የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g00 4/8 ገጽ 28-29
  • ትልቁና ትንሹ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትልቁና ትንሹ
  • ንቁ!—2000
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአንድ ቀን ውሎ በቢራቢሮ ሕይወት ውስጥ
    ንቁ!—1994
  • አስገራሚ የሆነው የቢራቢሮ ክንፍ
    ንቁ!—2012
  • ካቤጅ ኋይት ቢራቢሮ ክንፏን የምትዘረጋበት መንገድ
    ንድፍ አውጪ አለው?
  • በቢራቢሮዎች፣ በዕፅዋትና በጉንዳኖች መካከል ያለ ወሳኝ ትስስር
    ንቁ!—2001
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2000
g00 4/8 ገጽ 28-29

ትልቁና ትንሹ

“የእሳት እራትንም ሆነ ቢራቢሮን አትግደል።”—ዊልያም ብሌክ (1757-1827)

ቢራቢሮ ስትበር አይተህ ታውቃለህ? የዚህችን ለመንካት እንኳ የምታሳሳ ሦስት አፅቄ ውበት ቆሞ የማያደንቅ ማን ይኖራል? የተለያየ መጠንና ንድፍ ያላቸው በርካታ ቢራቢሮዎች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሲሆን ዓይነታቸው ከ15, 000 እስከ 20, 000 እንደሚደርስ ይነገራል!

እስከ ዛሬ ካየሃቸው ቢራቢሮዎች ሁሉ ትልቁ የትኛው ነው? በፓፑዋ ኒው ጊኒ የምትኖር ከሆነ 280 ሚሊ ሜትር የሚደርስ ክንፍ ያለውን ክዊን አሌክሳንድራ በርድዊንግ ተብሎ የሚጠራውንና በዓለማችን በትልቅነቱ ግንባር ቀደም የሆነውን ቢራቢሮ ተመልክተህ ይሆናል። በሰሜን ወይም በመካከለኛው አሜሪካ የምትኖር ከሆነ ደግሞ 150 ሚሊ ሜትር የሚደርስ ክንፍ ያለውን ሆመረስ ስዋሎውቴል የተሰኘ ቢራቢሮ የማየት አጋጣሚ አግኝተህ ይሆናል። አፍሪካ ውስጥ ከሚገኙት ቢራቢሮዎች ሁሉ ትልቁ አፍሪካን ጃይንት ስዋሎውቴል የሚባለው ሲሆን የክንፉ ርዝማኔ እስከ 230 ሚሊ ሜትር ይደርሳል።

ትንንሾቹ ቢራቢሮዎችስ? የት ነው የሚገኙት? በዶክተር ጆን ፌልትዌል የተዘጋጀው ዚ ኢሉስትሬትድ ኢንሳይክሎፒድያ ኦቭ በተርፍላይስ “በዓለማችን ውስጥ ከሚገኙት ቢራቢሮዎች ሁሉ ትንሹ ከ1/2-3/4 ኢንች (15-19 ሚሊ ሜትር) የሚደርስ ክንፍ ያለውና . . . በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ፒግሚ ብሉ ሳይሆን አይቀርም” ሲል ይገልጻል። በብሪታንያ ከሚገኙት ቢራቢሮዎች ትንሹ ስሞል ብሉ ሲሆን ክንፉ 24 ሚሊ ሜትር ይደርሳል።

በብዙ የዓለም ክፍሎች ልትጎበኛቸው የምትችላቸው የቢራቢሮ ማራቢያዎች የሚገኙ ሲሆን በዚያ አካባቢ በምትሄድበት ጊዜ እነዚህ ውብ ቢራቢሮዎች እየመጡ ላይህ ላይ ሊያርፉ ይችላሉ። ስለነዚህ አስደናቂ ፍጥረታትና ስለ ሕይወት ዑደታቸው ማለትም ከአንዲት አነስተኛ ዕንቁላል ወደ አባጨጓሬ፣ ከዚያም ወደ ሙሽሬ፣ በመጨረሻም ወደ ሙሉ ቢራቢሮነት በመለወጥ ስለሚያካሂዱት ልውጠተ ቅርጽ ብዙ መማር ትችላለህ። ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ እየበረረች ያለች አንዲት ቢራቢሮ ስታይ ቆም ብለህ በደንብ ለማየትና ለማድነቅ ሞክር። ትንሽም ትሁን ትልቅ በጣም አስገራሚ ሆና ታገኛታለህ!

[በገጽ 28 እና 29 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ክዊን አሌክሳንድራ በርድዊንግ እና ፒግሚ ብሉ ተብለው የሚጠሩት ትልቁና ትንሹ ቢራቢሮዎች (ሁለቱም ትክክለኛ መጠናቸው ይህን ይመስላል)

[ምንጭ]

ቢራቢሮዎች:- Allyn Museum of Entomology, Florida Museum of Natural History

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ