መዝሙር 114
የአምላክ መጽሐፍ ውድ ሀብት ነው
በወረቀት የሚታተመው
(ምሳሌ 2:1)
1. በእውቀት የተሞላ መጽሐፍ አለ፤
ሰላምን፣ ደስታን፣ ተስፋን ያዘለ።
ሐሳቦቹ ግሩም፣ ኃይልም ያላቸው፤
ብርሃን፣ ሕይወት የሚሰጡ ናቸው።
መጽሐፍ ቅዱስ ነው ይህ አስደናቂ ሀብት።
ጸሐፊዎቹን አምላክ መራቸው፤
ይሖዋን ይወዳሉ ከልባቸው፤
በመንፈስ ቅዱስ የጋሉ ናቸው።
2. ስላምላክ ፍጥረት ጻፉ እውነታውን፤
ጽንፋለም የ’ጁ ሥራ መሆኑን።
ሰው ሲፈጠር ፍጹም መሆኑን ጻፉ፤
በኋላም ከገነት መባረሩን።
ተርከዋል አንድ መልአክ የሠራውን፤
ያምላክን ሥልጣን መገዳደሩን።
ይህም ኃጢያትና ሐዘን አምጥቷል፤
በቅርቡ ግን አምላክ ድል ያደርጋል።
3. ዛሬ ደስታችን እጥፍ ድርብ ሆኗል፤
የአምላክ መንግሥት መግዛት ጀምሯል።
የይሖዋ አምላክ የማዳን ቀን ነው፤
ለሚኖሩ ከሱ ጋር ተስማምተው።
ይሄ መጽሐፍ ይህን ምሥራች ይዟል፤
ቅዱስ ማዕድ ነው እንመገበው።
ሰው የማይገምተው ሰላም ይሰጣል፤
ሕያው ነው ለማንበብ ይጋብዛል።
(በተጨማሪም 2 ጢሞ. 3:16ን እና 2 ጴጥ. 1:21ን ተመልከት።)