-
አድማጮችን የሚያበረታታ ንግግርበቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
-
-
አምላክ እያደረገልን ባለው ነገር እንደምትደሰት አሳይ። ወንድሞችህን ለማበረታታት ስትፈልግ ይሖዋ ዛሬ እያደረገልን ስላሉት ነገሮች እንዲያስቡ አድርግ። አንተ ራስህ በእነዚህ ነገሮች እንደምትደሰት በሚያሳይ መንገድ የምትናገር ከሆነ እነርሱም ተመሳሳይ ስሜት ያድርባቸዋል።
ይሖዋ የኑሮ ጭንቀቶችን እንድንቋቋም የሚረዳን እንዴት እንደሆነ አስረዳ። ሕይወታችንን መምራት የምንችልበትን ከሁሉ የተሻለ መንገድ ያስተምረናል። (ኢሳ. 30:21) የወንጀል፣ የፍትሕ መጓደል፣ የድህነት፣ የበሽታና የሞት መንስኤያቸው ምን እንደሆነና እነዚህን ነገሮች እንዴት እንደሚያስወግድልን ይነግረናል። ፍቅር ባለበት የወንድማማች ማኅበር ውስጥ እንድንታቀፍ አድርጓል። ውድ የሆነ የጸሎት መብት ሰጥቶናል። የእርሱ ምሥክሮች የመሆንም ታላቅ መብት አግኝተናል። ክርስቶስ በሰማይ ንጉሣዊ ሥልጣኑን እንደጨበጠና የዚህ አሮጌ ሥርዓት የመጨረሻ ቀኖች በፍጥነት ወደ ፍጻሜያቸው እየገሰገሱ እንዳሉ እንድናስተውል ረድቶናል።—ራእይ 12:1-12
ከእነዚህ ሁሉ በረከቶች በተጨማሪ የጉባኤ፣ የወረዳና የልዩ እንዲሁም የአውራጃ ስብሰባዎቻችንን ጥቀስ። ለእነዚህ ዝግጅቶች ልባዊ አድናቆት እንዳለህ በሚያሳይ መንገድ በመናገር ሌሎችም ከወንድሞቻቸው ጋር መሰብሰብን በቁም ነገር እንዲያዩት ማበረታታት ትችላለህ።—ዕብ. 10:23-25
ይሖዋ በአገልግሎት የምናደርገውን ጥረት እንደባረከው የሚያሳዩ ሪፖርቶችም የብርታት ምንጭ ይሆናሉ። በመጀመሪያው መቶ ዘመን ጳውሎስና በርናባስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲጓዙ በመንገዳቸው ላይ ላገኟቸው ወንድሞች ስለ አሕዛብ መለወጥ የሚገልጹ ሪፖርቶችን በመንገር ‘እጅግ ደስ አሰኝተዋቸው ነበር።’ (ሥራ 15:3) አንተም ገንቢ ተሞክሮዎችን በመናገር ወንድሞችህን ልታስደስታቸው ትችላለህ።
በተጨማሪም ወንድሞች የሚያደርጉትን ነገር ስናደንቅላቸው ይበረታታሉ። በአገልግሎት ለሚያደርጉት ተሳትፎ አመስግናቸው። በዕድሜ መግፋት ወይም በሕመም ምክንያት ብዙ እንቅስቃሴ ማድረግ የማይችሉትን ሆኖም በታማኝነት የጸኑትን አመስግናቸው። ይሖዋ ለስሙ ያሳዩትን ፍቅር እንደማይረሳ እንዲያስቡ አድርግ። (ዕብ. 6:10) የተፈተነ እምነት በዋጋ የማይተመን ውድ ሀብት ነው። (1 ጴጥ. 1:6, 7) ወንድሞች ይህን እንዲያስታውሱ ማድረግ ያስፈልጋል።
ስለ ወደፊቱ ተስፋ ከልብ በመነጨ ስሜት ተናገር። በአምላክ መንፈስ አማካኝነት የተነገሩት ተስፋዎች ይሖዋን ለሚወዱ ሁሉ ትልቅ የብርታት ምንጭ ናቸው። አብዛኞቹ አድማጮችህ ስለ እነዚህ ተስፋዎች በተደጋጋሚ ሰምተው ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ በአድናቆት የምትናገር ከሆነ እነዚህ ተስፋዎች ለአድማጮችህ ሕያው ሊሆኑላቸው፣ እንደሚፈጸሙ ትምክህት ሊያድርባቸውና ልባቸው በአድናቆት ሊሞላ ይችላል። በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ያገኘኸውን ትምህርት ሥራ ላይ ማዋልህ በዚህ መንገድ እንድትናገር ሊረዳህ ይችላል።
ይሖዋ ሕዝቡን በማጽናናትና በማበረታታት ረገድ አቻ የሌለው አምላክ ነው። ይሁን እንጂ አንተም የእርሱን ምሳሌ በመኮረጅ ሌሎችን ማበረታታትና ማጽናናት ትችላለህ። ለጉባኤው ንግግር የምትሰጥበት አጋጣሚ ስታገኝ ይህን ለማድረግ ጣር።
-
-
እድገት ማድረግህን ቀጥልበቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
-
-
እድገት ማድረግህን ቀጥል
በእያንዳንዱ ምክር መስጫ ነጥብ ሠርተህበታል? የቀረቡትን መልመጃዎች በሙሉ ሠርተህባቸዋል? በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤትም ሆነ በሌሎች ስብሰባዎች ላይ ንግግር ስታቀርብ እንዲሁም በአገልግሎት ስትካፈል የተማርከውን እያንዳንዱን ነጥብ እየሠራህበት ነው?
-