የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ነሐሴ 29, 2011 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
1. የአምላክ ፍቅራዊ ደግነት ‘ከሕይወት ይሻላል’ ሊባል የሚችለው እንዴት ነው? (መዝ. 63:3 NW) [w01 10/15 ገጽ 15 አን. 17]
2. መዝሙር 70 ስለ ዳዊት ምን ይጠቁመናል? [w08 9/15 ገጽ 4 አን. 4]
3. መዝሙር 75:5 ስለ ምን ነገር ያስጠነቅቃል? [w06 7/15 ገጽ 11 አን. 3]
4. ይሖዋ ጸሎታችንን እንደሚሰማ እርግጠኛ ሆነን መጠበቅ ያለብን በተለይ ስለ የትኞቹ ጉዳዮች ስንጸልይ ነው? (መዝ. 79:9) [w06 7/15 ገጽ 12 አን. 5]
5. ከመዝሙር 90:7, 8 ምን ትምህርት እናገኛለን? [w01 11/15 ገጽ 12-13 አን. 14-16]
6. በመዝሙር 92:12-15 ላይ እንደተገለጸው በጉባኤ ውስጥ ያሉ በዕድሜ የገፉ የይሖዋ አገልጋዮች ምን ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል? [w04 5/15 ገጽ 13-14 አን. 14-18]
7. በመዝሙር 102:25-27 ላይ ተመዝግበው የሚገኙት የመዝሙራዊው ቃላት አምላክ ለምድር ካለው ዘላለማዊ ዓላማ ጋር ይጋጫሉ? (ዘፍ. 1:28) [w08 4/1 ገጽ 12 አን. 1]
8. አስተዋይ አለመሆን ያለውን አደጋ አስመልክቶ ከመዝሙር 106:7 ምን ትምህርት እናገኛለን? [w95 9/1 ከገጽ 19 አን. 4 እስከ ገጽ 20 አን. 2]
9. በመዝሙር 110:1, 4 መሠረት ይሖዋ ተስፋ የተደረገበትን ዘር ወይም መሲሕ በተመለከተ ምን ዓይነት መሐላ ገብቷል? ይህስ የሰው ዘር በሙሉ በረከት እንዲያገኝ በር የሚከፍተው እንዴት ነው? [cl ገጽ 194 አን. 13]
10. መዝሙራዊው አምላክን በማገልገል ባገኛቸው ጥቅሞች ላይ ማሰላሰሉ ምን በጎ ተጽዕኖ አሳድሮበታል? (መዝ. 116:12, 14) [w09 7/15 ገጽ 29 አን. 4-5]