የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 መጋቢት ገጽ 15
  • ጓደኞቻችሁን በጥበብ ምረጡ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጓደኞቻችሁን በጥበብ ምረጡ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለጊዜያችን የሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎችን ልብ እንድንል የቀረበ ፍቅራዊ ማሳሰቢያ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሟችሁ እንደ ፊንሐስ ዓይነት እርምጃ ትወስዳላችሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ጓደኞችህን በጥበብ ምረጥ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • አንድ ሰው ለውጥ ሊያመጣ ይችላል?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 መጋቢት ገጽ 15
ሞዓባውያን ሴቶች እስራኤላውያን ወንዶችን ሲጋብዟቸው።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ጓደኞቻችሁን በጥበብ ምረጡ

እስራኤላውያን በሞዓብ ሜዳ ሳሉ የደረሰባቸው ነገር ለክርስቲያኖች የማስጠንቀቂያ ምሳሌ ይሆናል። (1ቆሮ 10:6, 8, 11) የፆታ ብልግና ከሚፈጽሙትና ጣዖት አምላኪ ከሆኑት የሞዓብ ሴቶች ጋር የተቀራረቡት እስራኤላውያን ተታለው ከባድ ኃጢአት ፈጽመዋል። ይህም አስከፊ መዘዝ አስከትሏል። (ዘኁ 25:9) እኛም በዙሪያችን ያሉት ሰዎች ማለትም የሥራ ባልደረቦቻችን፣ አብረውን የሚማሩት ልጆች፣ ዘመዶቻችን እንዲሁም ሌሎች የምናውቃቸው ሰዎች ይሖዋን አያመልኩም። እንዲህ ካሉ ሰዎች ጋር የቅርብ ወዳጅነት መመሥረት ስላለው አደጋ ከዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ምን ትምህርት እናገኛለን?

ለጊዜያችን የሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎች—ተቀንጭቦ የተወሰደ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘ለጊዜያችን የሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎች—ተቀንጭቦ የተወሰደ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ዚምሪ ለያሚንና ለሌሎቹ ጓደኞቹ ስለ ሞዓባውያን ሴቶች ሲነግራቸው።

    ዚምሪ እና ሌሎቹ ሰዎች ለያሚን የተሳሳተ አስተሳሰብ የሚንጸባረቅበት ምን ነገር ነግረውታል?

  • ‘ለጊዜያችን የሚሆኑ የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎች—ተቀንጭቦ የተወሰደ’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ፊንሃስ ያሚንን ሲያስረዳው።

    ፊንሃስ፣ ያሚን ትክክለኛ አመለካከት እንዲኖረው የረዳው እንዴት ነው?

  • ለማያምኑ ሰዎች ወዳጃዊ ስሜት በማሳየትና የእነሱ ጓደኛ በመሆን መካከል ምን ልዩነት አለ?

  • በጉባኤ ውስጥም የቅርብ ጓደኞች በምንመርጥበት ጊዜ ጠንቃቆች መሆን ያለብን ለምንድን ነው?

  • ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በግል የማናውቃቸው ሰዎች በሚገኙባቸው የቻት ቡድኖች ውስጥ ከመግባት መቆጠብ ያለብን ለምንድን ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ