የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ዜና መዋዕል 5
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

1 ዜና መዋዕል የመጽሐፉ ይዘት

      • የሮቤል ዘሮች (1-10)

      • የጋድ ዘሮች (11-17)

      • አጋራውያን ድል ተመቱ (18-22)

      • የምናሴ ነገድ እኩሌታ (23-26)

1 ዜና መዋዕል 5:1

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 29:32፤ 49:3, 4
  • +ዘፍ 35:22
  • +ዘፍ 49:22, 26፤ ኢያሱ 14:4

1 ዜና መዋዕል 5:2

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 49:8, 10፤ ዘኁ 2:3፤ 10:14፤ መሳ 1:1, 2፤ መዝ 60:7
  • +ማቴ 2:6፤ ዕብ 7:14

1 ዜና መዋዕል 5:3

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘፍ 46:9፤ ዘፀ 6:14

1 ዜና መዋዕል 5:6

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 16:7

1 ዜና መዋዕል 5:8

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 2:36
  • +ዘኁ 32:34, 38፤ ኢያሱ 13:15, 17፤ ሕዝ 25:9, 10

1 ዜና መዋዕል 5:9

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 22:9
  • +ዘፍ 15:18፤ ዘዳ 1:7፤ ኢያሱ 1:4፤ 2ሳሙ 8:3

1 ዜና መዋዕል 5:11

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 3:8, 10፤ ኢያሱ 12:4, 5

1 ዜና መዋዕል 5:16

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “ዙሪያ።”

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘኁ 32:1
  • +ዘዳ 3:3, 13፤ 32:14

1 ዜና መዋዕል 5:17

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ዳግማዊ ኢዮርብዓምን ያመለክታል።

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +2ነገ 15:32፤ 2ዜና 27:1፤ ኢሳ 1:1፤ ሆሴዕ 1:1፤ ሚክ 1:1
  • +2ነገ 14:16, 28

1 ዜና መዋዕል 5:18

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ቃል በቃል “ደጋን የሚረግጡና።”

1 ዜና መዋዕል 5:19

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +1ዜና 5:10
  • +ዘፍ 25:13, 15፤ 1ዜና 1:31

1 ዜና መዋዕል 5:20

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +መዝ 20:7፤ 22:4

1 ዜና መዋዕል 5:21

የግርጌ ማስታወሻዎች

  • *

    ወይም “የሰው ነፍሳት።”

1 ዜና መዋዕል 5:22

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 10:42፤ 1ሳሙ 17:45, 47፤ 2ዜና 20:15
  • +2ነገ 15:29፤ 17:6

1 ዜና መዋዕል 5:23

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ኢያሱ 13:29, 30
  • +ዘዳ 4:47, 48

1 ዜና መዋዕል 5:25

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዘዳ 5:7-9፤ መሳ 2:17፤ 8:33፤ 2ነገ 17:10, 11

1 ዜና መዋዕል 5:26

የኅዳግ ማጣቀሻዎች

  • +ዕዝራ 1:1፤ ምሳሌ 21:1
  • +2ነገ 15:19, 29
  • +2ነገ 17:6፤ 18:11

ተዛማጅ ሐሳብ

1 ዜና 5:1ዘፍ 29:32፤ 49:3, 4
1 ዜና 5:1ዘፍ 35:22
1 ዜና 5:1ዘፍ 49:22, 26፤ ኢያሱ 14:4
1 ዜና 5:2ዘፍ 49:8, 10፤ ዘኁ 2:3፤ 10:14፤ መሳ 1:1, 2፤ መዝ 60:7
1 ዜና 5:2ማቴ 2:6፤ ዕብ 7:14
1 ዜና 5:3ዘፍ 46:9፤ ዘፀ 6:14
1 ዜና 5:62ነገ 16:7
1 ዜና 5:8ዘዳ 2:36
1 ዜና 5:8ዘኁ 32:34, 38፤ ኢያሱ 13:15, 17፤ ሕዝ 25:9, 10
1 ዜና 5:9ኢያሱ 22:9
1 ዜና 5:9ዘፍ 15:18፤ ዘዳ 1:7፤ ኢያሱ 1:4፤ 2ሳሙ 8:3
1 ዜና 5:11ዘዳ 3:8, 10፤ ኢያሱ 12:4, 5
1 ዜና 5:16ዘኁ 32:1
1 ዜና 5:16ዘዳ 3:3, 13፤ 32:14
1 ዜና 5:172ነገ 15:32፤ 2ዜና 27:1፤ ኢሳ 1:1፤ ሆሴዕ 1:1፤ ሚክ 1:1
1 ዜና 5:172ነገ 14:16, 28
1 ዜና 5:191ዜና 5:10
1 ዜና 5:19ዘፍ 25:13, 15፤ 1ዜና 1:31
1 ዜና 5:20መዝ 20:7፤ 22:4
1 ዜና 5:22ኢያሱ 10:42፤ 1ሳሙ 17:45, 47፤ 2ዜና 20:15
1 ዜና 5:222ነገ 15:29፤ 17:6
1 ዜና 5:23ኢያሱ 13:29, 30
1 ዜና 5:23ዘዳ 4:47, 48
1 ዜና 5:25ዘዳ 5:7-9፤ መሳ 2:17፤ 8:33፤ 2ነገ 17:10, 11
1 ዜና 5:26ዕዝራ 1:1፤ ምሳሌ 21:1
1 ዜና 5:262ነገ 15:19, 29
1 ዜና 5:262ነገ 17:6፤ 18:11
  • አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • 1
  • 2
  • 3
  • 4
  • 5
  • 6
  • 7
  • 8
  • 9
  • 10
  • 11
  • 12
  • 13
  • 14
  • 15
  • 16
  • 17
  • 18
  • 19
  • 20
  • 21
  • 22
  • 23
  • 24
  • 25
  • 26
አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
1 ዜና መዋዕል 5:1-26

አንደኛ ዜና መዋዕል

5 የእስራኤል የበኩር ልጅ የሆነው የሮቤል+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሱ በኩር ቢሆንም እንኳ የአባቱን መኝታ ስላረከሰ+ የብኩርና መብቱ ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ+ ወንዶች ልጆች ተሰጠ፤ ከዚህም የተነሳ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የብኩርና መብት እንዳለው ተደርጎ አልተመዘገበም። 2 ይሁዳ+ ከወንድሞቹ የሚበልጥ ከመሆኑም ሌላ መሪ+ የሚሆነው የተገኘው ከእሱ ነው፤ ሆኖም የብኩርና መብቱን ያገኘው ዮሴፍ ነበር። 3 የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ወንዶች ልጆች ሃኖክ፣ ፓሉ፣ ኤስሮን እና ካርሚ+ ነበሩ። 4 ሸማያህ የኢዩኤል ልጅ ነበር፤ የሸማያህ ልጅ ጎግ፣ የጎግ ልጅ ሺምአይ፣ 5 የሺምአይ ልጅ ሚክያስ፣ የሚክያስ ልጅ ረአያህ፣ የረአያህ ልጅ ባአል፣ 6 የባአል ልጅ ቤኤራህ ነበር፤ የአሦር ንጉሥ ቴልጌልቴልፌልሶር+ የሮቤላውያን አለቃ የሆነውን ቤኤራህን በግዞት ወሰደው። 7 ወንድሞቹ በየቤተሰቦቻቸውና በየዘር ሐረጋቸው ሲዘረዘሩ እንደሚከተለው ነው፦ መሪ የሆነው የኢዔል፣ ዘካርያስ፣ 8 የኢዩኤል ልጅ፣ የሼማ ልጅ፣ የአዛዝ ልጅ ቤላ፤ እሱ ከአሮዔር+ አንስቶ እስከ ነቦ እንዲሁም እስከ በዓልመዖን+ ድረስ ይኖር ነበር። 9 መንጎቻቸው በጊልያድ ምድር+ እጅግ በዝተው ስለነበር በስተ ምሥራቅ በኤፍራጥስ ወንዝ+ በኩል እስካለው፣ ምድረ በዳው እስከሚጀምርበት ቦታ ድረስ ሰፈረ። 10 በሳኦል ዘመን በአጋራውያን ላይ ጦርነት ከፍተው ድል መቷቸው፤ በመሆኑም ከጊልያድ በስተ ምሥራቅ ባለው ክልል ሁሉ በድንኳኖቻቸው ውስጥ ኖሩ።

11 ከእነሱ ጋር የሚዋሰኑት የጋድ ዘሮች ደግሞ ከባሳን አንስቶ እስከ ሳልካ+ ባለው ምድር ላይ ኖሩ። 12 ኢዩኤል መሪ ነበር፤ ሁለተኛው ሻፋም ሲሆን ያናይ እና ሻፋጥ ደግሞ በባሳን መሪዎች ነበሩ። 13 ከአባቶቻቸው ቤት የሆኑት ወንድሞቻቸውም ሚካኤል፣ መሹላም፣ ሳባ፣ ዮራይ፣ ያካን፣ ዚአ እና ኤቤር ሲሆኑ በአጠቃላይ ሰባት ነበሩ። 14 እነዚህ የቡዝ ልጅ፣ የያህዶ ልጅ፣ የየሺሻይ ልጅ፣ የሚካኤል ልጅ፣ የጊልያድ ልጅ፣ የያሮሃ ልጅ፣ የሁሪ ልጅ፣ የአቢሃይል ወንዶች ልጆች ነበሩ። 15 የአባቶቻቸው ቤት መሪ የጉኒ ልጅ፣ የአብዲዔል ልጅ አሂ ነበር። 16 እነሱም በጊልያድ፣+ በባሳን፣+ በእነሱ ሥር* ባሉት ከተሞች እንዲሁም በሳሮን የግጦሽ መሬቶች ሁሉ እስከ ዳርቻዎቻቸው ድረስ ተቀመጡ። 17 እነዚህ ሁሉ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮዓታም+ እና በእስራኤል ንጉሥ በኢዮርብዓም*+ ዘመን በትውልድ መዝገቡ ላይ ሰፈሩ።

18 ሮቤላውያን፣ ጋዳውያንና የምናሴ ነገድ እኩሌታ 44,760 ኃያላን ተዋጊዎችን ያቀፈ ሠራዊት ነበራቸው፤ እነሱም ጋሻና ሰይፍ የታጠቁ፣ ደጋን ያነገቡና* ለውጊያ የሠለጠኑ ነበሩ። 19 እነዚህ ተዋጊዎች በአጋራውያን፣+ በየጡር፣ በናፊሽ+ እና በኖዳብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። 20 በጦርነቱ ወቅት አምላክ እንዲረዳቸው ስለጠየቁ እንዲሁም በእሱ ስለታመኑና+ እሱም ልመናቸውን ስለሰማ ከእነሱ ጋር በሚዋጉበት ጊዜ እርዳታ አገኙ፤ በመሆኑም አጋራውያንና ከእነሱ ጋር የነበሩት ሁሉ እጃቸው ላይ ወደቁ። 21 እነሱም መንጎቻቸውን ይኸውም 50,000 ግመሎች፣ 250,000 በጎችና 2,000 አህዮች እንዲሁም 100,000 ሰዎች* ማረኩ። 22 የተዋጋላቸው እውነተኛው አምላክ ስለነበር+ ተገድለው የወደቁት ብዙ ነበሩ። በግዞት+ እስከተወሰዱበትም ጊዜ ድረስ በእነሱ ቦታ ላይ ኖሩ።

23 የምናሴ ነገድ እኩሌታ+ ዘሮች ከባሳን እስከ በዓልሄርሞን፣ እስከ ሰኒር እንዲሁም እስከ ሄርሞን ተራራ+ ድረስ ባለው ምድር ላይ ኖሩ። ቁጥራቸውም እጅግ ብዙ ነበር። 24 የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች እነዚህ ነበሩ፦ ኤፌር፣ ይሽኢ፣ ኤሊዔል፣ አዝርዔል፣ ኤርምያስ፣ ሆዳውያህ እና ያህዲኤል፤ እነዚህ ሰዎች ኃያላን ተዋጊዎችና ስመ ገናና ሲሆኑ የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ነበሩ። 25 ሆኖም ለአባቶቻቸው አምላክ ታማኞች ሳይሆኑ ቀሩ፤ ደግሞም አምላክ ከፊታቸው ካጠፋቸው ከምድሪቱ ሕዝቦች አማልክት ጋር አመነዘሩ።+ 26 በመሆኑም የእስራኤል አምላክ የአሦርን ንጉሥ የፑልን መንፈስ አነሳሳ+ (የአሦርን ንጉሥ የቴልጌልቴልፌልሶርን+ መንፈስ ማለት ነው)፤ እሱም ሮቤላውያንን፣ ጋዳውያንንና የምናሴ ነገድ እኩሌታን በግዞት ወደ ሃላህ፣ ወደ ሃቦር፣ ወደ ሃራ እና ወደ ጎዛን+ ወንዝ ወሰዳቸው፤ እስከ ዛሬም በዚያ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ጽሑፎች (2011-2025)
ውጣ
ግባ
  • የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ