ክርስቲያናዊ ሕይወት
መጽሔቶችን መጠቀማችሁን ቀጥሉ
ከ2018 ወዲህ ለሕዝብ የሚበረከተው እያንዳንዱ መጽሔት አንድ ርዕሰ ጉዳይ ብቻ ይዞ መውጣት ጀምሯል። ከዚህ ጊዜ ወዲህ የወጡት እትሞች በሙሉ በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ ተካትተዋል። ስለዚህ አገልግሎት ላይ ልንጠቀምባቸው እንችላለን። በተጨማሪም ወደ አንድ ቦታ ስንሄድ ወይም ገበያ ስንወጣ ጥቂት መጽሔቶችን ልንይዝ እንችላለን። መጽሔቶቹ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጠናት የተዘጋጁ ባይሆኑም የሰዎችን መንፈሳዊ ፍላጎት ለመቀስቀስ ይረዳሉ።
ውይይት ከጀመራችሁ በኋላ አንድ ጥቅስ አንብቡና መጽሔት ላይ የወጣ የግለሰቡን ትኩረት የሚስብ አንድ ርዕሰ ጉዳይ አንሱለት። ለምሳሌ ያህል፣ ግለሰቡ ቤተሰብ ካለው አሊያም ሐዘን ወይም የሚያስጨንቅ ነገር አጋጥሞት ከሆነ “በቅርቡ ስለዚህ ጉዳይ የሚናገር አንድ ርዕስ አንብቤ ነበር። ባሳይህ ደስ ይለኛል” ልትሉት ትችላላችሁ። ፍላጎት እንዳለው ካስተዋላችሁ በመጀመሪያው ውይይታችሁ ጊዜም እንኳ ቢሆን የታተመውን መጽሔት ልትሰጡት ወይም የኤሌክትሮኒክ ቅጂውን ልትልኩለት ትችላላችሁ። ዋነኛው ግባችን ጽሑፍ ማበርከት ባይሆንም መጽሔቶቻችን፣ የተማሩትን ነገር በሥራ ላይ ለማዋል ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎችን ለማግኘት ይረዱናል።—ሥራ 13:48
2018
2019
2020
በክልላችሁ ያሉ ሰዎችን ትኩረት የሚስቡት የትኞቹ ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው?