ክርስቲያናዊ ሕይወት
“ፍቅር . . . ሁሉን ተስፋ ያደርጋል”
ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር ወንድሞቻችን ጥሩ ውሳኔ እንደሚያደርጉ ተስፋ እንድናደርግ ያነሳሳናል። (1ቆሮ 13:4, 7) ለምሳሌ አንድ ወንድም ኃጢአት ሠርቶ ተግሣጽ ቢሰጠው እሱን ለመርዳት ለሚደረገው ጥረት በጎ ምላሽ እንደሚሰጥ ተስፋ እናደርጋለን። ደካማ እምነት ያላቸውን ሰዎች በትዕግሥት እንይዛቸዋለን፤ እንዲሁም እነሱን ለመርዳት ጥረት እናደርጋለን። (ሮም 15:1) አንድ ሰው ጉባኤውን ቢተው ደግሞ አንድ ቀን እንደሚመለስ ተስፋ እናደርጋለን።—ሉቃስ 15:17, 18
ፍቅር የሚያደርጋቸውና የማያደርጋቸው ነገሮች—ሁሉን ተስፋ ያደርጋል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
አበኔር ምን ዓይነት ለውጥ አደረገ?
ዳዊት ለአበኔር ጥያቄ ምን ምላሽ ሰጠ? ኢዮዓብስ?
ወንድሞቻችን ጥሩ ውሳኔ እንደሚያደርጉ ተስፋ ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?