የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ሚያዝያ 27, 2015 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። እያንዳንዱ ነጥብ ውይይት የሚደረግበት መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ቀን በጥያቄዎቹ ላይ የተካተተው በየሳምንቱ ለትምህርት ቤቱ ዝግጅት በምናደርግበት ወቅት ምርምር እንድናደርግ ታስቦ ነው።
ጽኑ ፍቅር የሚባለው ምን ዓይነት ፍቅር ነው? እንዲህ ዓይነቱን ፍቅር በተለይ በየትኞቹ የሕይወታችን ዘርፎች ልናሳይ ይገባል? (ሩት 1:16, 17) [መጋ. 2, w12 7/1 ገጽ 26 አን. 6]
ሩት “ምግባረ መልካም ሴት” የሚል ስም ልታተርፍ የቻለችው እንዴት ነው? (ሩት 3:11) [መጋ. 2, w12 10/1 ገጽ 23 አን. 1]
ችግሮች ሲያጋጥሙን ማድረግ ስላለብን ነገር ከሐና ምን እንማራለን? (1 ሳሙ. 1:16-18) [መጋ. 9, w07 3/15 ገጽ 16 አን. 4-5]
ሳሙኤል “በይሖዋ ፊት እያደገ” ሲሄድ የኤሊን ልጆች መጥፎ ምሳሌ እንዳይከተል የረዳው ምንድን ነው? (1 ሳሙ. 2:21) [መጋ. 9, w10 10/1 ገጽ 16 አን. 3-4]
ሳኦል “አንዳንድ የማይረቡ ሰዎች” የእሱን ንግሥና እንደማይቀበሉ በገለጹበት ወቅት በችኮላ እርምጃ አለመውሰዱ ምን ያስተምረናል? (1 ሳሙ. 10:22, 27) [መጋ. 23, w05 3/15 ገጽ 23 አን. 2]
ሳኦል፣ ይሖዋን አለመታዘዝን መሥዋዕት በማቅረብ ማካካስ እንደሚቻል ተሰምቶት ነበር፤ እሱ ከነበረው የተሳሳተ አመለካከት ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን? (1 ሳሙ. 15:22, 23) [መጋ. 30, w07 6/15 ገጽ 26 አን. 3-4]
ይሖዋ ‘ልብን የሚያይ’ አምላክ መሆኑን ማወቃችን የሚያጽናናን ለምንድን ነው? (1 ሳሙ. 16:7) [ሚያ. 6, w10 3/1 ገጽ 23 አን. 7]
ምሳሌ 1:4 እንደሚናገረው ይሖዋ፣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን የትኛውን ችሎታችንን እንድንጠቀምበት ይፈልጋል? (1 ሳሙ. 21:12, 13) [ሚያ. 13, w05 3/15 ገጽ 24 አን. 5]
አቢጋኤል ለዳዊትና ለሰዎቹ ምግብ መላኳ የባሏን የራስነት ሥልጣን እንደማታከብር የሚያሳይ አይደለም የምንለው ለምንድን ነው? (1 ሳሙ. 25:10, 11, 18, 19) [ሚያ. 20, w09 7/1 ገጽ 20 አን. 4]
አቢጋኤል የእሷ ጥፋት ላልሆነ ነገር ይቅርታ ጠይቃለች። ከእሷ ምሳሌ ምን እንማራለን? (1 ሳሙ. 25:24) [ሚያ. 20, w02 11/1 ገጽ 5 አን. 1, 4]