መዝሙር 130
ሕይወት ተአምር ነው
በወረቀት የሚታተመው
1. ልጅ መወለዱ፣ ዝናብ መጣሉ፣ የፀሐይ ደማቅ ጮራ፣ የ’ህል ዛላ፣
ሁሉም የአምላክ ስጦታ ናቸው፤ በሕይወት የኖርነው በሱ ተአምር ነው።
እንዴት ’ናመስግነው፣ ለዚህ ስጦታው?
እሱን መውደድ፣ ስጦታውን ማክበር ብቻ ነው።
(አዝማች)
በኛ ጥረት ቢሆን ጭራሽ አናገኘው፤
ሕይወት ስጦታ ነው፤ ሕይወት ተአምር ነው።
2. እንደ ኢዮብ ሚስት ተስፋ ’ሚቆርጡ፣ አምላክን ’ሚያማርሩ ሰዎች አሉ።
እኛ ግን ጌታን ’ናወድሳለን፤ በሕይወት እንድንኖር ስላደረገን።
እንዴት እናመስግን፣ ለዚህ ስጦታ?
ሰዎችን ’ንውደዳቸው እንስጣቸው ቦታ።
(አዝማች)
በኛ ጥረት ቢሆን ጭራሽ አናገኘው፤
ሕይወት ስጦታ ነው፤ ሕይወት ተአምር ነው።
(በተጨማሪም ኢዮብ 2:9ን፣ መዝ. 34:12ን፣ መክ. 8:15ን፣ ማቴ. 22:37-40ን እና ሮም 6:23ን ተመልከት።)