መዝሙር 131
ይሖዋ ይታደጋል
በወረቀት የሚታተመው
1. ይሖዋ፣ ሕያው አምላክ መሆንህ ታይቷል፤
ምድር፣ ሰማይ፣ ባሕር በሥራህ ተሞልቷል።
እንዳንተ ያለ አምላክ ከቶ የለም።
ጠላትም፣ ይጠፋል አይኖርም።
(አዝማች)
ይሖዋ ታማኞቹን ይታደጋል።
ጠንካራ ዓለት እንደሆነ ያሳያል።
ታምነን በሱ ክብሩን፣ ዝናውን ’ናውጅ ላለም።
ከፍ እናድርግ ያዳኛችንን ገናና ስም።
2. የሞት ገመድ ተብትቦኛል ስማኝ ’ባክህ፤
“ድፍረት፣ ጥንካሬን ስጠኝ” ብዬ ስጮህ፣
“ከለላ ሁነኝ” ብዬ ስማጸንህ፣
ስማኝ ከማደሪያ መቅደስህ።
(አዝማች)
ይሖዋ ታማኞቹን ይታደጋል።
ጠንካራ ዓለት እንደሆነ ያሳያል።
ታምነን በሱ ክብሩን፣ ዝናውን ’ናውጅ ላለም።
ከፍ እናድርግ ያዳኛችንን ገናና ስም።
3. ነጎድጓድ ድምፅህ ሲሰማ ከማደሪያህ፣
ጠላትህ ይርዳል፤ ይደሰታል ሕዝብህ።
የምትሻውን መሆን ትችላለህ፤
መታደግህን ታሳያለህ።
(አዝማች)
ይሖዋ ታማኞቹን ይታደጋል።
ጠንካራ ዓለት እንደሆነ ያሳያል።
ታምነን በሱ ክብሩን፣ ዝናውን ’ናውጅ ላለም።
ከፍ እናድርግ ያዳኛችንን ገናና ስም።
(በተጨማሪም መዝ. 18:1, 2ን እና መዝ. 144:1, 2ን ተመልከት።)