የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ከታች የቀረቡት ጥያቄዎች ነሐሴ 27, 2012 በሚጀምር ሳምንት ውስጥ መልስ የሚሰጥባቸው ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀንም በጥያቄዎቹ ላይ ተካትቷል።
1. ሕዝቅኤል ስለ ከሃዲዋ ይሁዳ የተመለከተው ራእይ ለምን ነገር ጥላ ነው? እኛስ ከዚህ ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን? (ሕዝ. 8:15-17) [ሐምሌ 2, w07 7/1 ገጽ 13 አን. 6፤ w93 1/15 ገጽ 27-28 አን. 7, 12]
2. አብዛኞቹ የሃይማኖት መሪዎች በሕዝቅኤል ዘመን ከነበሩት ሐሰተኛ ነቢያት ጋር የሚመሳሰሉት በምን መንገድ ነው? (ሕዝ. 13:3, 7) [ሐምሌ 9, w99 10/1 ገጽ 13 አን. 14-15]
3. በሕዝቅኤል 17:22-24 ላይ ተመዝግቦ በሚገኘው ትንቢት ላይ የተገለጸው ‘ለምለም ቀንበጥ’ (የ1980 ትርጉም) ማን ነው? ቀንበጡ የተተከለበት ‘ከሁሉ ከፍ ያለው ተራራ’ የሚያመለክተው ማንን ነው? በተራራው ላይ የተተከለው ቀንበጥ ‘ያማረ ዝግባ’ የሚሆነውስ በምን መንገድ ነው? [ሐምሌ 16, w07 7/1 ገጽ 12-13 አን. 6]
4. ሕዝቅኤል 18:20 “ልጅ በአባቱ ኀጢአት አይቀጣም” ሲል ዘፀአት 20:5 ደግሞ ይሖዋ ‘ልጆችን ከአባቶቻቸው ኀጢአት የተነሣ እንደሚቀጣ’ መናገሩ ሁለቱ ጥቅሶች እርስ በርሳቸው እንደሚጋጩ ያሳያል? [ሐምሌ 23, w10 3/15 ገጽ 28-29]
5. ሕዝቅኤል 21:18-22 ላይ የሚገኘው ዘገባ ሰዎችም ሆኑ አጋንንት የይሖዋን ዓላማ ማጨናገፍ እንደማይችሉ የሚያሳየው እንዴት ነው? [ሐምሌ 30, w07 7/1 ገጽ 14 አን. 4]
6. በሕዝቅኤል 24:6, 11, 12 ላይ ተመዝግቦ እንደምናገኘው የብረት ድስቱ መዛግ ምን ያመለክታል? በቁጥር 14 ላይ ከሚገኘው ሐሳብ ምን ትምህርት እናገኛለን? [ነሐሴ 6, w07 7/1 ገጽ 14 አን. 2]
7. ጢሮስን አስመልክቶ የተነገረው ትንቢት ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነው? (ሕዝ. 26:2-21) [ነሐሴ 6, it-1-E ገጽ 70፣ ሣጥኑ፤ bsi07 ገጽ 7 አን. 4]
8. በሕዝቅኤል 28:2, 12-17 ላይ ‘የጢሮስን ንጉሥ’ አስመልክቶ ከተጻፉት አባባሎች ውስጥ ሰይጣንን በትክክል የሚገልጹት የትኞቹ ናቸው? [ነሐሴ 13, w05 10/15 ገጽ 23-24 አን. 10-14፤ it-2-E ገጽ 604 አን. 4-5]
9. ግብፅ ለ40 ዓመታት ባድማ የሆነችው መቼ ነበር? ይህ ሁኔታ ተፈጽሟል ብለን እንድናምን የሚያደርገንስ ምንድን ነው? (ሕዝ. 29:8-12) [ነሐሴ 13, w07 8/1 ገጽ 8 አን. 5]
10. ሕዝቅኤል፣ የሚያነጋግራቸው ሰዎች ግድየለሽ፣ ፌዘኛና መልእክቱን ለመቀበል እምቢተኛ በመሆናቸው ምን ተሰማው? ይሖዋስ ምን ማረጋገጫ ሰጥቶታል? (ሕዝ. 33:31-33) [ነሐሴ 20, w91 3/15 ገጽ 17 አን. 16-17]