የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 2 ሳሙኤል 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

2 ሳሙኤል የመጽሐፉ ይዘት

      • ዳዊት በመላው እስራኤል ላይ ነገሠ (1-5)

      • ኢየሩሳሌም ተያዘች (6-16)

        • የዳዊት ከተማ ተብላ የምትጠራው ጽዮን (7)

      • ዳዊት ፍልስጤማውያንን ድል አደረገ (17-25)

2 ሳሙኤል 5:1

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሥጋ ዘመዶችህ ነን።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 2:1, 11፤ 1ዜና 12:23
  • +1ዜና 11:1-3

2 ሳሙኤል 5:2

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “እስራኤልን የምታስወጣውና የምታስገባው።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 18:13፤ 25:28
  • +ዘፍ 49:10፤ 1ሳሙ 16:1፤ 25:30፤ 2ሳሙ 6:21፤ 7:8፤ 1ዜና 28:4፤ መዝ 78:71

2 ሳሙኤል 5:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 11:17
  • +1ሳሙ 16:13፤ 2ሳሙ 2:4፤ ሥራ 13:22

2 ሳሙኤል 5:4

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 29:26, 27

2 ሳሙኤል 5:5

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 14:18

2 ሳሙኤል 5:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፀ 23:23፤ ኢያሱ 15:63፤ መሳ 1:8, 21
  • +1ዜና 11:4-6

2 ሳሙኤል 5:7

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 2:10፤ ነህ 12:37

2 ሳሙኤል 5:8

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የዳዊት ነፍስ የምትጠላቸውን።”

2 ሳሙኤል 5:9

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ስፍራውንም የዳዊት ከተማ ብሎ ጠራው” ማለትም ሊሆን ይችላል።

  • *

    ወይም “ከሚሎ።” “መሙላት” የሚል ትርጉም ያለው የዕብራይስጥ ቃል ነው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 9:15, 24፤ 11:27፤ 2ዜና 32:5
  • +1ዜና 11:7-9

2 ሳሙኤል 5:10

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ሳሙ 16:13፤ 2ሳሙ 3:1
  • +1ሳሙ 17:45

2 ሳሙኤል 5:11

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ቤተ መንግሥት።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ነገ 5:1, 8
  • +2ዜና 2:3
  • +2ሳሙ 7:2፤ 1ዜና 14:1, 2

2 ሳሙኤል 5:12

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 7:16፤ መዝ 41:11፤ 89:21
  • +1ነገ 10:9፤ 2ዜና 2:11
  • +መዝ 89:27

2 ሳሙኤል 5:13

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 15:16
  • +1ዜና 3:5-9፤ 14:3-7

2 ሳሙኤል 5:14

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ሉቃስ 3:23, 31
  • +2ሳሙ 12:24

2 ሳሙኤል 5:17

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 5:3
  • +መዝ 2:2
  • +1ሳሙ 22:1, 5፤ 24:22፤ 2ሳሙ 23:14፤ 1ዜና 14:8

2 ሳሙኤል 5:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:8, 12፤ 1ዜና 11:15፤ 14:9

2 ሳሙኤል 5:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 27:21
  • +1ዜና 14:10-12

2 ሳሙኤል 5:20

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “በመደረማመስ የተዋጣለት” የሚል ትርጉም አለው።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ሳሙ 22:41
  • +ኢሳ 28:21

2 ሳሙኤል 5:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዳዊትና ሰዎቹ ጣዖታቱን ወስደው እንዳጠፏቸው ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። አንደኛ ዜና 14:12ን ተመልከት።

2 ሳሙኤል 5:22

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ረባዳማ ሜዳ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 15:8, 12፤ 1ዜና 11:15፤ 14:13-17

2 ሳሙኤል 5:23

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    “ባካ” የሚለው ስም የዕብራይስጥ ቃል ነው። የተክሉ ዓይነት በትክክል አይታወቅም።

2 ሳሙኤል 5:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 18:21, 24
  • +ኢያሱ 16:10
  • +ዘሌ 26:7

ተዛማጅ ሐሳብ

2 ሳሙ. 5:12ሳሙ 2:1, 11፤ 1ዜና 12:23
2 ሳሙ. 5:11ዜና 11:1-3
2 ሳሙ. 5:21ሳሙ 18:13፤ 25:28
2 ሳሙ. 5:2ዘፍ 49:10፤ 1ሳሙ 16:1፤ 25:30፤ 2ሳሙ 6:21፤ 7:8፤ 1ዜና 28:4፤ መዝ 78:71
2 ሳሙ. 5:32ነገ 11:17
2 ሳሙ. 5:31ሳሙ 16:13፤ 2ሳሙ 2:4፤ ሥራ 13:22
2 ሳሙ. 5:41ዜና 29:26, 27
2 ሳሙ. 5:5ዘፍ 14:18
2 ሳሙ. 5:6ዘፀ 23:23፤ ኢያሱ 15:63፤ መሳ 1:8, 21
2 ሳሙ. 5:61ዜና 11:4-6
2 ሳሙ. 5:71ነገ 2:10፤ ነህ 12:37
2 ሳሙ. 5:91ነገ 9:15, 24፤ 11:27፤ 2ዜና 32:5
2 ሳሙ. 5:91ዜና 11:7-9
2 ሳሙ. 5:101ሳሙ 16:13፤ 2ሳሙ 3:1
2 ሳሙ. 5:101ሳሙ 17:45
2 ሳሙ. 5:111ነገ 5:1, 8
2 ሳሙ. 5:112ዜና 2:3
2 ሳሙ. 5:112ሳሙ 7:2፤ 1ዜና 14:1, 2
2 ሳሙ. 5:122ሳሙ 7:16፤ መዝ 41:11፤ 89:21
2 ሳሙ. 5:121ነገ 10:9፤ 2ዜና 2:11
2 ሳሙ. 5:12መዝ 89:27
2 ሳሙ. 5:132ሳሙ 15:16
2 ሳሙ. 5:131ዜና 3:5-9፤ 14:3-7
2 ሳሙ. 5:14ሉቃስ 3:23, 31
2 ሳሙ. 5:142ሳሙ 12:24
2 ሳሙ. 5:172ሳሙ 5:3
2 ሳሙ. 5:17መዝ 2:2
2 ሳሙ. 5:171ሳሙ 22:1, 5፤ 24:22፤ 2ሳሙ 23:14፤ 1ዜና 14:8
2 ሳሙ. 5:18ኢያሱ 15:8, 12፤ 1ዜና 11:15፤ 14:9
2 ሳሙ. 5:19ዘኁ 27:21
2 ሳሙ. 5:191ዜና 14:10-12
2 ሳሙ. 5:202ሳሙ 22:41
2 ሳሙ. 5:20ኢሳ 28:21
2 ሳሙ. 5:22ኢያሱ 15:8, 12፤ 1ዜና 11:15፤ 14:13-17
2 ሳሙ. 5:25ኢያሱ 18:21, 24
2 ሳሙ. 5:25ኢያሱ 16:10
2 ሳሙ. 5:25ዘሌ 26:7
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
2 ሳሙኤል 5:1-25

ሁለተኛ ሳሙኤል

5 ከጊዜ በኋላ የእስራኤል ነገዶች በሙሉ በኬብሮን+ ወደሚገኘው ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉት፦ “እንግዲህ እኛ የአጥንትህ ፍላጭ፣ የሥጋህም ቁራጭ ነን።*+ 2 ባለፉት ዘመናት ሳኦል ንጉሣችን በነበረበት ጊዜ እስራኤል ወደ ጦርነት ሲወጣ የምትመራው* አንተ ነበርክ።+ ይሖዋም ‘ሕዝቤን እስራኤልን እረኛ ሆነህ ትጠብቃለህ፣ በእስራኤልም ላይ መሪ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር።”+ 3 በመሆኑም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ንጉሡ ወዳለበት ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም በኬብሮን ከእነሱ ጋር በይሖዋ ፊት ቃል ኪዳን ገባ።+ እነሱም ዳዊትን በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርገው ቀቡት።+

4 ዳዊት በነገሠ ጊዜ 30 ዓመቱ ነበር፤ ለ40 ዓመትም ገዛ።+ 5 በኬብሮን ተቀምጦ በይሁዳ ላይ ለ7 ዓመት ከ6 ወር ገዛ፤ በኢየሩሳሌም+ ሆኖ ደግሞ በመላው እስራኤልና ይሁዳ ላይ ለ33 ዓመት ገዛ። 6 ዳዊትና ሰዎቹም በምድሪቱ የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን+ ለመውጋት ወደ ኢየሩሳሌም ዘመቱ። እነሱም ዳዊትን “ፈጽሞ ወደዚህ አትገባም! ዕውሮችና ሽባዎች እንኳ ያባርሩሃል” በማለት ተሳለቁበት። ይህን ያሉት ‘ዳዊት ፈጽሞ ወደዚህ አይገባም’ ብለው ስላሰቡ ነበር።+ 7 ይሁን እንጂ ዳዊት በአሁኑ ጊዜ የዳዊት ከተማ+ ተብላ የምትጠራውን የጽዮንን ምሽግ ያዘ። 8 ስለሆነም በዚያን ቀን ዳዊት “በኢያቡሳውያን ላይ ጥቃት የሚሰነዝር ማንኛውም ሰው ዳዊት የሚጠላቸውን* ‘ሽባዎችንና ዕውሮችን’ ለመምታት በውኃ መውረጃው ቦይ በኩል ማለፍ አለበት!” አለ። “ዕውርና ሽባ ፈጽሞ ወደ ቤት አይገቡም” የሚባለውም በዚህ የተነሳ ነው። 9 ከዚያም ዳዊት በምሽጉ ውስጥ መኖር ጀመረ፤ ስፍራውም የዳዊት ከተማ ተብሎ ይጠራ ነበር፤* እሱም ከጉብታው*+ አንስቶ ወደ ውስጥ ዙሪያውን መገንባት ጀመረ።+ 10 በዚህ ሁኔታ ዳዊት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ ሄደ፤+ የሠራዊት አምላክ ይሖዋም ከእሱ ጋር ነበር።+

11 የጢሮስ ንጉሥ ኪራም+ መልእክተኞችን ወደ ዳዊት ላከ፤ እንዲሁም የአርዘ ሊባኖስ ሳንቃዎችን፣+ አናጺዎችንና ለቅጥር የሚሆን ድንጋይ የሚጠርቡ ሰዎችን ላከ፤ እነሱም ለዳዊት ቤት* መሥራት ጀመሩ።+ 12 ዳዊትም ይሖዋ በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናውና+ ስለ ሕዝቡ ስለ እስራኤል ሲል+ መንግሥቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለት+ አወቀ።

13 ዳዊት ከኬብሮን ከመጣ በኋላ በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ቁባቶችን+ አስቀመጠ፤ እንዲሁም ሌሎች ሚስቶችን አገባ፤ ተጨማሪ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም ተወለዱለት።+ 14 በኢየሩሳሌም ሳለ የተወለዱለት ልጆች ስም ይህ ነው፦ ሻሙአ፣ ሾባብ፣ ናታን፣+ ሰለሞን፣+ 15 ይብሃር፣ ኤሊሹዓ፣ ኔፌግ፣ ያፊአ፣ 16 ኤሊሻማ፣ ኤሊያዳ እና ኤሊፌሌት።

17 ፍልስጤማውያንም በሙሉ ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን+ ሲሰሙ እሱን ፍለጋ ወጡ።+ ዳዊትም ይህን ሲሰማ ወደ ምሽጉ ወረደ።+ 18 ከዚያም ፍልስጤማውያን መጥተው በረፋይም ሸለቆ*+ ተበታትነው ሰፈሩ። 19 ዳዊትም “ወጥቼ ፍልስጤማውያንን ልግጠም? አንተስ በእጄ አሳልፈህ ትሰጣቸዋለህ?” ሲል ይሖዋን ጠየቀ።+ ይሖዋም ዳዊትን “አዎ ውጣ፤ እኔም በእርግጥ ፍልስጤማውያንን በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ” አለው።+ 20 በመሆኑም ዳዊት ወደ በዓልጰራጺም መጥቶ በዚያ መታቸው። እሱም “ይሖዋ፣ ውኃ እንደጣሰው ግድብ ጠላቶቼን በፊቴ ደረማመሳቸው” አለ።+ ከዚህም የተነሳ ያን ቦታ በዓልጰራጺም*+ ብሎ ጠራው። 21 ፍልስጤማውያንም ጣዖቶቻቸውን በዚያ ጥለው ሸሹ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ወሰዷቸው።*

22 ከጊዜ በኋላ ፍልስጤማውያን እንደገና ወደ ረፋይም ሸለቆ*+ መጥተው ተበታትነው ሰፈሩ። 23 ዳዊትም ይሖዋን ጠየቀ፤ እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “በቀጥታ አትውጣ። ይልቁንም ከኋላቸው ዞረህ በባካ* ቁጥቋጦዎቹ ፊት ለፊት ግጠማቸው። 24 በባካ ቁጥቋጦዎቹ አናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ቆራጥ እርምጃ ውሰድ፤ ምክንያቱም ይህ በሚሆንበት ጊዜ ይሖዋ የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመምታት በፊትህ ወጥቷል ማለት ነው።” 25 በመሆኑም ዳዊት ልክ ይሖዋ እንዳዘዘው አደረገ፤ ፍልስጤማውያንንም ከጌባ+ አንስቶ እስከ ጌዜር+ ድረስ መታቸው።+

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ