-
ትናንሽ ልጆችም መጠመቅ አለባቸውን?የመንግሥት አገልግሎት—2002 | ጥቅምት
-
-
ትናንሽ ልጆችም መጠመቅ አለባቸውን?
1 ትናንሽ ልጆችም ጭምር መጠመቅ አለባቸውን? በራእዩ ውስጥ ይሖዋ መሣሪያ ለታጠቁት ስድስት ሰዎች የሚከተለውን መመሪያ ሰጥቷቸው ነበር:- “ሽማግሌውንና ጎበዙን፣ ቆንጆይቱንም፣ ሕጻናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ።” (ሕዝ. 9:6) እርግጥ ራሳቸውን ለመወሰን ያልደረሱ ትናንሽ ልጆች ወላጆቻቸው ይሖዋን እንዲወዱ አድርገው እያሳደጓቸው ከሆነና ልጆቹ በታዛዥነት ለውጥ ካደረጉ በወላጆቻቸው ላይ ባለው “ምልክት” መሠረት ከጥፋቱ ይጠበቃሉ። (1 ቆሮ. 7:14) ነገር ግን ልጁ የግል ውሳኔ ለማድረግ በቂ ማስተዋል ካለውና ‘በጎ ማድረግ ወደሚያውቅበት’ ደረጃ ከደረሰ በወላጆቹ “ምልክት” ለሁልጊዜው ተጠልሎ ይኖራል ብላችሁ አታስቡ።—ያዕ. 4:17
2 አንድ ትንሽ ልጅ ራሱን ከመወሰኑ በፊት ነገሩ ምን ማለት እንደሆነ እንዲገባው በቂ እውቀት ሊኖረው እንዲሁም ከአምላክ ጋር የግል ዝምድና የመመሥረት ፍላጎት ሊያዳብር ይገባል። የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች መረዳትና ከእነርሱም ጋር ተስማምቶ መኖር እንዲሁም ቢጥሳቸው ተጠያቂ እንደሚሆን ማወቅ ያስፈልገዋል። በተጨማሪም እምነቱን ለሌሎች በማካፈል ረገድ በቂ ተሞክሮ ሊኖረውና ይህ ሥራ የእውነተኛ አምልኮ አንዱ ትልቅ ክፍል መሆኑን ሊያውቅ ይገባዋል። አምላክን ለማገልገል ልባዊ ፍላጎት ሊኖረው ይገባል። የትልቅ ሰውን ያህል ጉልምስና እንዲያሳይ አይጠበቅበትም፣ ቢሆንም መንፈሳዊ እድገቱ በእርሱ ደረጃ ወደፊት እየቀጠለ የሚሄድ መሆን አለበት።
3 አንድ ትንሽ ልጅ ‘ወጪውን አስልቶ’ ከሆነ ራሱን ቢወስን ምንም ጉዳት አይደርስበትም። በአብዛኞቹ አዳዲስ ክርስቲያኖች እንደታየው ሁሉ ከጥምቀት በኋላ አድናቆታቸው ጥልቀት ያለው ይሆናል። ዴቪድ የተባለ አንድ ወጣት እንዲህ ብሏል:- “በልጅነቴ መጠመቄ ጥበቃ ሆኖልኛል። እያደግሁ ስሄድ በጉባኤው ውስጥ ያሉ አንዳንድ ያልተጠመቁ ልጆች ከሽማግሌዎቹ ሥልጣን ነጻ እንደሆኑ እንደተሰማቸውና ከዚህ የተነሳ ወደ መጥፎ አድራጎት እንደገቡ ተመልክቻለሁ። እኔ ግን ሕይወቴን ለአምላክ እንደወሰንኩ ሁልጊዜ አስታውስ ነበር። ሕይወቴ የአምላክ ንብረት ነው። ስለዚህ እንደነዚህ ያሉትን ወጣቶች ለመከተል አልቻልኩም።”
4 ‘ልጄ ገና በትንሽነቱ ተጠምቆ (ተጠምቃ) በኋላ ቢቀዘቅዝስ (ብትቀዘቅዝስ)?’ በማለት አንዳንድ ወላጆች ይጠይቃሉ። እርግጥ ነው አንድ ወጣት ልጅ ወላጆቹን ለማስደሰት ብቻ ወይም ጓደኞቼ አድርገውታል ብሎ መጠመቅ የለበትም። ይሁን እንጂ ዮሴፍ፣ ሳሙኤል፣ ንጉሥ ኢዮስያስና ኢየሱስ ገና በልጅነታቸው የይሖዋን አምልኮ በቁምነገር ተመልክተው አጥብቀው ይዘውታል።—ዘፍ. 37:2፤ 39:1-3፤ 1 ሳሙ. 1:24-28፤ 2:18-21፤ 2 ዜና 34:3፤ ሉቃስ 2:42-49
5 በዘመናችን ዣን የተባለች አንዲት ክርስቲያን የተጠመቀችው በአሥር ዓመቷ ነበር። ከጊዜ በኋላ የወሰደችው እርምጃ ገብቷት እንደነበረ ስትጠየቅ ዣን “ይሖዋን እንደምወድ አውቅ ነበር፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገልንን አደንቅ ነበር፣ ስለዚህ ይሖዋን ለማገልገል ፈለግኩ” ብላ መልሳለች። ከጥምቀቷ በኋላ ከ40 ለሚበልጡ ዓመታት በታማኝነት አገልግላለች። በአገራችንም በትንሽነታቸው የተጠመቁ በርካታ የሙሉ ጊዜ አገልጋዮችና አስፋፊዎች አሉ። እያንዳንዱ ወጣት ልጅ የተለየ ግለሰብ ነው፣ ማንም ሰው አንድ ቋሚ የዕድሜ ወሰን ማበጀት አይችልም። ወላጆች የልጆቻቸውን ልብ ለመንካት መጣር አለባቸው። ለአምላክ ያደሩ የመሆንን ባሕርይ እንዲያዳብሩ ሊረዷቸው ይገባል። በልጆቹ ፊት ራስን የመወሰንንና የመጠመቅን መብት ከማስቀመጣቸውም በተጨማሪ የማይነቃነቁ አምላኪዎች እንዲሆኑ ሊያጠናክሯቸው ይገባል።—3 ዮሐ. 4
-
-
አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራምየመንግሥት አገልግሎት—2002 | ጥቅምት
-
-
አዲስ የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም
1 በዚህ ተለዋዋጭ በሆነ ዓለም ውስጥ በእምነት ጸንተን ለመቆም እንድንችል በይሖዋ መታመን አለብን። በይሖዋ መታመን ሲባል ምን ማለት ነው? በይሖዋ መታመናችን የእኛንም ሆነ የቤተሰባችንን ሕይወት የሚነካው እንዴት ነው? የሰይጣን ዓለም የሚያሳድርብንን ተጽዕኖ ለመቋቋም የሚረዳንስ እንዴት ነው? በ2003 የወረዳ ስብሰባ ፕሮግራም ላይ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እናገኛለን። የስብሰባው ጭብጥ “በይሖዋ ታመኑ፣ መልካምም አድርጉ” የሚል ነው።—መዝ. 37:3 NW
2 በይሖዋ የምንታመን መሆናችንን የምናሳየው አንዳንድ የተለዩ ወይም አስቸጋሪ የሆኑ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙን ጊዜ ብቻ አይደለም። በዕለት ተዕለት ሕይወታችንም በይሖዋ እንደምንታመን ልናሳይ ይገባል። “ሁልጊዜ በይሖዋ ታመኑ” የሚለው የመክፈቻ ንግግር ይህንን የሚያጎላ ይሆናል። (መዝ. 62:8) “በይሖዋ የምንታመን መሆናችንን ማሳየት” በሚል ርዕስ የሚቀርበው ባለ አራት ክፍል ሲምፖዚየም የተሳካ ትዳር ለመመሥረት፣ በቤተሰብ ክልል ውስጥ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታትና ቁሳዊ ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት እንድንችል የሚረዱንን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች እንዴት መርምረን ማግኘትና በሥራ ላይ ማዋል እንደምንችል ያሳየናል።
3 የሰይጣን ዓለም ትክክልና ስህተት የሆኑ ነገሮችን በሚመለከት የተዛባ አመለካከት እንድንይዝ ለማድረግ የሚሞክር ከመሆኑም በላይ ለምን ነገሮች ቅድሚያ መስጠት እንዳለብን ግራ እንዲገባን ያደርጋል። (ኢሳ. 5:20) “ከንቱ የሕይወት ግቦችን ከማሳደድ ተጠበቁ” እና “ከክፉ ራቁ—መልካሙን የምታደርጉ ሁኑ” የሚሉት ንግግሮች የይሖዋን የላቁ የሥነ ምግባር መሥፈርቶች ለማክበር የገባነውን ቁርጥ አቋም ያጠናክሩልናል።—አሞጽ 5:14
4 ይሖዋ በጊዜያችን ያለውን ክፉ ሥርዓት በሚያጠፋበት ወቅት አገልጋዮቹ በእርሱ ሙሉ በሙሉ መታመን ያስፈልጋቸዋል። “ከዓለም መከራ ነጻ የምንወጣበት ጊዜ ቀርቧል” በሚል ርዕስ የሚቀርበው የሕዝብ ንግግር ይህንን ያብራራል። ከዚያም “የአምላክ መንግሥት ዜጋ ለመሆን ትበቁ ይሆን?” የሚለው ንግግር ራሳችንን እንድንመረምር ግብዣ ያቀርብልናል። በመጨረሻም ስብሰባው “ይሖዋ በገባቸው ተስፋዎች ላይ እምነት ይኑራችሁ” የሚል ጥብቅ ማሳሰቢያ በያዘ ንግግር ይደመደማል።
5 በሁሉም ትልልቅ ስብሰባዎች ላይ ጎላ ያለ ቦታ ከሚሰጣቸው ንግግሮች አንዱ የጥምቀት ንግግር ነው። ለመጠመቅ የሚፈልጉ ሁሉ ከአሁኑ አስፈላጊውን ዝግጅቶች ማድረግ ይቻል ዘንድ ለጉባኤያቸው ሰብሳቢ የበላይ ተመልካች በተቻለ ፍጥነት ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።
6 በዚህ አስተማማኝ ባልሆነ ጊዜ ትምክህት ሊጣልበት የሚችለውና ጽኑ መታመኛ የሆነው ይሖዋ ብቻ ነው። (መዝ. 118:8, 9) ሁላችንም ከወረዳ ስብሰባው ፕሮግራም አንዱም እንዳያመልጠን በማድረግ በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት እናጠናክር።
-