“የመጣነው . . .”
ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል የቤቱ ባለቤት በሩን ከፍቶ ደጃፉ ላይ ቆመን ሲያየን ማን እንደሆንንና ለምን እንደመጣን ሊያስብ ይችላል። ግለሰቡን ለማረጋጋት ምን ማለት እንችላለን? አንዳንድ አስፋፊዎች ለግለሰቡ ሰላምታ ከሰጡት በኋላ የመጡበትን ምክንያት ይገልጻሉ። ለምሳሌ ያህል እንዲህ ይሉ ይሆናል፦ “ወደ ቤትዎ የመጣነው ብዙ ሰዎች ወንጀል ስለሚያሳስባቸው በዚህ ጉዳይ ላይ ለመወያየት ነው። . . . ይመስልዎታል?” ወይም ደግሞ “የመጣነው መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ እንደምናስተምር ልንነግርዎ ነው።” በውይይቱ መጀመሪያ ላይ የመጣችሁበትን ምክንያት ከገለጻችሁለት የቤቱ ባለቤት የምትናገሩትን ነገር ለመስማት ሊነሳሳ ይችላል።