ጥቅምት 26 የሚጀምር ሳምንት ፕሮግራም
ጥቅምት 26 የሚጀምር ሳምንት
መዝሙር 15 እና ጸሎት
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦
bt ምዕ. 26 ከአን. 9-15 እና በገጽ 208 ላይ የሚገኝ ሣጥን (30 ደቂቃ)
ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት፦
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ 1 ዜና መዋዕል 12-15 (8 ደቂቃ)
የቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ (20 ደቂቃ)
የአገልግሎት ስብሰባ፦
የወሩ ጭብጥ፦ “ሥር ሰዳችሁ” እና “በእምነት ጸንታችሁ” ኑሩ።—ቆላ. 2:6, 7
10 ደቂቃ፦ በኅዳር ወር የምናበረክተው ጽሑፍ። በውይይት የሚቀርብ። ትራክቶችንና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት የተባለውን መጽሐፍ የማበርከት ፍላጎታቸው ይበልጥ እንዲነሳሳ አድርግ። ከሚያዝያ 2014 የመንግሥት አገልግሎታችን ላይ “አዲሶቹ ትራክቶች ያላቸው ማራኪ ገጽታ!” በሚለው ርዕስ ሥር የተጠቀሱ አንዳንድ አስፈላጊ ነጥቦችን በአጭሩ ጥቀስ። ለአገልግሎት ክልላችሁ ተስማሚ የሆነ ሠርቶ ማሳያ እንዲቀርብ አድርግ።
20 ደቂቃ፦ “የአምላክ ቃል ያለው ኃይል በሕይወትህ ውስጥ እንዲሠራ እያደረግክ ነው?” በንግግር የሚቀርብ። አጭር የመግቢያ ሐሳብ ካቀረብክ በኋላ በjw.org/am ላይ የሚገኘውን “ይሖዋ እርማት ሲሰጣችሁ አትታክቱ!” የሚል ርዕስ ያለውን ድራማዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ አጫውት። በአምላክ ቃል ላይ ማሰላሰላችን በግል ሕይወታችን ተግባራዊ ልናደርጋቸው የምንችላቸው መሠረታዊ ሥርዓቶችን ለማግኘት የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ጎላ አድርገህ ግለጽ። ሁሉም በjw.org/am ላይ የሚወጣውን ድራማዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ አዳምጠው ጥቅም እንዲያገኙ በማበረታታት ክፍልህን ደምድም።
መዝሙር 113 እና ጸሎት