የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 11/02 ገጽ 7
  • የጥያቄ ሣጥን

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የጥያቄ ሣጥን
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጉባኤ ያስፈልገናል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • ምሥራቹን የምንሰብክባቸው መንገዶች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • ጉባኤው እየተጠናከረ ይሂድ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • የመኖሪያ ቦታ ልትቀይር ነውን?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1999
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 11/02 ገጽ 7

የጥያቄ ሣጥን

◼ በክልላችን ውስጥ በሚገኝ ጉባኤ መሰብሰባችን ምን ጥቅሞች አሉት?

በጉባኤ ስብሰባዎች አማካኝነት ‘ለፍቅርና ለመልካም ሥራ የሚያነቃቁ’ ማበረታቻዎች እናገኛለን። (ዕብ. 10:24, 25) በጉባኤው በኩል እውነትን እንማራለን እንዲሁም ደቀ መዛሙርት የማድረግ ተልዕኳችንን ለመፈጸም የታጠቅን እንሆናለን። (ማቴ. 28:19, 20) የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በታማኝነት ለመቋቋም የሚያስችለን ማበረታቻ ከማግኘታችንም በላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ የሚሄዱትን ተጽዕኖዎችና የሚያስጨንቁ ሁኔታዎች መቋቋም እንድንችል የሚረዱን አፍቃሪ የሆኑ የበላይ ተመልካቾችም አሉልን። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ጉባኤ ለመንፈሳዊ ደህንነታችን በጣም አስፈላጊ ነው። ይሁን እንጂ በክልላችን ውስጥ በሚገኘው ጉባኤ መሰብሰባችን ምን ጥቅሞች አሉት?

የግለሰቦች ሁኔታ የሚለያይ ከመሆኑም በላይ እንደ ሰብዓዊ ሥራ፣ የማያምን የትዳር ጓደኛ እና የመጓጓዣ ሁኔታ ያሉት ነገሮች በየትኛው ጉባኤ መሰብሰብ እንደሚኖርብን በምናደርገው ውሳኔ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ። ያም ሆኖ ግን አንድ ሰው በክልሉ ውስጥ ባለው ጉባኤ ሲሰበሰብ የሚያገኛቸው ጉልህ ጥቅሞች አሉ። ድንገተኛ ሁኔታ ቢፈጠር ሽማግሌዎች ሁሉንም አስፋፊዎች በቶሎ ማግኘት ይችላሉ። ቀደም ባሉት ዓመታት የወጡ የጥያቄ ሣጥኖች አንድ አስፋፊ በክልሉ ውስጥ ባለው ጉባኤ መሰብሰቡ የሚያስገኛቸውን ሌሎች በርካታ ጥቅሞች ገልጸዋል።—ግንቦት 1991፣ መጋቢት 1976 እና ጥር 1967።

በአጠቃላይ ሲታይ በአቅራቢያችን በሚገኘው ጉባኤ መሰብሰብ ቀደም ብለን በመድረስ ከሌሎች ጋር ለመጫወት፣ አስፈላጊ የሆኑ ጉዳዮችን ለማከናወንና በመግቢያው መዝሙርና ጸሎት ላይ ለመገኘት ስለሚያስችለን ይበልጥ ተስማሚ ነው። ፍላጎት ያሳዩ አዳዲስ ሰዎች በአቅራቢያችን የሚኖሩ ከሆነ እነሱን ለማግኘት፣ ከእነርሱ ጋር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማካሄድና ለእነሱ አመቺ ወደሆነው ስብሰባ ይዘናቸው ለመሄድ ይበልጥ ቀላል ይሆንልናል።

የቤተሰብ ራሶች ለቤተሰባቸው መንፈሳዊና አካላዊ ደህንነት ተስማሚ የሆነ ውሳኔ ለማድረግ እንዲችሉ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ ሁኔታዎችን በሙሉ በጥንቃቄ በመመርመር በጸሎት እንደሚያስቡበት እንተማመናለን።—1 ጢሞ. 5:8

◼ የጉባኤ ስብሰባዎች የሚካሄዱበትን ቀንና ሰዓት በመወሰን ረገድ የትኞቹን ነጥቦች ግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል?

የጉባኤ ስብሰባ መቼ መደረግ አለበት የሚለው ጉዳይ ራሱን የቻለ ደንብ የለውም። ይሁንና አንድ ጉባኤ ስብሰባ የሚያካሂድበትን ቀንና ሰዓት ከመወሰኑ በፊት ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ ሊያስብባቸው የሚገቡ ነገሮች አሉ። ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው:- በመንግሥት አዳራሹ የሚጠቀሙት ስንት ጉባኤዎች ናቸው? ከዚህ አኳያ የስብሰባውን ቀንና ሰዓት ለመወሰን ምን አማራጮች አሉ? ለአዲሶች ይበልጥ ተስማሚ የሚሆነው የትኛው ቀንና ሰዓት ነው? ለሠራተኞችና ለተማሪዎችስ? ስብሰባው በዚህ ቀን ወይም ሰዓት ላይ እንዲሆን የምንፈልገው ለምንድን ነው? የስብሰባው ሰዓት ለሁሉም የጉባኤው አባላት አመቺ እንዲሆን ስንል አንዳንድ የግል ምርጫዎቻችንን መሥዋዕት ለማድረግ ፈቃደኞች ነንን?

ሐዋርያው ጳውሎስ የሰጠውን ምክር ልብ በሉ:- “ሁሉ ተፈቅዶልኛል፣ ሁሉ ግን የሚጠቅም አይደለም፤ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፣ ነገር ግን ሁሉ የሚያንጽ አይደለም። እያንዳንዱ የባልንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ።” (1 ቆሮ. 10:23, 24) ከዚህ መመሪያ ጋር በሚስማማ መልኩ ሽማግሌዎች ጉባኤው ውሳኔ እንዲያደርግበት የሚያቀርቡትን የስብሰባ ቀንና ሰዓት በሚመርጡበት ጊዜ እንደሚከተለው እያሉ ራሳቸውን ሊጠይቁ ይችላሉ:- ይህ ሰዓት የጉባኤው አባላትም ሆኑ አዲሶች በስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በመንፈሳዊ እንዲጠቀሙ የሚያስችል ነውን? ይህ ፕሮግራም በእርግጥ መንግሥቱን እንድናስቀድም ያስችለናል ወይስ የመንግሥቱ ጉዳዮች ቸል እንዲባሉ ያደርጋል?

እያንዳንዱ ጉባኤ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙትን ሁኔታዎችና ሽማግሌዎች የሚሰጡትን ሐሳብ ግምት ውስጥ በማስገባት ተስማሚ ሆኖ ያገኘውን የስብሰባ ሰዓት መምረጥ ይችላል። አገልግሎታችን የተባለው መጽሐፍ በገጽ 62 አንቀጽ 1 ላይ እንደሚለው ጉባኤው ‘ለአብዛኞቹ የጉባኤው አባላት ተስማሚ የሆነ የስብሰባ ሰዓት መምረጥ ይኖርበታል።’ ፕሮግራማቸው ከስብሰባው ሰዓት ጋር የሚጋጭባቸው ግለሰቦች መንፈሳዊ ፍላጎታቸውን በማስቀደም ማስተካከያ ያደርጋሉ። በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ በርካታ ጉባኤዎች የሚሰበሰቡ ከሆነ ጉባኤዎቹ ፍቅራዊና ክርስቲያናዊ በሆነ መንገድ የስብሰባ ሰዓታቸውን ያመቻቻሉ።

የጉባኤ የመጽሐፍ ጥናት የሚደረግበት ሰዓት በመጽሐፍ ጥናት ቡድኑ ውስጥ ባሉት ሰዎች ሁኔታ ላይ የተመካ ይሆናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ