የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb19 ነሐሴ ገጽ 3
  • ጊዜህን ይሖዋን ከሚወዱ ሰዎች ጋር አሳልፍ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጊዜህን ይሖዋን ከሚወዱ ሰዎች ጋር አሳልፍ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢዮአስ መጥፎ ጓደኝነት በመመሥረቱ ይሖዋን ተወ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ይሖዋን መፍራት የሚኖርብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ይሖዋ የድፍረት እርምጃን ይባርካል
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ዮዳሄ ያሳየው ድፍረት
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
mwb19 ነሐሴ ገጽ 3

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ጊዜህን ይሖዋን ከሚወዱ ሰዎች ጋር አሳልፍ

ጊዜያችንን ይሖዋን ከሚወዱ ሰዎች ጋር ማሳለፋችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? አብረናቸው የምንሆናቸው ሰዎች በጥሩም ሆነ በመጥፎ ተጽዕኖ ስለሚያደርጉብን ነው። (ምሳሌ 13:20) ንጉሥ ኢዮዓስን እንደ ምሳሌ እንውሰድ፤ ኢዮዓስ፣ ከሊቀ ካህኑ ከዮዳሄ ጋር በነበረበት ጊዜ ሁሉ “በይሖዋ ፊት መልካም የሆነውን ነገር [አድርጓል]።” (2ዜና 24:2) ዮዳሄ ከሞተ በኋላ ግን ኢዮዓስ መጥፎ ጓደኝነት ስለመሠረተ ይሖዋን ማገልገሉን ተወ።—2ዜና 24:17-19

በመጀመሪያው መቶ ዘመን፣ ሐዋርያው ጳውሎስ የክርስቲያን ጉባኤን ‘ከአንድ ትልቅ ቤት’ ጋር፣ የጉባኤውን አባላት ደግሞ በቤት ውስጥ ካሉ ‘ዕቃዎች’ ጋር አመሳስሏቸው ነበር። “ክብር ላለው ዓላማ የሚያገለግል . . . መሣሪያ” መሆን ከፈለግን ይሖዋን የሚያሳዝን ነገር ከሚያደርግ ማንኛውም ሰው ጋር አንቀራረብም፤ ይህ የቤተሰባችንን ወይም የጉባኤያችንን አባላትም ይጨምራል። (2ጢሞ 2:20, 21) ምንጊዜም ቢሆን ወዳጆቻችን ይሖዋን የሚወዱና እሱን እንድናገለግለው የሚያበረታቱን ሰዎች ሊሆኑ ይገባል።

ከመጥፎ ጓደኛ ራቁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • መጥፎ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩብን ሰዎች ጋር እንድንቀራረብ የሚያደርጉን አንዳንድ ሁኔታዎች የትኞቹ ናቸው?

  • በቪዲዮው ላይ የታዩት ሦስት ክርስቲያኖች መጥፎ ተጽዕኖ ከሚያሳድሩ ሰዎች ጋር ያላቸውን ቅርርብ ለማቋረጥ የረዳቸው ምንድን ነው?

  • ጓደኞችህን በጥበብ ለመምረጥ የሚረዱህ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የትኞቹ ናቸው?

ጆን ምግብ ቤት ውስጥ ለደንበኞቹ ወይን ሲቀዳ፤ ክርስቲን ማኅበራዊ ድረ ገጽ ስትቃኝ፤ ጄይደን በኢንተርኔት ጌም ሲጫወት፤ ጆን ከቤተሰቡ ጋር፣ ክርስቲን እና ጄይደን በጉባኤ ስብሰባ ላይ

“ክብር ላለው ዓላማ የሚያገለግል” መሣሪያ ነኝ?—2ጢሞ 2:21

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ