የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb18 ጥር ገጽ 8
  • በመጀመሪያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ—እንዴት?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በመጀመሪያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ—እንዴት?
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አለመግባባትን የምትፈቱት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • አለመግባባቶችን በፍቅር መፍታት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016
  • “ከእነዚህ ከትናንሾቹ መካከል አንዱንም” አታሰናክሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • ‘ሰላም የሚገኝበትን ማንኛውንም ጥረት እናድርግ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
mwb18 ጥር ገጽ 8

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በመጀመሪያ ከወንድምህ ጋር ታረቅ—እንዴት?

አንድ ሰው መሥዋዕቱን መሠዊያው ጋር ትቶ ከወንድሙ ጋር ለመታረቅ ሲሄድ

በኢየሱስ ዘመን በገሊላ እየኖርክ እንዳለ አድርገህ አስብ። የዳስ በዓልን ለማክበር ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘሃል። ከተማዋ ልክ እንደ አንተ በዓሉን ለማክበር ከሩቅ በመጡ ሰዎች ተጨናንቃለች። ለይሖዋ መሥዋዕት ለማቅረብ አስበሃል። በመሆኑም መሥዋዕት አድርገህ የምታቀርበውን ፍየል እየጎተትክ፣ በሕዝብ የተጨናነቁትን የከተማዪቱን ጎዳናዎች አቋርጠህ ወደ ቤተ መቅደሱ እየሄድክ ነው። እዚያ ስትደርስ ቤተ መቅደሱ እንደ አንተው መሥዋዕት ለማቅረብ በመጡ ሰዎች ተሞልቷል። በመጨረሻም መሥዋዕትህን ለካህናቱ የምታስረክብበት ተራ ደረሰ። በዚህ ቅጽበት ወንድምህ ቅር የተሰኘብህ ነገር እንዳለ ትዝ አለህ፤ ወንድምህ ያለው እዚያ በተሰበሰቡት ሰዎች መሃል ወይም ከተማው ውስጥ ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲያጋጥምህ ምን ማድረግ እንዳለብህ ተናግሯል። (ማቴዎስ 5:24⁠ን አንብብ።) ኢየሱስ በሰጠው መመሪያ መሠረት አንተም ሆንክ በአንተ ቅር የተሰኘው ወንድምህ ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖራችሁ ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው? ከዚህ ቀጥሎ ከተዘረዘሩት ምርጫዎች መካከል ትክክለኛ በሆነው ላይ ምልክት አድርግ።

አንተ ማድረግ ያለብህ ነገር

  • ወንድምህን ማናገር ያለብህ ቅር ሊሰኝ የሚችልበት በቂ ምክንያት እንዳለው ከተሰማህ ብቻ ነው

  • ወንድምህ ጉዳዩን አጋንኖ እንደተመለከተው ወይም እሱም ጥፋተኛ እንደሆነ ከተሰማህ አመለካከቱን ለማስተካከል መሞከር አለብህ

  • ወንድምህ ስሜቱን አውጥቶ ሲናገር በትዕግሥት ማዳመጥ አለብህ፤ እንደዚያ የተሰማው ለምን እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ባይገባህም ስሜቱን ስለጎዳኸው ወይም ያደረግከው ነገር ያላሰብከውን ውጤት ስላስከተለ ከልብ ይቅርታ ልትጠይቀው ይገባል

ወንድምህ ማድረግ ያለበት ነገር

  • ያደረስክበትን በደል ለጉባኤው አባላት በመንገር የእነሱን ድጋፍ ለማግኘት መሞከር አለበት

  • ሊጮህብህ፣ በደልህን አንድ በአንድ ሊነግርህና ጥፋትህን አምነህ እንድትቀበል ሊያደርግህ ይገባል

  • ቅድሚያውን ወስደህ እሱን ለማናገር ምን ያህል ትሕትናና ድፍረት እንደጠየቀብህ ሊረዳና ከልቡ በነፃ ይቅር ሊልህ ይገባል

በአሁኑ ጊዜ የምናቀርበው አምልኮ የእንስሳት መሥዋዕት ማቅረብን እንደማይጠይቅ እናውቃለን፤ ሆኖም ከወንድማችን ጋር ያለን ግንኙነት ለአምላክ በምናቀርበው አምልኮ ላይ ስለሚያሳድረው ተጽዕኖ ምን ትምህርት እናገኛለን?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ