የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwhf ርዕስ 18
  • አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ
  • ለቤተሰብ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በአካል አብረው ሆነው በስሜት መራራቅ—ለምን?
  • ምን ማድረግ ትችላላችሁ?
  • መወያያ ሐሳብ
  • ቴክኖሎጂ የሚያሳድረው ተጽዕኖ—​በትዳርህ ላይ
    ንቁ!—2021
  • ሥራን ሥራ ቦታ መተው
    ለቤተሰብ
  • ፍቺ በስተርጅና—መከላከያው ምንድን ነው?
    ለቤተሰብ
  • ቴክኖሎጂ ሕይወታችንን እንዳይቆጣጠረው ማድረግ
    ለቤተሰብ
ለተጨማሪ መረጃ
ለቤተሰብ
ijwhf ርዕስ 18
አንድ ባልና ሚስት በደስታ አብረው ምግብ ሲያዘጋጁ።

ለቤተሰብ | ትዳር

አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ

በርካታ ባለትዳሮች፣ በአካል አብረው ሆነውም እንኳ እርስ በርስ ብዙም እንደማይነጋገሩ ይስተዋላል። ምክንያቱ ምንድን ነው?

  • በአካል አብረው ሆነው በስሜት መራራቅ—ለምን?

  • ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • ባለትዳሮች ምን ይላሉ?

  • መወያያ ሐሳብ

በአካል አብረው ሆነው በስሜት መራራቅ—ለምን?

  • ድካም

    “አብረን የምንሆንበት ጊዜ ስናገኝ፣ ወይ እኔ ይደክመኛል ወይ ባለቤቴ ይደክመዋል። እኔ ደግሞ ሲደክመኝ ንጭንጭ ያደርገኛል። ስለዚህ ዝም ብለን ቲቪያችንን ብናይ እንመርጣለን።”—አና

  • ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች

    “ማኅበራዊ ድረ ገጾችና በኢንተርኔት የሚቀርቡ መዝናኛዎች ጊዜያችሁን ሊያሟጥጡባችሁ ይችላሉ። ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር አንድም ቃል ሳትነጋገሩ ለሰዓታት እዚያ ላይ አፍጥጣችሁ ልትቆዩ ትችላላችሁ። አንድ ክፍል ውስጥ ቁጭ ብላችሁ አንድ ላይ ያልሆናችሁ ያህል ነው።”—ካትሪን

  • የፍላጎት መለያየት

    “ባለቤቴ ከሥራ ሲመጣ፣ በአብዛኛው በትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች ይጠመዳል። ቀኑን ሙሉ ሲለፋ ስለሚውል የራሱ ጊዜ ማግኘት ያስፈልገዋል። እኔ ግን አብረን የምናሳልፈው ተጨማሪ ጊዜ ብናገኝ ደስ ይለኛል።”—ጄን

  • ሥራ

    “ቴክኖሎጂ፣ በሥራና በቤተሰብ ሕይወት መካከል ያለው ልዩነት እንዲደበዝዝ አድርጓል። ከባለቤቴ ጋር ላሳልፍ የምችለውን ጊዜ በአብዛኛው የሥራ ኢ-ሜይሎችንና መልእክቶችን በመመለስ አጠፋለሁ።”—ማርክ

ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

  • አብሮ ጊዜ ማሳለፍ፣ ስትችሉ ብቻ የምታደርጉት ሳይሆን መደረግ ያለበት ነገር እንደሆነ አስቡ።

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ለይታችሁ [እወቁ።]”—ፊልጵስዩስ 1:10

    ሊታሰብበት የሚገባ፦ የምታደርጉት ነገር፣ ከሥራችሁ ወይም ከትርፍ ጊዜ ማሳለፊያችሁ ትዳራችሁ እንደሚበልጥባችሁ ያሳያል? ለትዳር ጓደኛችሁ ትኩረት የምትሰጡት ጊዜ ሲተርፋችሁ ብቻ ነው?

    ጠቃሚ ምክር፦ ሁኔታዎች በራሳቸው እስኪመቻቹ አትጠብቁ። ትኩረታችሁ ሳይከፋፈል ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ጊዜ የምታሳልፉበትን ፕሮግራም አውጡ።

    “ባለቤቴ፣ እኔና እሱ ብቻ አብረን ጊዜ ማሳለፍ የምንችልበትን ሁኔታ ሲያመቻች ደስ ይለኛል። እንደሚወደኝና ከእኔ ጋር መሆን እንደሚያስደስተው እንዲሰማኝ ያደርጋል። ይህ ደግሞ ይበልጥ እንድወደው ያደርገኛል።”—አና

  • ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቻችሁን ተወት ማድረግን ተማሩ።

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ለሁሉም ነገር ጊዜ አለው።”—መክብብ 3:1

    ሊታሰብበት የሚገባ፦ ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ጊዜ ስታሳልፉ፣ በስልካችሁ የሚላኩላችሁ መልእክቶች ብዙ ጊዜ ትኩረታችሁን ይከፋፍሉታል?

    ጠቃሚ ምክር፦ በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ አብራችሁ ለመመገብ ጥረት አድርጉ፤ በዚህ ጊዜ ስልኮቻችሁን ሌላ ክፍል አስቀምጧቸው። አብሮ መመገብ፣ ስለ ውሏችሁ ለማውራት ጥሩ አጋጣሚ ይሰጣችኋል።

  • ከተቻለ፣ አብራችሁ ገበያ ውጡ ወይም የቤት ውስጥ ሥራዎችን አከናውኑ።

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “አንድ ከመሆን ሁለት መሆን ይሻላል፤ ምክንያቱም ሁለት ሆነው የሚያከናውኑት ሥራ የተሻለ ጥቅም ያስገኝላቸዋል።”—መክብብ 4:9 የግርጌ ማስታወሻ

    ሊታሰብበት የሚገባ፦ ለቤተሰቡ የሚያስፈልገውን ነገር ለመግዛት ብዙውን ጊዜ ብቻችሁን ትወጣላችሁ?

    ጠቃሚ ምክር፦ ሁለት ሰው የማይጠይቁ ሥራዎችንም እንኳ አብራችሁ ሥሩ እንዲሁም ተጋገዙ።

    “ገበያ መውጣት፣ ዕቃ ማጠብ፣ ልብስ ማጣጠፍ፣ ግቢ ማስተካከል—እነዚህን ነገሮች እንደ ሥራ ብቻ ከመመልከት ይልቅ አብራችሁ ጊዜ ለማሳለፍ የሚያስችሏችሁ አጋጣሚዎች አድርጋችሁ ማየት ጥሩ ነው።”—ኒና

  • አንዳችሁ ከሌላው በምትጠብቁት ነገር ረገድ ምክንያታዊ ሁኑ።

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ምክንያታዊነታችሁ . . . የታወቀ ይሁን።”—ፊልጵስዩስ 4:5

    ሊታሰብበት የሚገባ፦ ከትዳር ጓደኛችሁ በምትጠብቁት ነገር ረገድ ምክንያታዊ መሆናችሁን የምታሳዩት እንዴት ነው?

    ጠቃሚ ምክር፦ በግልጽ ተነጋገሩ፤ የትዳር ጓደኛችሁ የሚያስፈልገውን ነገር ለመረዳት ጥረት አድርጉ። ከዚያም ሁለታችሁንም የሚያስደስትና የሚያስማማ ውሳኔ ላይ ድረሱ።

    “ባለቤቴ ምንም አይደክመውም፤ እኔ ደግሞ በጤንነቴ የተነሳ ብዙም አቅም የለኝም። ስለዚህ ብዙ ጊዜ ባለቤቴን ‘አንተ ወጣ ብለህ ዘና ማለት ትችላለህ፤ እኔ እዚሁ እጠብቅሃለሁ’ እለዋለሁ። እኔ ቤት ቁጭ ስል የሚያስፈልገኝን እረፍት አገኛለሁ፤ እሱ ደግሞ ወጣ ብሎ ስፖርት መሥራት ያስፈልገዋል። ሁለታችንም የሚያስፈልገንን ነገር ማድረጋችን ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል።”—ዳንዬላ

    ባለትዳሮች ምን ይላሉ?

    ጄሚን እና ኬንድራ።

    “አብሮ መመገብ፣ ቁም ነገር የምታወሩበት ሌላው ቀርቶ የምትቀላለዱበት ጥሩ አጋጣሚ ይሰጣችኋል። ባለትዳሮች እንዲሁ የደባል ኑሮ ከመኖር ይልቅ አንዳቸው የሌላው ሕይወት ክፍል እንዲሆኑ ይረዳል።”—ጄሚን እና ባለቤቱ ኬንድራ

    ሞኒካ እና ባለቤቷ ሾውን።

    “መብላታችን አይቀርም፤ ታዲያ ለምን አብረን አንመገብም? ስለ ልጅነቴ ካሉኝ አስደሳች ትዝታዎች አንዱ፣ ከወላጆቼ ጋር አብረን ስንመገብ እናሳልፍ የነበረው ጊዜ ነው። አሁንም በምግብ ሰዓት ከባለቤቴ ጋር አብሬ መሆኔ፣ ለወደፊት ብዙ ጥሩ ትዝታዎች እንዲኖሩኝ ያደርጋል።”—ሞኒካ እና ባለቤቷ ሾውን

መወያያ ሐሳብ

በመጀመሪያ፣ ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች በየግላችሁ ለመመለስ ሞክሩ። ከዚያም መልሳችሁን ተወያዩበት።

  • አብሮ ጊዜ ከማሳለፍ አንጻር ምን ያህል ተሳክቶልናል ብላችሁ ታስባላችሁ?

  • አብሮ ጊዜ ለማሳለፍ ጥረት በማድረግ ረገድ የትዳር ጓደኛችሁ የሚመሰገንበት ነገር አለ?

  • በዚህ ረገድ ምን ቢያሻሽል ደስ ይላችኋል?

  • ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች፣ የትዳር ጓደኛችሁ ሲናገር ሙሉ ትኩረት ሰጥታችሁ እንዳታዳምጡ እንቅፋት የሚሆኑባችሁ ጊዜ አለ?

  • ሁለታችሁም አንዳችሁ ከሌላው በምትጠብቁት ነገር ረገድ ምክንያታዊ መሆናችሁን ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?

  • ሁለታችሁም አንዳችሁ ለሌላው ያልተከፋፈለ ትኩረት ለመስጠት በዚህ ሳምንት ምን ማስተካከያ ማድረግ ትችላላችሁ?

ክለሳ፦ አብራችሁ የምታሳልፉትን ጊዜ በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት

  • አብሮ ጊዜ ማሳለፍ፣ ስትችሉ ብቻ የምታደርጉት ሳይሆን መደረግ ያለበት ነገር እንደሆነ አስቡ።

  • ኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎቻችሁን ተወት ማድረግን ተማሩ።

  • ከተቻለ፣ አብራችሁ ገበያ ውጡ ወይም የቤት ውስጥ ሥራዎችን አከናውኑ።

  • አንዳችሁ ከሌላው በምትጠብቁት ነገር ረገድ ምክንያታዊ ሁኑ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ