የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 9/11 ገጽ 27-31
  • ቤተሰብ የሚወያይበት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤተሰብ የሚወያይበት
  • ንቁ!—2011
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሁለቱ ሥዕሎች ልዩነት ምንድን ነው?
  • ካርድ በመሰብሰብ መማር
  • ሕዝቦችና አገሮች
  • ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ
  • በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2011
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2012
  • ቤተሰብ የሚወያይበት
    ንቁ!—2011
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2011
g 9/11 ገጽ 27-31

ቤተሰብ የሚወያይበት

የሁለቱ ሥዕሎች ልዩነት ምንድን ነው?

በሥዕል ሀ እና ለ መካከል ያሉትን ሦስት ልዩነቶች መናገር ትችላለህ? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሎቹ የተሟሉ እንዲሆኑ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

ፍንጭ፦ ዘፀአት 25:23, 30, 31, 37⁠ን፤ 30:1-7⁠ን እና ዘሌዋውያን 24:5, 6⁠ን አንብብ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

4. ትክክለኛው ሥዕል የትኛው ነው? ሥዕል ሀ ወይስ ሥዕል ለ?

ለውይይት፦

ካህናቱ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ገብተው ከማገልገላቸው በፊት ምን ማድረግ ነበረባቸው?

ፍንጭ፦ ዘፀአት 30:17-21⁠ን አንብብ።

ወላጆችህንና ይሖዋን ለማስደሰት ንጹሕ መሆንህ ምን ያህል አስፈላጊ ነው? የሰውነት ንጽሕናህን ከመጠበቅ በተጨማሪ በምን መንገድ ንጹሕ መሆን ይኖርብሃል?

ፍንጭ፦ 1 ቆሮንቶስ 6:9-11⁠ን እና 2 ቆሮንቶስ 7:1⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በመገኛው ድንኳን ውስጥ ስለሚገኘው “ቅድስት” ምርምር ያድርግ። (ዕብራውያን 9:2) ከዚያም አንድ ላይ ተሰብሰቡና ምን አዲስ ነገር እንዳገኛችሁ ተነጋገሩ።

ፍንጭ፦ መዝሙር 119:105⁠ን፤ 141:2⁠ን፤ ማቴዎስ 4:4⁠ን፤ ዮሐንስ 4:34⁠ን እና ራእይ 8:4⁠ን አንብብ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 9 ኤርምያስ

ጥያቄ

ሀ. ይሖዋ በኤርምያስ አማካኝነት ያጻፋቸው አራት መጻሕፍት የትኞቹ ናቸው?

ለ. ኤርምያስ ጨርሶ ሚስት አላገባም። እውነት ወይስ ሐሰት?

ሐ. ኤርምያስ የተናገረውን ዓረፍተ ነገር አሟላ፦ “ቃሉ በልቤ እንደ . . . ሆነብኝ።”

[ቻርት]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

ኤርምያስ የኖረበት ዘመን 650 ዓ.ዓ. ገደማ

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

በኢየሩሳሌም ኖሯል። ወደ ኤፍራጥስ ወንዝና ወደ ግብፅ ተጉዟል።​—ኤርምያስ 13:1-9፤ 43:8-13

ኢየሩሳሌም

ኤፍራጥስ

ግብፅ

ኤርምያስ

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

ገና ከመወለዱ በፊት ነቢይ እንዲሆን ተመርጧል። (ኤርምያስ 1:1-5) ኤርምያስ ከ65 ለሚበልጡ ዓመታት አምላክን በታማኝነት አገልግሏል። ምንም እንኳ ኤርምያስ ልምድ እንደሌለውና ለመናገር እንደሚፈራ ቢሰማውም ይሖዋ “እኔ አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ” ብሎታል።​—ኤርምያስ 1:6-8

መልስ

ሀ. አንደኛና ሁለተኛ ነገሥት፣ ኤርምያስ እና ሰቆቃወ ኤርምያስ።

ለ. እውነት።​—ኤርምያስ 16:1-4

ሐ. “. . . እሳት በዐጥንቴም ውስጥ እንደ ረመጥ”​—ኤርምያስ 20:9

ሕዝቦችና አገሮች

5. ጄፍሪ እባላለሁ። የ9 ዓመት ልጅ ስሆን የምኖረው በፊጂ ነው። በፊጂ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 500፣ 2,500 ወይስ 10,500?

6. የምኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ። የምትኖርበት አገር ከፊጂ በጣም ይርቃል?

ሀ

ለ

ሐ

መ

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 27 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. በመቅረዙ ላይ ያሉት መብራቶች ቁጥር።

2. የኅብስቶቹ ቁጥር።

3. በዕጣን መሠዊያው ላይ ያሉት ቀንዶች።

4. ሀ።

5. 2,500።

6. መ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ