የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwhf ርዕስ 30
  • ፖርኖግራፊ ትዳራችሁን ሊያናጋው ይችላል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ፖርኖግራፊ ትዳራችሁን ሊያናጋው ይችላል
  • ለቤተሰብ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ማወቅ የሚኖርብህ ነገር
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • የትዳር አጋርሽ ፖርኖግራፊ የሚመለከት ከሆነ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ወሲባዊ ሥዕሎችንና ፊልሞችን ከመመልከት መራቅ የምችለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2007
  • ፖርኖግራፊ መመልከት የሌለብህ ለምንድን ነው?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • የብልግና ሥዕሎች የሚያስከትሉት ጉዳት
    ንቁ!—2003
ለተጨማሪ መረጃ
ለቤተሰብ
ijwhf ርዕስ 30
አንድ ባል ተስፋ ቆርጦ አንገቱን አቀርቅሯል፤ ሚስቱ ደግሞ በሐዘን ወደ ውጭ በመስኮት እየተመለከተች ነው።

ለቤተሰብ | ትዳር

ፖርኖግራፊ ትዳራችሁን ሊያናጋው ይችላል

ባለቤቱ ሚስጥሩን አወቀችበት። አጥብቆ ይቅርታ ጠየቃት። እንደሚያቆም ቃል ገባላት፤ ደግሞም ለተወሰነ ጊዜ አቆመ። ከዚያ ግን አገረሸበት። አሁንም ታሪክ ራሱን ደገመ።

አንተስ እንዲህ ያለ ሁኔታ አጋጥሞሃል? ከሆነ የፖርኖግራፊ ሱስህ ባለቤትህን የሚጎዳት እንዴት እንደሆነ እንዲሁም ይህን ሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማሸነፍ የምትችለው እንዴት እንደሆነ መማር ይኖርብሃል።a

በዚህ ርዕስ ውስጥ

  • ማወቅ የሚኖርብህ ነገር

  • ምን ማድረግ ትችላለህ?

  • ባለቤትሽ ፖርኖግራፊ የሚመለከት ከሆነ

ማወቅ የሚኖርብህ ነገር

ፖርኖግራፊ ትዳርን ሊያናጋ ይችላል። በባለትዳሮች መካከል መቃቃር እንዲፈጠር እንዲሁም ሚስትየዋ ባሏን ማመን እንዲከብዳት ሊያደርግ ይችላል።b

ፖርኖግራፊ የሚመለከት ባል ያላት ሴት የሚከተሉት ስሜቶች ሊፈጠሩባት ይችላሉ፦

  • መከዳት። ሣራ የተባለች አንዲት ባለትዳር “ባለቤቴ በተደጋጋሚ ምንዝር የፈጸመ ያህል ሆኖ ተሰማኝ” ብላለች።

  • ለራስ አክብሮት ማጣት። አንዲት ባለትዳር የባሏ የፖርኖግራፊ ሱስ ‘አስቀያሚ እንደሆነች እንዲሰማትና እንድትሸማቀቅ’ እንዳደረጋት ተናግራለች።

  • አለመተማመን። ሄለን የተባለች አንዲት ባለትዳር “ባለቤቴ የሚያደርገውን እያንዳንዱን ነገር በጥርጣሬ ዓይን ነው የማየው” ብላለች።

  • ጭንቀት። ካትሪን የተባለች አንዲት ባለትዳር “ስለ ባለቤቴ የፖርኖግራፊ ሱስ መብሰልሰሌ መላ ሕይወቴን ተቆጣጠረው” ብላለች።

ሊታሰብበት የሚገባው ነጥብ፦ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ባል ሚስቱን መውደድ እንዳለበት ይናገራል። (ኤፌሶን 5:25) ታዲያ አንድ ባል፣ ሚስቱ ከላይ የተጠቀሱት ስሜቶች እንዲሰሟት ካደረገ በእርግጥ ይወዳታል ሊባል ይችላል?

ምን ማድረግ ትችላለህ?

የፖርኖግራፊ ሱስን ማሸነፍ ቀላል አይደለም። ስቴሲ የተባለች አንዲት ባለትዳር እንዲህ ብላለች፦ “ባለቤቴ የሲጋራ፣ የማሪዋና እና የአልኮል ሱሱን ማሸነፍ ችሏል። የፖርኖግራፊ ሱሱ ግን አሁንም ድረስ ያታግለዋል።”

የአንተም ሁኔታ እንደዚህ ከሆነ የሚከተሉት ምክሮች ይህን ሱስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማሸነፍ ይረዱሃል።

  • ፖርኖግራፊ መጥፎ የሆነው ለምን እንደሆነ ተረዳ። ፖርኖግራፊ ሰዎች የራስ ወዳድነት ምኞታቸውን ለማርካት እንዲነሳሱ ያደርጋል። ይህ ደግሞ ለደስተኛ ትዳር ቁልፍ የሆኑትን ፍቅርን፣ መተማመንን እና ታማኝነትን ይሸረሽራል። በተጨማሪም ፖርኖግራፊ መመልከት የትዳር ዝግጅትን ላቋቋመው ለይሖዋ አምላክ አክብሮት የጎደለው ድርጊት ነው።

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ ‘ጋብቻ ክቡር ይሁን።’—ዕብራውያን 13:4

  • ለድርጊትህ ኃላፊነት ውሰድ። ‘ሚስቴ ይበልጥ ፍቅር ብታሳየኝ ኖሮ ፖርኖግራፊ አያስፈልገኝም ነበር’ አትበል። ተጠያቂነቱን ወደ ሚስትህ ማዞር በፍጹም አግባብ አይደለም። እንዲሁም እንዲህ ያለው አስተሳሰብ፣ ሚስትህ ቅር ባሰኘችህ ቁጥር ወደዚህ ሱስ እንድትመለስ ሰበብ ይፈጥራል።

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “እያንዳንዱ ሰው በራሱ ምኞት ሲማረክና ሲታለል ይፈተናል።”—ያዕቆብ 1:14

  • ከሚስትህ ጋር በግልጽና በሐቀኝነት ተነጋገር። ኬቨን የተባለ አንድ ባለትዳር እንዲህ ብሏል፦ “የፆታ ስሜት የሚቀሰቅስ ነገር ሲያጋጥመኝ ማየቴን መቀጠሌን ወይም ፈተናውን ማሸነፌን ለሚስቴ በየቀኑ እነግራታለሁ። በዚህ መልኩ በየቀኑ መነጋገራችን በመካከላችን ምንም ዓይነት ሚስጥር እንዳይኖር አድርጓል።”

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “በሁሉም ነገር በሐቀኝነት ለመኖር እንፈልጋለን።”—ዕብራውያን 13:18

  • ምንጊዜም ንቁ ሁን። ሱሱን እንዳሸነፍከው ከተሰማህ ከበርካታ ዓመታት በኋላም ሊያገረሽብህ ይችላል። ቀደም ሲል የተጠቀሰው ኬቨን እንዲህ ብሏል፦ “የፖርኖግራፊ ሱሴ ለአሥር ዓመት ያህል ሳያገረሽብኝ ስለቆየ ችግሩን ሙሉ በሙሉ እንዳሸነፍኩት ተሰምቶኝ ነበር። ለካስ ሱሱ አመቺ ጊዜ ሲያገኝ ብቅ ለማለት ተደብቆ እያደባ ነበር።”

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “የቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።”—1 ቆሮንቶስ 10:12

  • ለማየት ስትፈተን ታገሥ። ፖርኖግራፊ የማየት ምኞት እንዳያድርብህ መከላከል ባትችልም እንኳ ምኞቱን ለመፈጸም ወይም ላለመፈጸም መምረጥ ትችላለህ። ምኞቱ ማለፉ አይቀርም፤ በተለይም ሐሳብህ በሌሎች ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ማድረግ ከቻልክ ምኞቱ ቶሎ ብሎ ሊያልፍልህ ይችላል።

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ከእናንተ እያንዳንዱ የገዛ ራሱን አካል በመቆጣጠር እንዴት በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት ሊያውቅ ይገባል። ይህም . . . ስግብግብነት በሚንጸባረቅበት ልቅ የፍትወት ስሜት አይሁን።”—1 ተሰሎንቄ 4:4, 5

  • ልማዱ እንዲያገረሽብህ ከሚያደርጉ ሁኔታዎች ራቅ። ዊልፓወር ኢዝ ኖት ኢነፍ የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ “ለአደጋ የሚያጋልጥ ሁኔታ ውስጥ ስትገባ ክብሪት እንደለኮስክ ሊቆጠር ይችላል። ትንሽ ነዳጅ ካገኘ . . . እሳቱ ይቀጣጠላል።”

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ማንኛውም ክፉ ነገር በእኔ ላይ አይሠልጥን።”—መዝሙር 119:133

  • ተስፋ አትቁረጥ። ሚስትህ መልሳ እምነት እስክትጥልብህ ረጅም ጊዜ፣ ምናልባትም ዓመታት ሊወስድ ይችላል። ሆኖም ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት የሚስትህን አመኔታ መልሰህ ማትረፍ ትችላለህ።

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ፍቅር ታጋሽ . . . ነው።”—1 ቆሮንቶስ 13:4

አንድ ባልና ሚስት ጎን ለጎን ተቀምጠው እጅ ለእጅ ተያይዘው ሲያወሩ።

a ይህ ርዕስ በዋነኝነት የሚናገረው ስለ ባሎች ቢሆንም በውስጡ ያሉት ሐሳቦች ፖርኖግራፊ ለሚመለከቱ ሚስቶችም ይሠራሉ።

b አንዳንድ ባለትዳሮች፣ አብረው ፖርኖግራፊ ማየታቸው ጥምረታቸውን እንደሚያጠናክርላቸው ይገልጻሉ። ሆኖም እንዲህ ያለው ልማድ ከመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ጋር ይጋጫል።—ምሳሌ 5:15-20፤ 1 ቆሮንቶስ 13:4, 5፤ ገላትያ 5:22, 23

ባለቤትሽ ፖርኖግራፊ የሚመለከት ከሆነ

ራስሽን አትውቀሺ። ተፈላጊ እንዳልሆንሽ፣ እንደማታምሪ ወይም የጎደለሽ ነገር እንዳለ ሊሰማሽ አይገባም። ፖርኖግራፊ የሚያሳድረውን ስግብግብነት የሚንጸባረቅበትና ተፈጥሯዊ ያልሆነ ምኞት የትኛዋም ሴት ልታረካው አትችልም።

ባለቤትሽ መልሶ አመኔታሽን እንዲያተርፍ ልትረጂው ትችዪ ይሆን? በተለይም ሱሱን ለማሸነፍ ልባዊ ጥረት እያደረገ ከሆነ ልትረጂው ትችዪ ይሆናል። ፌሊሲያ የተባለች አንዲት ባለትዳር፣ ባለቤቷ ልማዱ እንዲያገረሽበት የሚያደርጉት ነገሮች የትኞቹ እንደሆኑ እንዲገነዘብ እንዲሁም ከእነዚህ ነገሮች እንዲርቅ ትረዳዋለች። እንዲህ ብላለች፦ “ይህ ችግር የባለቤቴ እንጂ የእኔ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ሆኖም እሱን መርዳቴ ትዳራችንን ለማሻሻል ረድቶኛል።”—መክብብ 4:9-12

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ