የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • th ገጽ 3
  • የበላይ አካሉ መልእክት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የበላይ አካሉ መልእክት
  • ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የተባለውን ብሮሹር መጠቀም የሚቻልበት ሌላ መንገድ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • በብሮሹሮች ተጠቅማችሁ የመንግሥቱን ምሥራች አውጁ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1996
  • የሰዎችን አእምሮና ልብ ለመማረክ በብሮሹሮች ተጠቀሙ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1998
ለተጨማሪ መረጃ
ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
th ገጽ 3

የበላይ አካሉ መልእክት

‘አስተማሪዎች ልትሆኑ ይገባችኋል።’ (ዕብ. 5:12) በአጽናፈ ዓለም ውስጥ ከሁሉ የላቀ አስተማሪ የሆነው ይሖዋ፣ ስለ እሱ ሌሎችን እንድናስተምር እኛን መጋበዙ በጣም የሚያስገርም ነው! ስለ ይሖዋ የሚገልጸውን እውነት በቤተሰብና በጉባኤ ውስጥ ወይም በአገልግሎት ላይ ለሌሎች ማስተማር ታላቅ መብት ቢሆንም ከባድ ኃላፊነትም ያስከትላል። ታዲያ በዚህ ረገድ ሊሳካልን የሚችለው እንዴት ነው?

ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ የጻፈው ሐሳብ መልሱን ይጠቁመናል፤ ጳውሎስ ጢሞቴዎስን “ለሰዎች ለማንበብ፣ አጥብቀህ ለመምከርና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ” ብሎት ነበር። አክሎም “ይህን በማድረግ ራስህንም ሆነ የሚሰሙህን ታድናለህ” ብሎታል። (1 ጢሞ. 4:13, 16) አንተም ሕይወት አድን የሆነውን መልእክት ለሌሎች የማካፈል መብት ተሰጥቶሃል። በመሆኑም የማንበብና የማስተማር ችሎታህን ለማሻሻል ጥረት ማድረግህ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ ብሮሹር የተዘጋጀው ይህን ለማድረግ እንዲረዳህ ታስቦ ነው። እስቲ ከብሮሹሩ ገጽታዎች አንዳንዶቹን እንመልከት።

ጥቅስ

በእያንዳንዱ ገጽ ላይ አንድ ጥቅስ ይገኛል። ጥቅሱ፣ ከሚብራራው ነጥብ ጋር የሚዛመድ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓት አሊያም ነጥቡ እንዴት ተግባራዊ መሆን እንደሚችል የሚያሳይ ምሳሌ የያዘ ነው

ጠቃሚ ሐሳብ

ከዋናው ነጥብ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጠቃሚ ሐሳቦች

ለአገልግሎት

በአገልግሎት ላይ ተግባራዊ የሚሆኑ ሐሳቦች። በብሮሹሩ ውስጥ ከሚገኙት ሐሳቦች አብዛኞቹን በመስክ አገልግሎት ላይም ሆነ ከመድረክ ስናስተምር ልንሠራባቸው እንችላለን።

ይሖዋ ‘ታላቅ አስተማሪ’ ነው። (ኢሳ. 30:20) ይህ ብሮሹር የማንበብም ሆነ የማስተማር ችሎታህን ለማሻሻል የሚረዳህ ቢሆንም የምንሰብከው መልእክት ከይሖዋ የመጣ መሆኑንና ሰዎችን የሚስበው እሱ መሆኑን መዘንጋት የለብህም። (ዮሐ. 6:44) እንግዲያው ቅዱስ መንፈሱን እንዲሰጥህ ሁልጊዜ ጸልይ። በአምላክ ቃል አዘውትረህ ተጠቀም። የአድማጮችህን ትኩረት ወደ ራስህ ከመሳብ ይልቅ በይሖዋ ላይ እንዲያተኩሩ መርዳት ይኖርብሃል። አድማጮችህ ለይሖዋ ጥልቅ ፍቅር እንዲያዳብሩ ለመርዳት ጥረት አድርግ።

ለሰው ልጆች ከተሰጡት መልእክቶች ሁሉ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነውን መልእክት የማስተላለፍ መብት ተሰጥቶሃል። “አምላክ በሚሰጠው ኃይል” ከተማመንክ እንደሚሳካልህ እርግጠኞች ነን።—1 ጴጥ. 4:11

አብረናችሁ የምንሠራ

የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል

አንድ ወንድም ንግግር ሲያቀርብ፣ አንዲት እህት ስትመሠክር፣ አንድ ወንድም በሥራ ቦታው ሲያገለግል፣ አንዲት ወጣት የምትማርበት ክፍል ውስጥ ንግግር ስታቀርብ
    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ