-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 26—ሕዝቅኤል“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
-
-
ይሖዋ ከፍ ከፍ እንደሚያደርገው ተናግሯል።—ሕዝ. 17:22-24፤ ኢሳ. 11:1-3
32 ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደስ የተመለከተውን ራእይ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ስለ “ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም” ከተገለጸው ራእይ ጋር ማወዳደሩ ጥሩ ነው። (ራእይ 21:10) በሁለቱ ራእዮች መካከል ልዩነቶች አሉ፤ ለምሳሌ ሕዝቅኤል የተመለከተው መቅደስ የሚገኘው ነጠል ብሎ በከተማዋ ሰሜናዊ ክፍል ሲሆን በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሰችው ከተማ መቅደስ ግን ይሖዋ ራሱ ነው። ሆኖም ሁለቱም ስለሚፈስሰው የሕይወት ወንዝ፣ በየወሩ ስለሚያፈሩትና ቅጠሎቻቸው ለመፈወሻነት ስለሚያገለግሉት ዛፎች እንዲሁም የይሖዋ ክብር በዚያ ስለመኖሩ ተናግረዋል። ሁለቱም ራእዮች ለይሖዋ ንግሥና እንዲሁም ለእርሱ ቅዱስ አገልግሎት ለሚያቀርቡለት ሰዎች ላደረገው የመዳን ዝግጅት አድናቆት እንዲኖረን የራሳቸውን አስተዋጽኦ ያበረክታሉ።—ሕዝ. 43:4, 5—ራእይ 21:11፤ ሕዝ. 47:1, 8, 9, 12—ራእይ 22:1-3
33 የሕዝቅኤል መጽሐፍ ይሖዋ ቅዱስ እንደሆነ ጠበቅ አድርጎ ይገልጻል። የይሖዋ ስም መቀደስ ከማንኛውም ነገር ይበልጥ አንገብጋቢ መሆኑን ያስታውቃል። “የታላቁን ስሜን ቅድስና አሳያለሁ፤ . . . አሕዛብ እኔ እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW] እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW]።” ትንቢቱ እንደሚያሳየው የማጎጉን ጎግ ጨምሮ ስሙን የሚያረክሱትን በጠቅላላ በማጥፋት ስሙን ይቀድሳል። በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አምልኮ ለማቅረብ እርሱ የሚፈልግባቸውን ብቃቶች በማሟላት በአሁኑ ጊዜ በአኗኗራቸው ይሖዋን የሚቀድሱ ሰዎች ጥበበኞች ናቸው። እነዚህ ሰዎች ከይሖዋ መቅደስ በሚፈስሰው ወንዝ አማካኝነት ፈውስና የዘላለም ሕይወት ያገኛሉ። “እግዚአብሔር በዚያ አለ” ተብላ የምትጠራው ከተማ የላቀ ክብርና ፍጹም ውበት አላት!—ሕዝ. 36:23፤ 38:16፤ 48:35
-
-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 27—ዳንኤል“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
-
-
የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 27—ዳንኤል
ጸሐፊው:- ዳንኤል
የተጻፈበት ቦታ:- ባቢሎን
ተጽፎ ያለቀው:- 536 ከክ. ል. በፊት ገደማ
ታሪኩ የሚሸፍነው ጊዜ:- ከ618 እስከ 536 ከክ. ል. በፊት ገደማ
የዳንኤል መጽሐፍ፣ የምድር መንግሥታት በሙሉ በጥፋት አፋፍ ላይ በቆሙበት በዚህ ዘመን ለምንኖረው ሰዎች ከፍተኛ ቁም ነገር ያዘሉ ትንቢታዊ መልእክቶች ይዞልናል። የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆኑት የሳሙኤልና የነገሥት እንዲሁም የዜና መዋዕል መጻሕፍት፣ የአምላክን አገዛዝ ይወክል ስለነበረው የዳዊት ሥርወ መንግሥት በወቅቱ የነበሩ ሰዎች በጻፉት ታሪክ ላይ የተመሠረቱ ዘገባዎች ሲሆኑ የዳንኤል መጽሐፍ ግን በዓለም መንግሥታት ላይ ያተኩራል። መጽሐፉ ከዳንኤል ዘመን አንሥቶ እስከ “ፍጻሜው ዘመን” ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በሚነሡት ታላላቅ ሥርወ መንግሥታት መካከል የሚኖረውን የሥልጣን ሽኩቻ የሚገልጽ ራእይ ይዟል። የዳንኤል መጽሐፍ ከብዙ ዘመናት አስቀድሞ የተጻፈ የዓለም ታሪክ ነው። መጽሐፉ “በኋለኛው ዘመን” ስለሚሆነው ነገር በመግለጽ ትኩረት በሚስብ መንገድ ይደመደማል። እንደ ናቡከደነፆር ሁሉ ብሔራትም፣ “ልዑሉ በሰዎች መንግሥታት ሁሉ ላይ እንደሚገዛ” እንዲሁም እነዚህን መንግሥታት “የሰውን ልጅ የሚመስል” ለተባለው መሲሕና ገዢ ማለትም ለክርስቶስ ኢየሱስ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው በግድ እንዲገነዘቡ ይደረጋሉ። (ዳን. 12:4፤ 10:14 የ1954 ትርጉም፤ 4:25፤ 7:13, 14፤ 9:25፤ ዮሐ. 3:13-16) በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው የዳንኤል መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙትን ትንቢቶች ፍጻሜ በትኩረት መከታተላችን፣ የይሖዋን ትንቢት የመናገር ችሎታ እንዲሁም ሕዝቦቹን ለመጠበቅና ለመባረክ የሰጠውን ማረጋገጫ ይበልጥ እንድንገነዘብ ያደርገናል።—2 ጴጥ. 1:19
2 መጽሐፉ የተሰየመው በጸሐፊው ስም ነው። “ዳንኤል” (በዕብራይስጥ ዳኒየል) የሚለው ስም “ፈራጄ አምላክ ነው” የሚል ትርጉም አለው። በዳንኤል ዘመን ይኖር የነበረው ሕዝቅኤል፣ ከኖኅና ከኢዮብ ጋር ዳንኤልን አብሮ መጥቀሱ ዳንኤል በእርግጥም በሕይወት የነበረ ሰው መሆኑን ያረጋግጥልናል። (ሕዝ. 14:14, 20፤ 28:3) ዳንኤል መጽሐፉን የጀመረው “የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በነገሠ በሦስተኛው ዓመት” መሆኑን ገልጿል። ኢዮአቄም፣ የናቡከደነፆር ገባር ንጉሥ ሆኖ መግዛት የጀመረበት ሦስተኛ ዓመት 618 ከክርስቶስ ልደት በፊት ነው።a ዳንኤል፣ እስከ ቂሮስ ሦስተኛ የግዛት ዓመት ማለትም እስከ 536 ከክርስቶስ ልደት በፊት ድረስ ትንቢታዊ ራእዮችን መመልከቱን ቀጥሎ ነበር። (ዳን. 1:1፤ 2:1፤ 10:1, 4) በዳንኤል የሕይወት ዘመን፣ ትኩረት የሚስቡ ብዙ ታላላቅ ድርጊቶች ተፈጽመዋል! ይህ ነቢይ የልጅነት ሕይወቱን ያሳለፈው በይሁዳ በሚገዛው የአምላክ መንግሥት ሥር ነበር። በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ እያለ፣ እንደ እርሱው መሳፍንት ከሆኑ አይሁዳዊ ጓደኞቹ ጋር ወደ ባቢሎን ተወሰደ። ባቢሎን በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ የተጠቀሰው ሦስተኛው የዓለም ኃያል መንግሥት ሲሆን ይህ መንግሥት ከተነሣበት ጀምሮ እስከ ወደቀበት ጊዜ ድረስ ዳንኤል በዚህ አገር ኖሯል። ነቢዩ በአራተኛው የዓለም ኃያል መንግሥት ማለትም በሜዶ
-