“. . . መጽሔቶችን ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች”
በየወሩ በአገልግሎት ስብሰባ ላይ መጽሔቶችን እንዴት ማበርከት እንደምንችል የሚያሳይ ክፍል ይቀርባል። የዚህ ክፍል ዓላማ የመጽሔቶቹን ርዕሶች መከለስ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ይህ ክፍል የተዘጋጀው መጽሔቶችን ለማበርከት በሚረዱ ሐሳቦች ላይ ለመወያየት ነው። በመሆኑም በመመሪያው መሠረት፣ ክፍሉ የተሰጠው ወንድም አድማጮች መጽሔቶቹን ለማበርከት ያላቸው ጉጉት እንዲቀሰቀስ የሚያደርግ በጣም አጭር የመግቢያ ሐሳብ ይናገራል። ከዚያም ርዕሶችን (ተከታታይ የሆኑትን እንደ አንድ ርዕስ መቁጠር ይቻላል) ተራ በተራ እያነሳ አስፋፊዎች በአገልግሎት ላይ እንዴት ሊጠቀሙበት እንዳሰቡ ሐሳብ እንዲሰጡ ይጋብዛል፤ ይህ ደግሞ ሁሉም አስፋፊዎች ክፍሉን ለመከታተልና በአገልግሎት ሊጠቀሙበት የሚችሉትን ሐሳብ ለማግኘት ይረዳቸዋል። አድማጮች ሙሉ የመግቢያ ሐሳብ እንዲናገሩ ከማድረግ ይልቅ በቅድሚያ በአገልግሎት ላይ ሊጠቀሙባቸው ያሰቧቸውን ትኩረት የሚስቡ ጥያቄዎች እንዲናገሩ በመጋበዝ ለብዙ ሰዎች ዕድል ይሰጣል፤ ከዚያም አድማጮች ሊያነብቡ ያሰቡትን ጥቅስ እንዲናገሩ ይጋብዛል። ለእያንዳንዱ መጽሔት ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ በማድረግ ክፍሉን ይደመድማል። ክፍሉ በሚቀርብበት ወቅት ሐሳብ ለመስጠት እንድንችል አስቀድመን መጽሔቶቹን መከለሳችን አስፈላጊ ነው። ሁሉም ሰው ጥሩ ዝግጅት አድርጎ የሚመጣ ከሆነ አንዳችን ሌላውን መሳል እንችላለን።—ምሳሌ 27:17