ነሐሴ 27 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ነሐሴ 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 17 እና ጸሎት
□ የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
fy ምዕ. 14 ከአን. 1-9 (25 ደቂቃ)
□ ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ሕዝቅኤል 35-38 (10 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
□ የአገልግሎት ስብሰባ፦
10 ደቂቃ፦ ማስታወቂያዎች። “በሳምንቱ መሃል በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ የተደረጉ ማስተካከያዎች።” በንግግር የሚቀርብ። ከንግግሩ በኋላ በቅርብ ጊዜ ለደረሰን መጠበቂያ ግንብ የተዘጋጀውን የአቀራረብ ናሙና በመጠቀም በነሐሴ ወር የመጀመሪያ ቅዳሜ እንዴት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር እንደሚቻል የሚያሳይ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
15 ደቂቃ፦ ሰዎች በቀላሉ ሊገባቸው በሚችል መንገድ መሥክሩ። በአገልግሎት ትምህርት ቤት መጽሐፍ ከገጽ 226 እስከ 229 ባለው ሐሳብ ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። የቀረቡትን ነጥቦች በመጠቀም አንድ ወይም ሁለት ሠርቶ ማሳያዎች እንዲቀርቡ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ምን ትምህርት እናገኛለን? በውይይት የሚቀርብ። ሉቃስ 10:1-4, 17 እንዲነበብ አድርግ። ከዚያም ይህ ዘገባ ከአገልግሎታችን ጋር በተያያዘ ሊጠቅመን የሚችለው እንዴት እንደሆነ ተወያዩበት።
መዝሙር 22 እና ጸሎት