የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lmd ትምህርት 2
  • ተፈጥሯዊ አነጋገር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተፈጥሯዊ አነጋገር
  • ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ፊልጶስ ምን አድርጓል?
  • ከፊልጶስ ምን እንማራለን?
  • ፊልጶስን ምሰል
  • ፊልጶስ ቀናተኛ ወንጌላዊ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር​—ከሰዎች ጋር ውይይት በመጀመር መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • ስለ ሰዎች ማሰብ
    ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
  • “ስለ ኢየሱስ የሚገልጸውን ምሥራች” ማወጅ
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
ለተጨማሪ መረጃ
ሰዎችን ውደዱ—ደቀ መዛሙርት አድርጉ
lmd ትምህርት 2

ውይይት መጀመር

ወንጌላዊው ፊልጶስ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጋር ሲነጋገር፤ ሰውየው ሠረገላው ላይ ሆኖ ጥቅልል እያነበበ ነው።

ሥራ 8:30, 31

ምዕራፍ 2

ተፈጥሯዊ አነጋገር

መሠረታዊ ሥርዓት፦ “በትክክለኛው ጊዜ የተነገረ ቃል . . . ምንኛ መልካም ነው!”—ምሳሌ 15:23

ፊልጶስ ምን አድርጓል?

ወንጌላዊው ፊልጶስ ከአንድ ኢትዮጵያዊ ጋር ሲነጋገር፤ ሰውየው ሠረገላው ላይ ሆኖ ጥቅልል እያነበበ ነው።

ቪዲዮ፦ ፊልጶስ ለኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ሰበከ

1. ቪዲዮውን ተመልከት፤ ወይም የሐዋርያት ሥራ 8:30, 31ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

  1. ሀ. ፊልጶስ ውይይቱን የጀመረው እንዴት ነው?

  2. ለ. ውይይቱን የጀመረበትና እውነትን ለዚህ ሰው ያስተዋወቀበት መንገድ የጭውውት ለዛውን የጠበቀ ነው የምንለው ለምንድን ነው?

ከፊልጶስ ምን እንማራለን?

2. ውይይቱን ለመምራት ከመሞከር ይልቅ ጭውውቱ ራሱ እንዲመራን ከፈቀድን የምናነጋግረው ሰው ዘና ይላል፤ መልእክቱን ለመስማትም ፈቃደኛ ሊሆን ይችላል።

ፊልጶስን ምሰል

3. ጥሩ አድርገህ ታዘብ። በሰውየው የፊት ገጽታ ላይ የሚነበበው ነገርና አኳኋኑ ስለ እሱ ብዙ የሚነግረን ነገር አለ። ግለሰቡ ሊያነጋግርህ የሚፈልግ ይመስላል? ከሆነ የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለማስተዋወቅ በቀላሉ ጥያቄ ልታነሳለት ትችላለህ፤ ለምሳሌ “አምላክ፣ ስም እንዳለው ሰምተህ ታውቃለህ?” ልትለው ትችላለህ። ግለሰቡ ሊያዋራህ የማይፈልግ ከሆነ አታስገድደው።

4. ትዕግሥተኛ ሁን። ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ለማንሳት አትቸኩል። በውይይቱ ላይ ይህን ማንሳት ተስማሚ የሚሆንበትን ጊዜ ጠብቅ። አንዳንድ ጊዜ ይህን ለማድረግ የሚያስችል አመቺ አጋጣሚ የምታገኘው ግለሰቡን በሌላ ጊዜ ስታገኘው ሊሆን ይችላል።

5. እንደአስፈላጊነቱ ለውጥ አድርግ። ውይይታችሁ ወዳላሰብከው አቅጣጫ ሊያመራ ይችላል። ስለዚህ ለግለሰቡ ሁኔታ የሚስማማ ሐሳብ ለማንሳት ፈቃደኛ ሁን፤ ከተዘጋጀኸው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ የተለየ ቢሆንም እንኳ እንደአስፈላጊነቱ ለውጥ ማድረግህ ጠቃሚ ነው።

ተጨማሪ ጥቅሶች

መክ. 3:1, 7፤ 1 ቆሮ. 9:22፤ 2 ቆሮ. 2:17፤ ቆላ. 4:6

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ