መዝሙር 94
አምላክ በሰጠን መልካም ነገሮች መርካት
በወረቀት የሚታተመው
1. መልካም ስጦታና ፍጹም ገጸ በረከቱ፣
ከአምላክ የተገኘ ነው ሁሉም በያይነቱ።
እሱ ከቶ አይወላውል፤ መቼም አይለወጥ።
ሁሉን ነገር የሚያሟላ ነው፤ ሕይወት ብርሃን ’ሚሰጥ።
2. ሊያስጨንቀን አይገባም፣ ለዕለት ’ሚያስፈልገን፤
ወፎችን ’ሚመግብ አምላክ፣ አለ ከጎናችን።
ከንቱ ነገር ቦታ ይጣ፤ ጊዜም አናጥፋበት።
ይልቁን ’ንርካ ባለን ነገር፤ ’ንምራ ቀላል ሕይወት።
3. በሰዎች ዘንድ ታላቅ ነገር፣ ባምላክ ፊት ከንቱ ነው።
ዘላቂ ለሆነ ጥቅም፣ ጊዜውን ’ናውለው።
በአምላክ ዘንድ ’ሚከማች ሀብት፣ አይጠፋም ብንሞትም።
ባለን መርካት በረከት ነው፤ አጥርቶ የሚያይ ዓይንም።
(በተጨማሪም ኤር. 45:5ን፣ ማቴ. 6:25-34ን፣ 1 ጢሞ. 6:8ን እና ዕብ. 13:5ን ተመልከት።)