ሚያዝያ 27 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ሚያዝያ 27 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 1 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 18 ከአን. 1-5፣ በገጽ 142 እና 144 ላይ የሚገኙት ሣጥኖች (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ሳሙኤል 26-31 (8 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ ‘ጊዜያችሁን በተሻለ መንገድ በመጠቀም’ እንደ ጥበበኛ ሰዎች ተመላለሱ።—ኤፌ. 5:15, 16
7 ደቂቃ፦ “ቀጥተኛ ግብዣ።” በጥያቄና መልስ የሚቀርብ። በአንቀጽ 3 ላይ ስትወያዩ ግብዣውን እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል የሚያሳይ አጭር ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
10 ደቂቃ፦ ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት።
13 ደቂቃ፦ “የአምላክ ቃል ያለውን ኃይል በአገልግሎታችሁ ተጠቀሙበት።” በውይይት የሚቀርብ። በስተ መጨረሻ ላይ ሁለት ክፍል ያለው ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ። መጀመሪያ አንድ አስፋፊ መጽሐፍ ቅዱሱን ሳያወጣ በ2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17 ላይ ያለውን የተወሰነ ሐሳብ በቃሉ በመጥቀስ ምሥራች የሚለውን ብሮሹር ያስተዋውቃል። ከዚያም አስፋፊው ሠርቶ ማሳያውን በድጋሚ ያቀርባል፤ በዚህ ጊዜ ግን ጥቅሱን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያነብለታል። ሁለተኛው አቀራረብ ውጤታማ የሆነው ለምን እንደሆነ ሐሳብ እንዲሰጡ አድማጮችን ጋብዝ።
መዝሙር 124 እና ጸሎት