የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
ጥቅምት 26, 2015 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው።
በ2 ነገሥት 13:18, 19 ላይ የሚገኘው ዘገባ አምላክን በቅንዓትና በሙሉ ልብ ማገልገል አስፈላጊ መሆኑን የሚያጎላው እንዴት ነው? [መስ. 7, w10 4/15 ገጽ 26 አን. 11]
ዮናስ ነቢይ ሆኖ ባገለገለበት ወቅት የእስራኤል ንጉሥ የነበረው ማን ነው? በ2 ነገሥት 14:23-25 ላይ ከሚገኘው ዘገባ አንጻር ስለ ዮናስ አገልግሎት ምን ነገር መገንዘብ እንችላለን? [መስ. 7, w09 1/1 ገጽ 25 አን. 4]
አካዝ አምላክ በነቢዩ ኢሳይያስ በኩል በተናገረው ቃል ላይ እምነት እንዳልነበረው ያሳየው እንዴት ነው? ከባድ ውሳኔዎችን ስናደርግ ራሳችንን ምን ብለን መጠየቅ ይኖርብናል? (2 ነገ. 16:7) [መስ. 14, w13 11/15 ገጽ 17 አን. 5]
የአምላክን ሕዝቦች ለመጨቆን የሚሞክሩ ሰዎች ራፋስቂስ የተጠቀመውን የትኛውን ዘዴ ይጠቀማሉ? ተቃዋሚዎች የሚያቀርቧቸውን የሐሰት ማስረጃዎች ውድቅ ለማድረግ የትኛውን ባሕርይ ማዳበር ይኖርብናል? (2 ነገ. 18:22, 25) [መስ. 14, w10 7/15 ገጽ 13 አን. 3-4]
ኢዮስያስ የተወው የትሕትና ምሳሌ ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችንና ጥናታችን ይበልጥ ጥቅም ማግኘት እንድንችል የሚረዳን እንዴት ነው? (2 ነገ. 22:19, 20 ግርጌ) [መስ. 21, w00 3/1 ገጽ 30 አን. 2]
በ2 ነገሥት 25:27-30 ላይ የተጠቀሱት ሁለት ነገሥታት በእርግጥ እንደነበሩ አርኪኦሎጂ ያረጋገጠው እንዴት ነው? [መስ. 28, w12 6/1 ገጽ 5 አን. 2-3]
ያቤጽ ለይሖዋ ያቀረባቸው ሦስት ልመናዎች ምንድን ናቸው? ይህስ ስለ ጸሎት ምን ያስተምረናል? (1 ዜና 4:9, 10) [ጥቅ. 5, w10 10/1 ገጽ 23]
በ1 ዜና መዋዕል 5:18-22 ላይ የተጠቀሰው ጦርነት ውጤት፣ በምናደርገው መንፈሳዊ ውጊያ በድፍረት እንድንቀጥል የሚያበረታታን እንዴት ነው? [ጥቅ. 12, w05 10/1 ገጽ 9 አን. 7]
ዳዊት ይሖዋ ስለ ደም ቅድስና ያለውን አመለካከት መረዳትና በሥራ ላይ ማዋል የቻለው ለምንድን ነው? ዳዊት የተወው ምሳሌ ምን እንድናደርግ ያነሳሳናል? (1 ዜና 11:17-19) [ጥቅ. 19, w12 11/15 ገጽ 6-7 አን. 12-14]
ዳዊት የቃል ኪዳኑን ታቦት ወደ ኢየሩሳሌም ሲያመጣ ምን ነገር አላደረገም ነበር? ከዚህ ዘገባ ምን ጠቃሚ ትምህርት እናገኛለን? (1 ዜና 15:13) [ጥቅ. 26, w03 5/1 ገጽ 10-11 አን. 11-13]