ክርስቲያናዊ ሕይወት
ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው—ራስ ወዳድና በቀላሉ የምትበሳጩ አትሁኑ
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ በመካከላቸው ባለው ፍቅር ተለይተው እንደሚታወቁ አስተምሯል። (ዮሐ 13:34, 35) የክርስቶስ ዓይነት ፍቅር ለማሳየት እንድንችል የሌሎችን ፍላጎት የምናስቀድም እንዲሁም በቀላሉ የማንበሳጭ ሰዎች መሆን ይኖርብናል።—1ቆሮ 13:5
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
አንድ ሰው ስሜትህን የሚጎዳ ነገር ቢናገር ወይም ቢያደርግ ይህ ሁኔታ እንዲፈጠር ያደረገው ምን እንደሆነና አንተ ልትወስድ ያሰብከው እርምጃ ምን እንደሚያስከትል ቆም ብለህ አስብ።—ምሳሌ 19:11
ሁላችንም ፍጹማን እንዳልሆንን እንዲሁም በኋላ ላይ የምንጸጸትበትን ነገር ልንናገር ወይም ልናደርግ እንደምንችል አስታውስ
አለመግባባቶችን ሳትውል ሳታድር ለመፍታት ጥረት አድርግ
“እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ”—ራስ ወዳድና በቀላሉ የምትበሳጩ አትሁኑ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ላሪ፣ ቶም ላቀረበለት ሐሳብ ምን ምላሽ ሰጠ?
ቶም በቀላሉ እንዳይበሳጭ የረዳው ምንድን ነው?
ቶም በገርነት ምላሽ መስጠቱ ምን ውጤት አስገኝቷል?
የሚያበሳጭ ሁኔታ ሲያጋጥመን ጉዳዩን በእርጋታ መያዛችን ጉባኤውን የሚጠቅመው እንዴት ነው?