የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መጋቢት 26 የሚጀምር ሳምንት
    የመንግሥት አገልግሎት—2012 | መጋቢት
    • መጋቢት 26 የሚጀምር ሳምንት

      መጋቢት 26 የሚጀምር ሳምንት

      መዝሙር 47 እና ጸሎት

      □ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦

      fy ምዕ. 7 ከአን. 24-27 (25 ደቂቃ)

      □ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦

      የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ኤርምያስ 12-16 (10 ደቂቃ)

      ቁ. 1፦ ኤርምያስ 13:1-14 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

      ቁ. 2፦ ከጌታ ራት መካፈል ያለባቸው እነማን ናቸው?​—rs ገጽ 267 አን. 2, 3 (5 ደቂቃ)

      ቁ. 3፦ የመታሰቢያው በዓል መከበር የሚኖርበት በየስንት ጊዜው ነው? የሚከበረውስ መቼ ነው?​—rs ገጽ 268 አን. 2, 3 (5 ደቂቃ)

      □ የአገልግሎት ስብሰባ፦

      መዝሙር 50

      5 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። ጉባኤው የመታሰቢያው በዓል የመጋበዣ ወረቀት ያልተሰራጨባቸው ስንት ክልሎች እንደቀሩት ተናገር።

      10 ደቂቃ፦ እንግዳ ተቀባይ መሆንን አትርሱ። (ዕብ. 13:1, 2) በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው ለመታሰቢያው በዓል ያደረጋቸውን ዝግጅቶች ተናገር። በበዓሉ ላይ ለሚገኙ እንግዶችም ሆነ ለቀዘቀዙ አስፋፊዎች የእንግዳ ተቀባይነት መንፈስ ማሳየት የምንችልባቸውን አንዳንድ መንገዶች ጥቀስ። ሁለት ክፍሎች ያሉት አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። የመጀመሪያው ክፍል አንድ አስፋፊ መጋበዣ ወረቀት ደርሶት ለመጣ ሰው ከፕሮግራሙ በፊት ጥሩ አቀባበል ሲያደርግለት የሚያሳይ ነው። ሁለተኛው ደግሞ አስፋፊው፣ ከፕሮግራሙ በኋላ የግለሰቡን ፍላጎት ይበልጥ ለማነሳሳት የሚያስችል ጥረት ለማድረግ ቀጠሮ ሲይዝ የሚያሳይ ነው።

      20 ደቂቃ፦ “አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በመጀመሪያውና በመጨረሻው አንቀጾች ውስጥ ያሉትን ሐሳቦች መግቢያና መደምደሚያ አድርገህ ተጠቀምባቸው። ይህን ፊልም በማየታቸው የተጠቀሙት እንዴት እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ። ፊልሙን በአገልግሎታችን መጠቀም የምንችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩ።

      መዝሙር 15 እና ጸሎት

  • አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉ
    የመንግሥት አገልግሎት—2012 | መጋቢት
    • አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉ

      ብዙ ሰዎች ተፈጥሮን ያደንቃሉ። ሆኖም ተፈጥሮ የታላቁ ፈጣሪ አስተሳሰብና ስሜት ነጸብራቅ እንደሆነ የሚረዱት በጣም ጥቂት ናቸው። (ሮም 1:20) ከረጅም ዘመናት በፊት የኖረው ዳዊት፣ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፈውን ቃሉን በማንበብ ስለ ይሖዋ ማወቅ ችሎ ነበር። በተጨማሪም ዳዊት የፍጥረት ሥራዎችን ‘መመልከቱም’ ወደ አምላክ እንዲቀርብ ረድቶታል። (መዝ. 8:3, 4) በተመሳሳይም ዎንደርስ ኦቭ ክርኤሽን ሪቪል ጎድስ ግሎሪ (አስደናቂ የፍጥረት ሥራዎች የአምላክን ክብር ይገልጣሉ) የተባለውን ቪዲዮ መመልከታችን እኛም ሆነ ልጆቻችን እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎቻችን ከይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች አንዳንዶቹን ጠለቅ ብለን እንድንመረምር ብሎም ታላቁ ፈጣሪያችን ያሉትን ባሕርያት እንድናስተውል ይረዳናል፤ ይህ ደግሞ ወደ እሱ ይበልጥ እንድንቀርብ ያስችለናል። ፊልሙን ከተመለከታችሁ በኋላ ለሚከተሉት ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ሞክሩ።

      (1) ግዑዙ አጽናፈ ዓለም ያለውን ስፋት እንዲሁም የተደራጀበት መንገድ ለይሖዋ ያለህ አድናቆት እንዲጨምር የሚያደርገው እንዴት ነው? (ኢሳ. 40:26) (2) ስለ ውኃ ጠለቅ ብለን ስንመረምር አምላክን በተመለከተ ምን እንማራለን? (ራእይ 14:7) (3) የምድራችን ስፋት እና ከፀሐይ ያላት ርቀት የይሖዋን ጥበብ የሚያሳየው እንዴት ነው? (4) ጨረቃ ምን ጥቅም አላት? (መዝ. 89:37) (5) ይሖዋ፣ የሰው ልጆችን በሕይወት እንዲደሰቱ አድርጎ የፈጠራቸው እንዴት ነው? (6) ዲ ኤን ኤ ምንድን ነው? (መዝ. 139:16) (7) በምድር ላይ ካሉት የይሖዋ የፍጥረት ሥራዎች ሁሉ የሰው ልጆች የሚለዩት እንዴት ነው? (ዘፍ. 1:26) (8) በአዲሱ ዓለም ውስጥ ለማግኘት የምትጓጓው ነገር ምንድን ነው?

      ተጨማሪ ክፍሎች፦ (9) አንድ ነገር ቀለም እንዲኖረው የሚያደርገው ምንድን ነው? (10) ውኃ የስበትን ኃይል ተቋቁሞ ወደ ዛፎች ጫፍ መድረስ የሚችለው እንዴት ነው? (11) ውኃ በሰውነታችን ውስጥ ምን ተግባር ያከናውናል? (12) ሕይወት ያላቸው ነገሮች እርስ በርስ እንደሚረዳዱ የሚያሳዩ ምሳሌዎችን ጥቀስ። (13) አንዳንድ ፍጥረታት ከሌሎች ፍጥረታት ጋር ዝምድና እንዲፈጥሩ የሚያደርጋቸው ነገር ምንድን ነው? (14) “ወርቃማ ማዕዘን” (ጎልደን አንግል) የሚባለው ነገር ምንድን ነው? ይህ ነገር በአንዳንድ ፍጥረታት ላይ የሚታየውስ እንዴት ነው?

      የይሖዋን የእጅ ሥራዎች “ልብ ብላችሁ ተመልከቱ”፦ ኢየሱስ ‘የሰማይ ወፎችን’ እና ‘የሜዳ አበቦችን’ ልብ ብለን እንድንመለከት አበረታቶናል። (ማቴ. 6:26, 28) እንዲህ ማድረጋችን በይሖዋ ላይ ያለን እምነት እንዲጠናከር፣ በፈጣሪ እንድንተማመን እንዲሁም ለጥበቡ፣ ለማዳን ኃይሉና ለፍቅሩ ያለን አድናቆት ከፍ እንዲል ይረዳናል። በመሆኑም ሰዎች ለሚሠሯቸው ነገሮች የበለጠ ትኩረት ከመስጠት ይልቅ አስደናቂ የሆኑትን የይሖዋን የፍጥረት ሥራዎች ለመመልከትና እነዚህ ፍጥረታት ስለ ታላቁ አምላካችን ስለሚናገሩት ነገር በጥሞና ለማሰብ ጊዜ መመደብ ይኖርብናል።​—መዝ. 19:1

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ