የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 12/12 ገጽ 2
  • ታኅሣሥ 24 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ታኅሣሥ 24 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ታኅሣሥ 24 የሚጀምር ሳምንት
የመንግሥት አገልግሎታችን—2012
km 12/12 ገጽ 2

ታኅሣሥ 24 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም

ታኅሣሥ 24 የሚጀምር ሳምንት

መዝሙር 5 እና ጸሎት

□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦

w09 6/15 ከገጽ 19 አን. 13 እስከ ገጽ 20 አን. 20 (30 ደቂቃ)

□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዘካርያስ 9-14 (10 ደቂቃ)

ቁ. 1፦ ዘካርያስ 11:1-13 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ቁ. 2፦ አምላክ ለመስማት ፈቃደኛ የሚሆነው የእነማንን ጸሎት ነው?—rs ከገጽ 292 አን. 1 እስከ ገጽ 293 አን. 1 (5 ደቂቃ)

ቁ. 3፦ ምሳሌ 15:1 ላይ ያለውን ምክር ምን ዓይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ተግባራዊ ማድረግ እንችላለን? (5 ደቂቃ)

□ የአገልግሎት ስብሰባ፦

መዝሙር 28

30 ደቂቃ፦ ሕጋዊ ድረ ገጻችንን በጥሩ ሁኔታ መጠቀም የምንችለው እንዴት ነው? ከገጽ 3-6 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። ገጽ 4 ላይ ስትወያዩ አንድ ቤተሰብ፣ የቤተሰብ አምልኳቸውን ከማጠናቀቃቸው በፊት የሚያደርጉትን ነገር የሚያሳይ ሦስት ደቂቃ የሚወስድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የቤተሰቡ ራስ፣ በሚቀጥለው ሳምንት ምን ማጥናት እንደሚፈልጉ የቤተሰቡን አባላት ይጠይቃል። በዚህ ጊዜ ልጆቹ ድረ ገጹ ላይ “ቲንኤጀርስ” በሚለው ሥር ከቀረቡ ሐሳቦች መካከል የመረጡትን በመጠቆም በዚያ ላይ መወያየት እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። ከዚያም jw.org የተባለውን ድረ ገጽ በግልና በቤተሰብ ጥናት ወቅት እንዴት እንደተጠቀሙበት ወይም ወደፊት እንዴት ሊጠቀሙበት እንዳሰቡ እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ። በክልላችሁ ሊተገበር የሚችል ከሆነ፣ ገጽ 5 ላይ ስትወያዩ አንድ አስፋፊ የምናምንባቸውን ነገሮች በተመለከተ ጥያቄ ላቀረበለት አንድ ሰው በተንቀሳቃሽ የኤሌትሮኒክ መሣሪያ አማካኝነት ድረ ገጹን ተጠቅሞ ሲመልስለት የሚያሳይ ሦስት ደቂቃ የሚወስድ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። ገጽ 6 ላይ ስትወያዩ ደግሞ አንድ አስፋፊ በሌላ ቋንቋ ጽሑፋችንን ማንበብ ከሚፈልግ ሰው ጋር ሲወያይ የሚያሳይ የአራት ደቂቃ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። አስፋፊው የራሱን ተንቀሳቃሽ የኤሌትሮኒክ መሣሪያ ወይም የሰውየውን ኮምፒውተር ተጠቅሞ jw.org የተባለውን ድረ ገጽ በመክፈት እውነቱን ማወቅ የተባለውን ትራክት ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ ለግለሰቡ በራሱ ቋንቋ ያሳየዋል፤ ከዚያም በዚያ ላይ ይወያያሉ። jw.org የተባለውን ድረ ገጽ በአገልግሎታቸው እንዴት እንደተጠቀሙበት እንዲናገሩ አድማጮችን ጋብዝ።

መዝሙር 10 እና ጸሎት

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ