የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mrt ርዕስ 25
  • ምድርን የሚታደጋት ማን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምድርን የሚታደጋት ማን ነው?
  • ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሰው ልጆች የሚያደርጉት ጥረት ውጤት ያስገኝ ይሆን?
  • አስተማማኝ ተስፋ አለ
  • ምድር ትጠፋለች?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የሰው ልጆች ምድርን ለዘለቄታው ያጠፏት ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • አምላክ ፕላኔታችን እንደምትተርፍ ቃል ገብቷል
    ንቁ!—2023
  • ፈጣሪ ለሰው ልጆች የሰጠው ዘላለማዊ ስጦታ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
ለተጨማሪ መረጃ
ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
mrt ርዕስ 25
አንዲት ትንሽ ልጅ፣ አበባ ውኃ ስታጠጣ። አካባቢውን የሚበክሉ ኢንዱስትሪዎች ከርቀት ይታያሉ።

ምድርን የሚታደጋት ማን ነው?

ብዙዎች፣ የሰው ልጆች በምድርና በውስጧ ባሉት ሕያዋን ፍጥረታት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ እንዳሉ ያምናሉ፤ በዚህም ምክንያት ስጋት ገብቷቸዋል። አንዳንድ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች እንደሚገልጹት የሰው ልጆች የሚያደርጓቸው ነገሮች አንዳንድ ፍጥረታት ከምድር ገጽ የመጥፋት አደጋ እንዲደቀንባቸው ያደረጉ ከመሆኑም ሌላ በምድራችን ላይ ያለው ብዝሐ ሕይወት እስካሁን ድረስ ሆኖ በማያውቅ መጠን እንዲጎዳ አድርገዋል።

ታዲያ የሰው ልጆች ምድርን ሙሉ በሙሉ ያበላሿት ይሆን? ወይስ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምተው መኖር ይጀምራሉ?

የሰው ልጆች የሚያደርጉት ጥረት ውጤት ያስገኝ ይሆን?

በርካታ ምሁራን፣ የሰው ልጆች ምድርን መታደግና ከተፈጥሮ ጋር ተስማምተው መኖር እንደሚችሉ በእርግጠኝነት ይናገራሉ። አንዳንድ ተመራማሪዎች ግን የሰው ልጆች የሚያደርጉት ጥረት እንዲሳካ ከተፈለገ በተለያዩ አቅጣጫዎች፣ በተመሳሳይ ጊዜ ለውጥ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያምናሉ። መደረግ ካለባቸው ለውጦች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦

  • መሬትን፣ ደኖችን፣ ረግረጋማ አካባቢዎችን እና ውቅያኖሶችን በምንጠቀምበት መንገድ ላይ ማሻሻያ ማድረግ።

  • የተለያዩ የግብርና ዘዴዎችንና የኃይል ምንጮችን መጠቀም።

  • የምግብ ምርትንና አቅርቦትን ማስተካከል፤ ይኸውም በአብዛኛው አትክልት መመገብ፣ ሥጋና ዓሣ በመጠኑ ብቻ መመገብ እንዲሁም የምግብ ፍጆታንና ብክነትን መቀነስ።

  • ጥሩ ሕይወት ለመምራት ቁሳዊ ነገሮችን ማካበት የግድ አስፈላጊ እንዳልሆነ መገንዘብ።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? መንግሥታት፣ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦች ከዚህ በፊት ሆኖ በማያውቅ መጠን በመተባበር እንዲህ ዓይነት ለውጥ ያመጣሉ ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ ነው? ወይስ የአንዳንዶች ሥር የሰደደ ስግብግብነት፣ ራስ ወዳድነትና አርቆ አለማሰብ ለዚህ እንቅፋት ይሆናል?—2 ጢሞቴዎስ 3:1-5

አስተማማኝ ተስፋ አለ

መጽሐፍ ቅዱስ የምድራችን ዕጣ ፈንታ አስተማማኝ እንደሆነ ዋስትና ይሰጠናል። የሰው ልጆች የሚያደርጉት ጥረት ብቻውን ምድርን ለመታደግ በቂ ያልሆነው ለምን እንደሆነ የሚያብራራ ከመሆኑም ሌላ ምን ዓይነት ለውጥ መደረግ እንዳለበት ይገልጻል። በተጨማሪም ይህ ለውጥ የሚመጣው እንዴት እንደሆነ ይነግረናል።

የሰው ልጆች የሚያደርጉት ጥረት ብቻውን ምድርን ለመታደግ በቂ ያልሆነው ለምንድን ነው? ይሖዋa አምላክ ምድርን ከፈጠረ በኋላ ምድርን የመንከባከቡን ኃላፊነት ለሰዎች ሰጥቷቸዋል። (ዘፍጥረት 1:28፤ 2:15) ሰዎች ይህን ኃላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት የሚችሉት የፈጣሪያቸውን አመራር ለማግኘት ጥረት ካደረጉና መመሪያውን ከታዘዙ ብቻ ነው። (ምሳሌ 20:24) እነሱ ግን የይሖዋን መመሪያ ችላ በማለት ራሳቸውን ለመምራት መረጡ። (መክብብ 7:29) ሰዎች ያለፈጣሪ እርዳታ ምድርን በተሳካ ሁኔታ መንከባከብ አይችሉም፤ ምንም ያህል ጥረት ቢያደርጉ መሠረታዊ ለውጥ ማምጣት አይችሉም።—ምሳሌ 21:30፤ ኤርምያስ 10:23

ምን ዓይነት ለውጥ መደረግ አለበት? አምላክ የሰው ልጆች ምድርን እንዳያጠፏት እንደሚያስቆማቸው ተናግሯል። (ራእይ 11:18) አምላክ፣ ምድርን እያበላሹ ያሉትን መንግሥታት እና ሰብዓዊውን ማኅበረሰብ ለማስተካከል ከመሞከር ይልቅ በአዲስ መንግሥትና በአዲስ ማኅበረሰብ ይተካቸዋል። (ራእይ 21:1) ይሖዋ “እነሆ፣ ሁሉንም ነገር አዲስ አደርጋለሁ” ያለው ለዚህ ነው።—ራእይ 21:5

እንዲህ ዓይነት ለውጥ የሚመጣው እንዴት ነው? ይሖዋ ሰብዓዊ መንግሥታትን አጥፍቶ ሰማያዊ በሆነ መንግሥት ይተካቸዋል፤ ይህ መንግሥት የአምላክ መንግሥት ይባላል። ኢየሱስ ክርስቶስ ንጉሥ ሆኖ የሚያስተዳድረው ይህ መንግሥት ምድርን ይገዛል።—ዳንኤል 2:44፤ ማቴዎስ 6:10

የአምላክ መንግሥት የሰው ልጆችን በማስተማር በአምላክ የጽድቅ መሥፈርቶች እንዲመሩ ያደርጋቸዋል። የሰው ልጆች ለፈጣሪያቸው እውቅና ሲሰጡ እና የእሱን መመሪያ ሲታዘዙ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምተው መኖር ይችላሉ። (ኢሳይያስ 11:9) የአምላክ መንግሥት፣ ዜጎቹ ምድርን በማይጎዳ መልኩ የተመቻቸ ሕይወት እንዲመሩ የሚያደርጋቸው እንዴት እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። የአምላክ መንግሥት የሚከተሉትን ነገሮች ያደርጋል፦

  • ሁሉም ሰው በቂ ምግብ እንዲያገኝ ያደርጋል።—መዝሙር 72:16

  • የተፈጥሮ ሀብቶችን ያድሳል።—ኢሳይያስ 35:1, 2, 6, 7

  • በሰዎችና በእንስሳት መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖር ያደርጋል።—ኢሳይያስ 11:6-8፤ ሆሴዕ 2:18

  • የተፈጥሮ አደጋዎችን ያስቀራል።—ማርቆስ 4:37-41

የአምላክ መንግሥት እነዚህን ለውጦች በቅርቡ እንደሚያመጣ መጠበቅ እንችላለን። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት “የአምላክ መንግሥት ምድርን የሚገዛው መቼ ነው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

a ይሖዋ የአምላክ የግል ስም ነው።—መዝሙር 83:18

በአሁኑ ወቅት ምድርን በአግባቡ መያዝ የምንችለው እንዴት ነው?

በምድር ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ሙሉ በሙሉ የሚያስተካክለው የአምላክ መንግሥት እንደሆነ እንገነዘባለን፤ ሆኖም በአሁኑ ወቅትም ቢሆን ምድርን በአግባቡ ለመያዝ አንዳንድ እርምጃዎችን መውሰድ እንችላለን። ለምሳሌ፣ ብክለትን መቀነስ እንዲሁም በአካባቢያችን ያሉ የቆሻሻ አወጋገድ መመሪያዎችን መከተል እንችላለን።—ዮሐንስ 6:12, 13፤ ሮም 13:1, 5

  • ብሬት

    ብሬት የተፈጥሮ ንብረት አማካሪ የነበረ አሁን ግን ጡረታ የወጣ ግለሰብ ነው። ስለ ሥነ ምሕዳር ያካበተው እውቀት ምድርን የሚታደግ ፈጣሪ እንዳለ እንዲገነዘብ ረድቶታል። የብሬትን ታሪክ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

  • በይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት ሁለት ሠራተኞች አዲስ የተሠሩ ሕንፃዎችን ሲመለከቱ።

    የይሖዋ ምሥክሮች ለፈጣሪ አክብሮት የሚያሳዩበት አንዱ መንገድ ትላልቅ ግንባታዎችን ሲያካሂዱ በአካባቢው ላይ ጉዳት ላለማድረስ የተለያዩ ዘዴዎችን መጠቀም ነው። የይሖዋ ምሥክሮች በዚህ ረገድ ያከናወኑትን ነገር ለማየት ለይሖዋ ክብር የሚያመጣ በአካባቢው ላይ ጉዳት የማያደርስ ንድፍ የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት።

ስለ ምድር የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ዘፍጥረት 2:15፦ “ይሖዋ አምላክ ሰውየውን ወስዶ እንዲያለማውና እንዲንከባከበው በኤደን የአትክልት ስፍራ አስቀመጠው።”

ትርጉሙ፦ አምላክ፣ ሰዎች መኖሪያቸው የሆነችውን ምድር እንዲንከባከቡ አደራ ሰጥቷቸው ነበር።

ዘፍጥረት 1:28፦ “አምላክ ባረካቸው፤ እንዲህም አላቸው፦ ‘ብዙ ተባዙ፤ ምድርንም ሙሏት፤ ግዟትም። እንዲሁም የባሕር ዓሣዎችን፣ በሰማያት ላይ የሚበርሩ ፍጥረታትንና በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረታትን በሙሉ ግዟቸው።’”

ትርጉሙ፦ ሰዎች እንስሳትን እንዲንከባከቡ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው ነበር።

ኢሳይያስ 45:18፦ “ሰማያትን የፈጠረው፣ እውነተኛው አምላክ፣ ምድርን የሠራትና ያበጃት፣ አጽንቶም የመሠረታት፣ መኖሪያ እንድትሆን እንጂ ለከንቱ ያልፈጠራት ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘እኔ ይሖዋ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ የለም።’”

ትርጉሙ፦ አምላክ ለምድር የነበረው ዓላማ አልተለወጠም። ምድር፣ አምላክ መጀመሪያ ላይ ያሰበውን ነገር በሚፈጽሙ ሰዎች ትሞላለች።

መዝሙር 37:29፦ “ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፤ በእሷም ላይ ለዘላለም ይኖራሉ።”

ትርጉሙ፦ የአምላክን የጽድቅ መሥፈርቶች የሚከተሉ ሰዎች በምድር ላይ ለዘላለም የመኖር መብት ያገኛሉ።

መዝሙር 98:6-8፦ “በንጉሡ በይሖዋ ፊት በድል አድራጊነት እልል በሉ። ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ፣ መሬትና በላይዋ የሚኖር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰሙ። ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፤ ተራሮችም በአንድነት በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ።”

ትርጉሙ፦ የአምላክ አገዛዝ፣ ተፈጥሮ በአግባቡ እንዲያዝ ያደርጋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ