የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g25 ቁጥር 1 ገጽ 4-5
  • እውነታውን ተቀበል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እውነታውን ተቀበል
  • ንቁ!—2025
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ዓለም አቀፍ የዋጋ ግሽበት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2025
  • ተስፋ ይኑርህ
    ንቁ!—2025
  • ገንዘብህን በጥበብ ተጠቀም
    ንቁ!—2025
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2025
g25 ቁጥር 1 ገጽ 4-5
ምስሎች፦ 1. ከጉልት የምትሸምት አንዲት ሴት ቲማቲም ስትመርጥ። 2. ለገዛችው ሸቀጥ ለመክፈል ለሻጯ ገንዘብ ስትሰጣት።

የኑሮ ውድነትን መቋቋም

እውነታውን ተቀበል

የሸቀጦች ዋጋ የሚጨምረው ቀስ በቀስ ከሆነ ለውጡን ያን ያህል ላናስተውለው እንችላለን፤ በተለይ ገቢያችንም እኩል የሚሄድ ከሆነ። ይሁን እንጂ የዋጋ ንረቱ ድንገተኛ ሲሆን እንዲሁም ገቢያችን እምብዛም ካልተለወጠ ልንጨነቅ እንችላለን፤ በተለይ የምናስተዳድረው ቤተሰብ ካለን ሁኔታው ያሳስበናል።

የሸቀጦች ዋጋ በእኛ ቁጥጥር ሥር አይደለም። እውነታውን መቀበላችን ግን ይጠቅመናል።

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የኑሮ ውድነት ሲከሰት እውነታውን አምነው የሚቀበሉ ሰዎች በአብዛኛው . . .

  • መረጋጋት አይከብዳቸውም። ስንረጋጋ ደግሞ በደንብ ማሰብና ጥሩ ውሳኔዎች መወሰን እንችላለን።

  • ተገቢ ካልሆኑ ልማዶች ይቆጠባሉ። ለምሳሌ ክፍያዎችን ችላ አይሉም ወይም አባካኝ አይሆኑም።

  • ከቤተሰባቸው አባላት ጋር በገንዘብ ዙሪያ አይጨቃጨቁም።

  • ሁኔታውን ለመቋቋም መንገድ ይፈልጋሉ፤ ለምሳሌ ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ነገሮችና የገንዘብ አወጣጣቸውን ያስተካክላሉ።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ማስተካከያ ለማድረግ ፈቃደኛ ሁን። የዋጋ ንረት በሚከሰትበት ወቅት፣ የሚቻል ከሆነ ወጪዎቻችንን መቀነሳችን ጥበብ ነው። አንዳንድ ሰዎች ከገቢያቸው በላይ ቢሆንም የቀድሞ ሕይወታቸውን ላለመተው ብዙ ይፍጨረጨራሉ፤ ሁኔታው በፍጥነት ከሚፈስ ወንዝ በተቃራኒ አቅጣጫ ለመዋኘት እንደመሞከር ነው! ትርፉ ድካም ብቻ ነው። እርግጥ ነው፣ ቤተሰብ ካለህ ለእነሱ የሚያስፈልጋቸውን ነገር ማሟላት መቻልህ ያሳስብህ ይሆናል፤ ደግሞም ይህ ትክክል ነው! ይሁንና ቤተሰብህ ከምንም በላይ የሚፈልገው የአንተን ፍቅር፣ ጊዜ እንዲሁም ትኩረት መሆኑን አትርሳ።

“ለመሆኑ ከእናንተ ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንዲት ደቂቃ መጨመር የሚችል ማነው?”—ሉቃስ 12:25 አ.መ.ት

“ስለ ነገ ፈጽሞ አትጨነቁ፤ ምክንያቱም ነገ የራሱ የሆኑ የሚያስጨንቁ ነገሮች አሉት። እያንዳንዱ ቀን የራሱ የሆነ በቂ ችግር አለው።”—ማቴዎስ 6:34

ቀድሞ የነበረንን የምቾት ሕይወት ላለመተው መፍጨርጨር በፍጥነት ከሚፈስ ወንዝ በተቃራኒ አቅጣጫ ለመዋኘት እንደመሞከር ነው

ፋዚሊያ።

“መጽሐፍ ቅዱስ በ2 ጢሞቴዎስ 3:1 ላይ አስቀድሞ እንደተናገረው የምንኖረው ‘ለመቋቋም በሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን’ ውስጥ ነው። በመሆኑም ኢኮኖሚው አስቸጋሪ ሲሆን እንዲሁም የዋጋ ንረት ሲከሰት ብዙም አልገረምም። የግድ አስፈላጊ ባልሆኑ ነገሮች ላይ የማወጣውን ወጪ በመቀነስ አኗኗሬን ለማስተካከል እሞክራለሁ።”—ፋዚሊያ፣ አዘርባጃን

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ