በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ከሰዎች ጋር ውይይት በመጀመር መደበኛ ባልሆነ መንገድ መመሥከር
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል አብዛኛውን ጊዜ ሰዎችን ቤታቸው አናገኛቸውም። ይሁን እንጂ እነዚህን ሰዎች የሕዝብ መጓጓዣ ስንጠቀም፣ የሐኪም ቤት ወረፋ ስንጠብቅ፣ በትምህርት ቤት ወይም በሥራ ቦታ የዕረፍት ሰዓት ላይ በምንሆንበት ጊዜና በሌሎች አጋጣሚዎች ልናገኛቸው እንችላለን። ይሖዋ፣ ሁሉም ሰው የመንግሥቱን መልእክት እንዲሰማ ይፈልጋል። (1 ጢሞ. 2:3, 4) ይሁንና በእነዚህ ወቅቶች ምሥክርነት ለመስጠት ከፈለግን እኛ ቅድሚያውን በመውሰድ ውይይት መጀመር ይኖርብናል።
በዚህ ወር እንዲህ ለማድረግ ሞክሩ፦
መደበኛ ባልሆነ መንገድ ምሥክርነት የመስጠት ግብ በመያዝ በየሳምንቱ ቢያንስ ከአንድ ሰው ጋር ውይይት ለመጀመር ጥረት አድርጉ።