ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዮሐንስ 18-19
ኢየሱስ ስለ እውነት መሥክሯል
ኢየሱስ ስለ አምላክ ዓላማዎች የሚገልጸውን እውነት በተመለከተ መሥክሯል
በንግግሩ፦ ስለ አምላክ መንግሥት የሚገልጸውን እውነት በቅንዓት አውጇል
በተግባሩ፦ አምላክ የተናገረው ትንቢት እውነት መሆኑን በአኗኗሩ አሳይቷል
እኛም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን ስለ እውነት እንመሠክራለን
በንግግራችን፦ ክርስቶስ ንጉሥ ሆኖ ስለሚያስተዳድርበት የአምላክ መንግሥት የሚገልጸውን ምሥራች በቅንዓት እንሰብካለን፤ ፌዝ ቢሰነዘርብንም እንኳ ይህን ማድረጋችንን እንቀጥላለን
በተግባራችን፦ የገለልተኝነት አቋማችንን በመጠበቅና ጥሩ ምግባር በማሳየት የኢየሱስን አገዛዝ እንደምንደግፍ እናሳያለን