውስጥ ኢየሱስ 80 ጊዜ ያህል “የሰው ልጅ” ተብሎ ተጠርቷል። (ሕዝ. 2:1፤ ማቴ. 8:20) ሕዝቅኤል (በዕብራይስጥ ዬቼዝቄል) የሚለው ስሙ “አምላክ ያጠነክራል” ማለት ነው። ሕዝቅኤል የነቢይነት ተልዕኮውን ከይሖዋ የተቀበለው ዮአኪን በተማረከ በአምስተኛው ዓመት ማለትም በ613 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው። በግዞት ባሳለፉት በ27ኛው ዓመት ማለትም በነቢይነት ማገልገል ከጀመረ ከ22 ዓመት በኋላም ሕዝቅኤል በሥራው ላይ እንደነበረ እናነባለን። (ሕዝ. 1:1, 2፤ 29:17) ሕዝቅኤል አግብቶ የነበረ ቢሆንም ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን ለመጨረሻ ጊዜ መክበብ በጀመረበት ቀን ሚስቱ ሞታለች። (24:2, 18) ነቢዩ የሞተበት ቀንና እንዴት እንደሞተ አይታወቅም።
3 ሕዝቅኤል በስሙ የሚጠራውን መጽሐፍ መጻፉንና መጽሐፉ ተቀባይነት ያገኙት ቅዱሳን መጻሕፍት ክፍል መሆኑን በተመለከተ የተነሳ ውዝግብ የለም። መጽሐፉ በቅዱሳን ጽሑፎች ዝርዝር ውስጥ የተጨመረው በዕዝራ ዘመን ሲሆን በመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ዘመን በነበሩት በተለይም ኦሪጀን ባዘጋጀው የቅዱሳን ጽሑፎች ዝርዝር ውስጥ ይገኛል። በተጨማሪም መጽሐፉ የሚጠቀምባቸው ምሳሌያዊ አገላለጾች በኤርምያስና በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ጋር በሚያስገርም ሁኔታ መመሳሰላቸው የመጽሐፉን ትክክለኛነት ያረጋግጣል።—ሕዝ. 24:2-12—ኤር. 1:13-15፤ ሕዝ. 23:1-49—ኤር. 3:6-11፤ ሕዝ. 18:2-4—ኤር. 31:29, 30፤ ሕዝ. 1:5, 10—ራእይ 4:6, 7፤ ሕዝ. 5:17—ራእይ 6:8፤
-