የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w19 ታኅሣሥ ገጽ 15
  • የአንባቢያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባቢያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በገነት ውስጥ የነበረው ሕይወት ምን ይመስል ነበር?
    አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • ከሞት በኋላ ሕይወት—ሰዎች ምን ብለው ያምናሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • በመንፈሳዊው ዓለም ውስጥ የተነሳ ዓመፅ
    የሙታን መናፍስት—ሊረዱህ ወይም ሊጎዱህ ይችላሉን? ደግሞስ በእርግጥ አሉን?
  • የማትሞት ነፍስ አለችህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
w19 ታኅሣሥ ገጽ 15

የአንባቢያን ጥያቄዎች

ሔዋን ከመልካምና ክፉ እውቀት ዛፍ ብትበላ እንደማትሞት ሰይጣን ሲነግራት በዛሬው ጊዜ በስፋት የሚታመንበትን ነፍስ አትሞትም የሚለውን ትምህርት እያስተዋወቀ ነበር?

ሰይጣን፣ ሔዋንን በእባብ አማካኝነት ሲያነጋግራት፤ ሔዋን ፍሬውን ለመብላት ተፈትና

አይመስልም። ዲያብሎስ፣ አምላክ የከለከላትን ፍሬ ብትበላ እንደማትሞት ለሔዋን ሲነግራት በሥጋ የሞተች ቢመስልም ከእሷ የሚወጣ አንድ የማይታይ ነገር (በዛሬው ጊዜ አንዳንዶች የማይሞት ነፍስ ብለው የሚጠሩት ነገር) በሌላ ቦታ መኖሩን እንደሚቀጥል መግለጹ አልነበረም። ሰይጣን በእባብ አማካኝነት ለሔዋን የነገራት ከዛፉ ፍሬ ከበላች ‘ፈጽሞ እንደማትሞት’ ነው። ሰይጣን ይህን ሲል ሔዋን በሕይወት መኖሯን እንደምትቀጥል እንዲሁም ከአምላክ አመራር ውጭ ሆና በምድር ላይ አስደሳች ሕይወት እንደሚኖራት መጠቆሙ ነበር።—ዘፍ. 2:17፤ 3:3-5

ታዲያ ነፍስ እንደማትሞት የሚገልጸው የሐሰት ትምህርት የመነጨው በኤደን ካልሆነ ይህ ትምህርት የተጠነሰሰው መቼ ነው? በእርግጠኝነት መናገር አንችልም። ሆኖም የሐሰት አምልኮ በሙሉ በኖኅ ዘመን በደረሰው የጥፋት ውኃ እንደጠፋ እናውቃለን። ከጥፋቱ የተረፉት እውነተኛ የአምላክ አገልጋዮች የሆኑት ኖኅና ቤተሰቡ ብቻ ስለሆኑ የተሳሳተ ሃይማኖታዊ ትምህርት የሚያስተምሩ ሰዎች ከጥፋቱ አላለፉም።

እንግዲያው በዛሬው ጊዜ ያለው፣ የሰው ነፍስ እንደማትሞት የሚገልጸው ትምህርት የመነጨው ከጥፋት ውኃ በኋላ መሆን አለበት። አምላክ በባቤል የሰዎችን ቋንቋ ባዘበራረቀበት ወቅት ሰዎቹ “በመላው ምድር ላይ እንዲበተኑ አድርጓል”፤ እነዚህ ሰዎች የማትሞት ነፍስ እንዳለች የሚገልጸውን ትምህርት ወደተበተኑባቸው አካባቢዎች ይዘው ሄደው መሆን አለበት። (ዘፍ. 11:8, 9) ይህ የሐሰት ትምህርት የተጠነሰሰው መቼም ይሁን መቼ ትምህርቱን ያስጀመረው “የውሸት አባት” የሆነው ሰይጣን ዲያብሎስ እንደሆነና ይህ ትምህርት ሲስፋፋ በማየት እንደተደሰተ ጥርጥር የለውም።—ዮሐ. 8:44

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ