እንደ አንድ አካል ሆኖ የአምላክን ፈቃድ ማድረግ
በዚህ ብሮሹር ውስጥ ስለ ይሖዋ ምሥክሮች አገልግሎት፣ ስብሰባዎችና ድርጅት የቀረበው መረጃ አንተን አንባቢውን ከእነርሱ ጋር በይበልጥ ተቀራርበህ አምላክን እንድታመልክ እንዳበረታታህ ተስፋ እናደርጋለን። ከይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤ ጋር ግንኙነት በመመሥረትና በትልልቅ ስብሰባዎች በመገኘት ራስህ ሁኔታዎችን አይተህ እንድትረዳ እንጋብዝሃለን። ይህም በአሁኑ ጊዜ የአምላክን ፈቃድ በይበልጥ እንድትረዳ አስተዋጽኦ ያደርግልሃል።—ቲቶ 2:11–14
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ በጐ ሥራ የገለጸውን የአቋም ደረጃ ጠብቀህ መኖር ስትጀምር በይሖዋ ምሥክሮች ሥራ የመካፈል መብት ታገኛለህ። በጋለ ፍቅር ከተሳሰረ ዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር ጋር ለመቀራረብ ትችላለህ። ከዚህም በላይ ከመጪው የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ ተርፈህ ሰላምና ጽድቅ በሚሰፍንበት አዲስ ሥርዓት ውስጥ የመኖር ተስፋ ልታገኝ ትችላለህ።—2 ጴጥሮስ 3:13
[በገጽ 30, 31 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]
የይሖዋ ምሥክሮች እንደ አንድ አካል ሆነው የአምላክን ፈቃድ ከሚያደርጉባቸው ከ200 በላይ አገሮች እና ደሴቶች መካከል በ18ቱ የሚከናወነውን ሥራ የሚያሳዩ ፎቶግራፎች
ናይጄሪያ
ኦስትሪያ
ብራዚል
ጃፓን
ካናዳ
ጉዋቴማላ
አርጀንቲና
ጀርመን
ታይዋን
ፊንላንድ
ደቡብ አፍሪካ
ሕንድ
ዩናይትድ ስቴትስ
ፊጂ
ቺሊ
ኢጣልያ
ቦሊቪያ
ፊሊፒንስ